NaFi Printing and Related Work

NaFi Printing and Related Work We Design, We Print, We Care

01/02/2026
የ90ዎቹ ትዝታ ያለባችሁ ሁሉ… ወዴት አላችሁ? 🎶✨ያ ድምፅ፣ ያ ግሩቭ፣ ያ ትዝታ… በአንድ ምሽት ይመለሳል!🔥 Timeless Groove – የ90ዎቹ ሙዚቃ ምሽት📅 ጥር 30 | 🕛 ከምሽቱ 12...
01/02/2026

የ90ዎቹ ትዝታ ያለባችሁ ሁሉ… ወዴት አላችሁ? 🎶✨
ያ ድምፅ፣ ያ ግሩቭ፣ ያ ትዝታ… በአንድ ምሽት ይመለሳል!

🔥 Timeless Groove – የ90ዎቹ ሙዚቃ ምሽት
📅 ጥር 30 | 🕛 ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ
📍 ዲሎዎፖል ሆቴል
🎧 ከተወዳጅ እና ዝነኛ ዲጄዎች ጋር ሳቅ፣ ጫዋታ እና የትዝታ ማዕበል!

🎟️ ትኬት: በቴሌብር እንዲሁም ቦሌ ሸገር ጀርባ ባኮስ ላውንጅ
⭐ VIP: 1000 ብር | 🎫 መደበኛ: 500 ብር

አዘጋጅ: ሞሪያድ ኤቨንትስ × ኒርቫና ኢንተርቴመንት
Timeless Groove ይደምቃል… ግሩቩም ይቀጥላል! ✅

Happy
11/09/2025

Happy

06/07/2025

እንኳን ወደ 'ልጆች የዓለም' ቻናል በደህና መጣችሁ! በዚህ አጭር የመግቢያ ቪዲዮ፣ ቻናላችን ምን እንደሚመስል እና ምን አይነት አስደሳች ጉዞ እንደሚጠብቃችሁ እናሳያችኋለን።'ልጆች የዓ.....

03/01/2024

16/08/2023

(ጎሥዐ ልብየ ቃለ ሠናይ....)
የበሬ መንኳኳት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። ሰዐቱ ከሌሊቱ 10:30 ይላል፣ አከራዬ ከኔ ቀድመው ነቅተው ለኪዳን ለመቀስቀስ ነበር በሬን የመቱት። እኔ ወጣት ሆኜ በእሳቸው በመቀስቀሴ እፍረት ነገር ውልብ አለብኝ። ወዲያው ደግሞ የዩንቨርሲቲ ጊዜዬ ታወሰኝ።

የመጀመሪያ ዲግሪዬን የተማርኩት በመቀሌ ዩንቨርሲቲ ነበር። የኢንጅነሪንግ ተማሪ ስለነበርኩ የተመደብኩት እንዳ ኢየሱስ ካምፓስ ነበር። ፍሬሽ ተማሪ ሆኜ ወደ ጊቢው ከገባሁ በኋላ ከኛ የቀደሙ /ሲኒየር/ ኦርቶዶክሳውያን በእንዳ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር አዘጋጅተው እግራችንን ወርደው አጥበው ከተቀበሉን በኋላ ፎርም አስሞልተው በጊቢ ጉባዔ ከሚገኙ የአገልግሎት ክፍላት መደቡን። ክፍላቱም እንደ ትልቁ ጊቢ ጉባኤ በድጋሚ እግር አጥበው ተቀበሉን። እኔ የገባሁበት ክፍል የመዝሙርና ኪነ ጥበብ ክፍል ነበር። በመጀመሪያው ዓመታችን በአስኳላው ትምህርት እንዳንደክም ሲባል ወደ አገልግሎት እንድንገባ ባንደረግም በየዕለቱ በቤተ ክርስቲያን የኪዳን ጸሎት ላይ እንገኝና ማታ ማታ ኮርስ እንማር ነበር።

ታዲያ የፍሬሽማን ሕይወት ብዙ አዳዲስ ነገሮች ስለነበሩትና ከቤተሰብ መራቅ የሚፈጥረው መረበሽ ስላለ በየክፍላቱ ለተመደብን ልጆች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሻል ያሉ አንድ ወንድና አንድ ሴት በበላይነት ይመደቡልንና በነሱ እናትና አባትነት ቤተሰብ ይመሰረታል። እናትና አባቶቹም በየሌሊት ለኪዳን ለመቀስቀስ ይደውሉልን ነበር። እንቅልፋም ስለነበርኩ አባቴ ሲደውል ስልኬን እየዘጋሁ እተኛ ስለነበር ዶርሜ ድረስ መጥቶ አንኳክቶ ቀስቅሶ ነበር ኪዳን ይዞኝ ይሄድ የነበረው።

የዛሬ የአከራዬ አቀሳቀስ ያንን ደስ የሚል ቆይታዬን አስታወሰኝና ለልጅህ ሌላ አባት የሰጠህ እግዚአብሔር ተመስገን ብዬ እያመሰገንኩ በሩን ከፈትኩት።

ከአከራዬ ጋር አብረን ኪዳን አድርሰን ከተመለስን በኋላ ወደ ቤት ገብቼ ቦርሳዬን ይዤ ወደ ሥራ ለመሄድ ከቤት ወጣሁ። ዛሬ ሰኞ ነው። የዛሬ ሳምንት ነበር "ውዳሴሃ.." የምትል ድምጽ ወደ ጆሮዬ ገብታ በሕይወቴ ላይ አብዮት ያስነሳችው። በእርግጥ መጾም መጀመሬ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄዴ ትንሽ ለውጥ ቢመስልም በውስጤ የፈጠረው ምቾት ግን ልዩ ነበር። ለዛ ነው የሳምንቱን እንቅስቃሴ አብዮት ብዬ ያልኩት። ሳምንት ድምፅ የሰማሁበት ቦታ ላይ ዛሬም ትርጓሜ እየተሰማ ነው እንደኔ ዓይነቱን ሌላውን ሊጣራ።

ብዙም ሳልቆይ ወደ መስሪያ ቦታ የሚወስደኝ ታክሲ መጣና ገባሁ። ከመኪናው ቴፕ መዝሙር ይሰማል። "...ጎሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ወአነ እየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም..." መዝሙሩ ከቅዳሴ ማርያም መግቢያ የተወሰደ ነበር።

የብህንሳው ኤጲስ ቆጶሱ አባ ሕርያቆስ ቅዳሴዋን የጀመረው " ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ..." እያለ ነበር። በታሪካቸው ከምወሰድባቸው አባቶች አንዱ ናቸው። በመገፋታቸውና በመናቃቸው ውስጥ የነበረች ትህትናና ጽድቅ ታላቋን ድርሰት አስገኘችላቸው። ይህች ድርሰት የሰው ፈጠራ አልነበረችም የመንፈስ ቅዱስ እንጂ።

የኔ ልቦና ግን በጎ ነገርን ያወጣው መቼ ነው። ከልቤ ባሕር መልካሙ ነገር የሚፈልቀው መቼ ነው?። ብዙ ዘመን የሆነው ያህል ከአእምሮዬ ርቋል። ራሴን በዓለማዊ ጉዳይ ወጥሬ አምላኬን ከማመስገን፣ ቅዱሳኑን ደጅ ከመጥናት ከራቅኩ ዘመናት አልፈውኛል። ደህና አደርክ ስባል እንኳን እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ጊዜ የሚፈጅ መስሎ ስለሚሰማኝ መልሼ ደህና አደርክ/ሽ ወይ ደግሞ ደህና ብቻ ብዬ ነው የማልፈው።

አንዳንዴ ከሳምንት በፊት የነበረውን ማንነቴን ሳስብ የሆነ ሌላ ሰው እንጂ እኔው ራሴ የሆንኩት አይመስልም። በእርግጥ አሁንም ብዙም ለውጥ የለኝም ግን ቢያንስ ልቦናዬ በጎ ነገርን ማውጣት ጀምሯል።

ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ
እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ
በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ
እኔም የድንግልን ውዳሴዋን እናገራለሁ
መዘንጋት ባለበት ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ።

እኔም የማርያምን ገናነትዋን እናገራለሁ!!!

ከራስ ጋር ሱባኤ - ይቀጥላል...

https://t.me/EMislene

01/08/2023

አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ዘኢትዮጵያ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕ....

ለተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ስጦታ  #ስጦታ  #ተመራቂ
31/07/2023

ለተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ስጦታ #ስጦታ #ተመራቂ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911973231

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NaFi Printing and Related Work posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to NaFi Printing and Related Work:

Share