ኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ

ኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ➵እንኳን ወደ " Ethio Consulting Group" በደህና መጡ !
በታክስና ኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም ተጓዳኝ ጉዳዮች የምክር አገልግሎት ካስፈለገዎ ይደውሉልን።

18/09/2025

ለግንዛቤ :-
°°°°°°°°°
በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 85 መሠረት በታክስ ስሌት ላይ ስህተቶችን ስለማረም አስመልክቶ ባለሥልጣኑ በታክስ ሕግ መሠረት ለታክስ ከፋዩ የሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ በታክስ ሕግ ወይም በጉዳዩ ኩነቶች ላይ የትርጉም ጥያቄ የማያስነሳ የጽሁፍ፣ የሂሳብ ስሌት ወይም ሌላ ማንኛውንም ስህተት የያዘ በሚሆንበት ጊዜ፣ ባለሥልጣኑ ስህተቱን ለማረም ሲባል የታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ወይም ሌላውን ሰነድ የታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ሰነዱ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ዓመታት ውስጥ ማሻሻል ይችላል፡፡

የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/ethio_consulting_group
በቴሌግራም ጥያቄና አስተያየት ፡ https://t.me/ecg_talk
በፌስቡክ ፡ https://www.facebook.com/share/1EbLoWuFTj/

16/09/2025

❝𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 𝐭𝐨 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐂𝐨𝐧𝐬𝐮𝐥𝐭𝐢𝐧𝐠 𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩❞ =================================== በታክስና ኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች ተ....

የኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ(ECG) ቤተሰቦች ዛሬ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ ግብይቶችን በተመለከተ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን እናስታውሳችኋለን:-=====================||=====...
16/09/2025

የኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ(ECG) ቤተሰቦች ዛሬ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ ግብይቶችን በተመለከተ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን እናስታውሳችኋለን:-
=====================||======================
እንደሚታወቀው የሐሰተኛ ደረሰኝ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ግብር ከፋዩች ግብራቸውን በሚያሳውቁበት ወይም ኦዲት በሚደረጉበት ጊዜ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከፍተኛ የሆነ የግብርና ታክስ እዳ ከማስተናገዳቸው በተጨማሪ በህግ ተጠያቂ ሲሆኑ ይታያል። ስለሆነም ይህንን ችግር በዘለቄታው ለመፍታት የአገር ውስጥ ግዢ በሚፈፀምበት ጊዜ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ተገቢ ይሆናል፥
1. የሀገር ውስጥ ግዢ በሚፈጸምበት ወቅት ክፍያ መፈጸም ያለበት ደረሰኙን በተቆረጠበት ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይኖርበታል። ከዚህም በተያያዘ፥
ሀ. ክፍያው የሚፈጸመው በቼክ ከሆነ ቼኩ በሻጭ መፃፍ አለበት
ለ. ክፍያ የሚፈጽመው በባንክ ትልልፍ ወይም ትራንስፈር ከሆነ ገንዘቡ መተላለፍ ያለበት በደረሰኙ የሚገኙ የግለሰብ ወይም የድርጅት ስም ነው
ሐ. ዕቃ አቅራቢው ገንዘብ የሚሰበስበው በተወካይ ከሆነ የተወካዩን ህጋዊ ውክልና ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማስቀመጥ ተገቢ ነው።
2. የሀገር ውስጥ ግዥ በሚፈጸመበት ወቅት ገዥው የዕቃ መረከቢያ ሰነድ(Goods Receiving Voucher) መቁረጥ ይኖርበታል።
እነዚህን ሰነዶች በተገቢ ሁኔታ የያዘ ማንኛውም ግብር ከፋይ በማንኛውም ጊዜ በኦዲትም ይሁን በሌላ ምክንያት የሚያቀርባቸው የግዥ ሰነዶች ሐሰተኛ ሆኖው ቢገኙና በተጨባጭ ከላይ በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የተዘረዘሩ ሰነዶችን የያዘ ከሆነ እራሱንና ድርጅቱን ከተጠያቂነት ያድናል።

የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/ethio_consulting_group
በቴሌግራም ጥያቄና አስተያየት ፡ https://t.me/ecg_talk
በፌስቡክ ፡ https://www.facebook.com/share/1EbLoWuFTj/

❝𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 𝐭𝐨 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐂𝐨𝐧𝐬𝐮𝐥𝐭𝐢𝐧𝐠 𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩❞ =================================== በታክስና ኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች ተ....

15/09/2025

የተከበራችሁ #የኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ(ECG) ቤተሰቦች ዛሬ የታክስ ውሳኔን በተመለከተ አንድ ወሳኝ መልዕክት ልናጋራችሁ ወደናል። በተለያዩ ጊዜያት ለግብር ከፋዩች በኦዲት ወይም በሌሎች ምክንያቶች የታክስ ውሳኔ ተወስኖ ከደረሳቸው በኋላ በውሳኔው ላይ የማይስማሙ ከሆነ ውሳኔው በተወሰነበት ቅርንጫፍ ቅሬታ መግባት የሚችሉት የውሳኔውን 25% ወይም ያመናችሁበትን ከፍላችሁ መሆን አለበት የሚል መከራከሪያ ይቀርባል። ይህ መከራከሪያ በታክስ አስተዳደር 983/2008 አንቀጽ 56(2) እና አንቀጽ 57(3) ከተቀመጠው ድንጋጌ ውጭ የሆነና በደንብ እና መመሪያ ያልተደገፈ የህግ መሰረት የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ ግብርና ታክሱን የወሰነው ቅርንጫፍ ለእቅድ ማሟያነት በራሱ ፈቃድ ያስቀመጠው አስገዳጅ ተግባር ነው። ስለሆነም በየትኛውም ሁኔታ እንደዚህ አይነት ጉዳይ ሲገጥማችሁ በአዋጁ መሰረት
1ኛ. ግብር ከፋዩች የግብሩን 50% ለመክፈል አስገዳጅ ሁኔታ የሚኖረው ተወስኖ በተሰጣቸው የግብርና ታክስ ውሳኔ ግብር ይግባኝ መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ።
2. ግብር ከፋዩች የግብሩን 75% ለመክፈል የሚገደዱት ተወስኖ በደረሳቸው የግብርና ታክስ ውሳኔ ካልተስማሙ ወደ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ብቻ ነው። በዚህም የውሳኔው 75% ድረስ የተከፈለ እንደሆነ በግብር አወሳሰን ሂደት በተጣሱ ህጎች ላይ በፍርድ ቤት ቀርቦ መከራከር ይቻላል።

ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ የኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ(ECG) የውይይት ግሩፕ join ማድረግ ይሳተፉ
https://t.me/ecg_talk

ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/ethio_consulting_group

14/09/2025

== በታክስ ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ የቅሬታ ==

በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ታክስ ከፋይ የውሳኔውን ማስታወቂያ በደረሰው በ21 ቀናት ውስጥ የታክስ ቅሬታ ዝርዝር ማስታወቂያ ለታክስ ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት በጹሑፍ ማቅረብ ይችላል፡፡

ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱ የቅሬታ ማስታወቂያው በአግባቡ አልቀረበም ብሎ ሲያምን ወይም የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ለታክስ ከፋዩ የጹሑፍ ማስታወቂያ ወዲያውኑ ይሰጠዋል፡፡

በታክስ ውሳኔ ላይ ታክስ ከፋዩ ላቀረበው ቅሬታ ለግብር ሰብሳቢ መ/ቤቱ ቅሬታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት አንድ መቶ ሰማንያ ቀናት(በ6 ወራት) ውስጥ ለቅሬታው ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡

በቅሬታ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ማስታወቂያ የጉዳዩን ዋና ፍሬ ነገሮች፣ ግኝቶች እና ለውሳኔ መሠረት የሆኑትን ምክንያቶች እና ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ማቅረብ እንደሚቻል የሚገልጽ መግለጫ ማካተት አለበት፡፡
ግብር ከፋዮች በማንኛቸውም የግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቶች ተወስኖ በሚሰጣቸው የግብር ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ካላቸው ከላይ በዝርዝር በተገለፀው መሰረት ቅሬታቸው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ያልተፈታላቸው ወደሚቀጥለው ሂደት መሄድ ይጠበቅባቸዋል።
1. ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ
ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ግብር ከፋዮች በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተወስኖ የተሰጣቸው የግብር ውሳኔ በግብር ሰብሳቢ ተቋም ቅሬታቸው መፈታት ካልቻለ የሚሄዱበት ቀጣይ ሂደት ነው።
#የይግባኝ ማመልከቻ፤
በውሳኔው ቅር የተሰኘ ሰው የቅሬታ ውሳኔ በደረሰ በ30 ቀናት ውስጥ ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ማመልከቻ ያቀርባል፡፡

በታክስ ስሌት ላይ ከቀረበ ቅሬታ ጋር በተገናኘ በታክስ ከፋይ ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሚቀርብ የይግባኝ ማስታወቂያ በአግባቡ ቀርቧል ሊባል የሚችለው በክርክር ላይ ያለ ታክስ 5ዐ% የተከፈለ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

2. ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ስለማቅረብ፡-

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡

https://t.me/ethio_consulting_group
03/09/2025

https://t.me/ethio_consulting_group

❝𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 𝐭𝐨 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐂𝐨𝐧𝐬𝐮𝐥𝐭𝐢𝐧𝐠 𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩❞ =================================== በታክስና ኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች ተ....

https://t.me/ethio_consulting_groupአዲሱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/ 2017 ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
24/07/2025

https://t.me/ethio_consulting_group
አዲሱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/ 2017 ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

❝𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 𝐭𝐨 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨-𝐂𝐨𝐧𝐬𝐮𝐥𝐭𝐢𝐧𝐠-𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩❞ በታክስና ኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሌሎች ተጓዳኝ በሆኑ ጉዳዮች የ....

ከፍተኛ የገቢ ግብር መጣል የሚጀምርበት የደመወዝ መጠን ወደ 14 ሺህ ብር ከፍ ሊደረግ ነው ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚሰበሰበው ከፍተኛው 35 በመቶ ታክስ፤ መቆረጥ የሚጀምርበት የደመወዝ እር...
10/07/2025

ከፍተኛ የገቢ ግብር መጣል የሚጀምርበት የደመወዝ መጠን ወደ 14 ሺህ ብር ከፍ ሊደረግ ነው

ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚሰበሰበው ከፍተኛው 35 በመቶ ታክስ፤ መቆረጥ የሚጀምርበት የደመወዝ እርከን ከ10,900 ብር ወደ 14 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ይህ ከፍተኛ ግብር መቆረጥ የሚጀምርበት የደመወዝ እርከን ከዚህ በላይ ከፍ ያልተደረገው "በተለይ በክልል መንግሥታት ገቢ ላይ ከፍተኛ ጫናን ስለሚሳያድር" እንደሆነ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የደመወዝ ገቢ ታክስ ምጣኔ የመጨረሻው ደረጃ የሆነው 35 በመቶ ግብር፤ ከ11 ሺህ ብር ገደማ ጀምሮ መቆረጥ እንዲጀምር የተደረገው በ2008 ዓ.ም. በወጣው የገቢ ግብር አዋጅ ነው። ከዘጠኝ ዓመት በፊት የወጣውን ይህንን አዋጅ የሚያሻሽል ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ባለፈው ሳምንት አርብ ሰኔ 27/2017 ዓ.ም. በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ነው።
ይህ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀው፤ ከግብር እና ቀረጥ የሚገኘው ገቢ ከዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ያለውን ዝቅተኛ ድርሻ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ወደ 11 በመቶ ለማድረስ በፌደራል መንግሥት የተዘጋጀው ስትራቴጂ "አንድ ክፍል" በመሆኑ እንደሆነ በማሻሻያ ማብራሪያ ላይ ተጠቅሷል።

አዋጁ "ሥራ ላይ ከዋለ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ያሳለፈው በመሆኑ ካለንበት የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ከንግዱ ውስብስብ ባህሪ አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች" እንዳሉበት ማብራሪያው ያስረዳል። "ከዲጂታል ኢኮኖሚው ጋር የተጣጣመ ዘመናዊ የታክስ መሠረት" መፍጠርን ዓላማው ያደረገው ረቂቅ አዋጅ፤ "ለታክስ ማጭበርበር በር የሚከፍቱ አሠራሮችን መቀየርንም" ግቡ እንዳደረገ በማብራሪያው ላይ ሰፍሯል።

በረቂቅ ሕጉ ማብራሪያ ላይ በቀዳሚነት የተጠቀሰው "ከመቀጠር፣ ከቤት ኪራይ እና ከግለሰብ ንግድ ሥራ" በሚገኙ ገቢዎች ላይ በሚጣለው ታክስ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ነው። በነባሩ አዋጅ ላይ ያለው "የማስከፈያ መጣኔው እና የገቢ ቅንፉ (income bracket) አሁን ካለው የገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር የሚሄዱ" እንዳልሆኑ ማብራሪያው ያስረዳል። አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት በመቀጠር በሚገኝ ገቢ በተለያየ ደረጃ ከ10 እስከ 35 በመቶ ግብር ይጣልበታል። እስከ 600 ብር ያለው ገቢ ከግብር ነጻ ሲሆን፣ ከ601 እስከ 1,650 ብር ያለው የደመወዝ ገቢ ደግሞ 10 በመቶ ግብር ይቆረጥበታል።
ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ እርከን ስድስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ የመጨረሻው የግብር ምጣኔ 35 በመቶ ነው። ይህ የ35 በመቶ ግብር የሚቆረጠው ከ10,900 ብር በላይ ደመወዝ ከሚያገኙ ሠራተኞች ላይ እንደሆነ በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ላይ ሰፍሯል።
አሁን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ ቀድሞም የነበረው ከ10 እስከ 35 በመቶ የሚደርስ የገቢ ግብር ምጣኔ አስቀጥሏል። ረቂቅ ማሻሻያው ያተኮረው እነዚህ የግብር ምጣኔዎች በሚያርፍባቸው የደመወዝ እርከኖች ላይ መጠነኛ ማስተካከያ ማድረግ ላይ ነው። በዚህም መሠረት ከግብር ነጻ የሚሆነውን በመቀጠር የሚገኝ ዝቅተኛ ደመወዝ ከነበረበት 600 ብር ወደ 2,000 ብር አሳድጓል።
ከፍተኛው የግብር ምጣኔ የሆነው 35 በመቶ የሚጀምርበት የ10,900 ብር ገቢ ላይ ደግሞ የ3,100 ብር ጭማሪ ተደርጓል። ማብራሪያው፤ "ከፍተኛው የማስከፈያ መጣኔ የሆነው 35 በመቶ የሚያርፍበት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ደግሞ ወደ ብር 14,000 ከፍ እንዲል ሆኗል" ሲል የተደረገውን ማሻሻያ ያስረዳል።

ማብራሪያው እንደሚያመለክተው፤ ይህንን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በተካሄደ "የሕዝብ አስተያያት መስጫ መድረክ" ላይ "ከግብር ነጻ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በከፍተኛ መጠን እንዲያድግ" ሀሳብ ቀርቦ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሀሳብ ተቀባይነት እንዳላገኘ ማብራሪያው ይገልጻል። "[ይህ ሀሳብ] በዚህ ምክንያት የሚታጣውን የመንግሥት ገቢ ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና በሌላ ገቢ ሊካካስ በማይችልበት ደረጃ ገቢን የሚቀንስ በመሆኑ ለመቀበል አልተቻለም" ሲልም ምክንያቱን ያስረዳል።
አሁን በሥራ ላይ ያለው የገቢ እና ታክስ ምጣኔ ከነባራዊው "የገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር የሚሄድ" እንዳልሆነ የሚጠቅሰው ማብራሪያው፤ ይሁን እንጂ አሁን በረቂቅ ከተቀመጠው መጠን በላይ ማሻሻያ ማድረግ በመንግሥት ገቢ ላይ ያስከትላል ያለውን ጉዳት ያብራራል። ማብራሪያው፤ "መንግሥት በተለይም የክልል መንግሥታት" ከሚሰበስቡት ገቢ ውስጥ ከደመወዝ ላይ ከሚቆረጥ ግብር "የሚሰበሰበው ትልቅ ድርሻ" እንዳለው ያነሳል። "በመሆኑ መጣኔውን መቀነስ ወይም የገቢ ቅንፉን ማሳደግ በመንግሥት በተለይም በክልል መንግሥታት ገቢ ላይ ከፍተኛ ጫናን እንደሚያሳድር" አመልክቷል።

በዚህም ምክንያት ይህንን በተመለከተ የሚደረግ ማሻሻያ "በጥንቃቄ መታየት አለበት" የሚለው ማብራሪያው፤ ይህ ማሻሻያ የተደረገው ሁለት ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ይጠቅሳል። "በመሆኑም ተቀጣሪው በኑሮ ውድነት ምክንያት ያለበትን ጫና በአንድ በኩል፤ የመንግሥት ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መሸርሸር፣ በመንግሥት አገልግሎቶች ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በሌላ በኩል ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰንጠረዦቹ ላይ ሚዛኑን የጠበቀ ማስተካከያ ተደርጓል" ሲል የተደገውን አነስተኛ ማሻሻያ አመክንዮ ያስረዳል።
ከዚህም በተጨማሪ ከኪራይ እና ከግለሰብ ንግድ በሚገኝ ዓመታዊ ገቢ ላይ ተመሳሳይ ማሻሻያ መደረጉን ማብራሪያው ገልጿል። እነዚህ ማሻሻያዎች "ምክንያት መንግስት የሚያጣው ገቢ ከአገራዊ ጠቅላላ ምርት 0.21 በመቶ" ያህል እንደሚሆን ተጠቅሷል። ማብራሪያው፤ "ከዚህ በላይ ማስተካከያ ይደረግ ቢባል በመንግስት አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ውጤትን የሚያስከትል ይሆናል" ይላል። አሁን በተደረገው ማሻሻያ "ምክንያት የሚታጣውን ገቢ የግብር መሰረትን ለማስፋት በአዋጁ በተወሰዱ ማስተካከያዎች እና የታክስ አስተዳደሩን ውጤታማ በማድረግ ማካካስ እንደሚቻል" እምነት እንደተያዘም ተገልጿል።

በአርብ ዕለቱ ልዩ ስብሰባ ይህ ረቂቅ የቀረበለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ህጉን ለዝርዝር እይታ ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ፓርላማው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም. የስራ ጊዜ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ መታየት የሚጀምረው ምክር ቤቱ በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር ወደ ስራ ሲመለስ እንደሆነ ይጠበቃል።

በታክስ ፣ በኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም ተጓዳኝ ጉዳዮች የምክር አገልግሎት ካስፈለገዎ ይደውሉልን።

ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ONE PERSON PLC) በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ  ህግ የተካተተው የፒ ኤል ሲ አይነትእና ዝርዝር ጉዳዮች1ኛ . ስለ ማህበሩ ባህሪያት ...
08/07/2025

ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ONE PERSON PLC)

በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ የተካተተው የፒ ኤል ሲ አይነት
እና ዝርዝር ጉዳዮች

1ኛ . ስለ ማህበሩ ባህሪያት እና አመሠራረት
••==•••••===•••====•••===••••••==••==•••===••••••==••
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ማለት አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ (Unilateral Declaration) መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማህበር ነው:: ማህበሩ ከአባላት የተለየና የተነጠለ የራሱ የህግ ሰውነት ወይም corporate existence አለው፡፡ ይህን ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልገው አነስተኛ ካፒታል መጠን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ነው፡፡

ይህ የንግድ ማህበር በአገራችን ከተለመዱት የንግድ ማህበራት የተለየ ሲሆን በአዲሱ የንግድ ህግ የተካተተበት ምክንያት አንድ ማህበር (ኩባንያ) ለመመስረት በቂ ካፒታል የያዘ ባለሃብት የግድ ምናባዊ (fictitious) ማህበርተኛ መፈለግ እንዳይገደድ ፤ የተለያየ ካፒታል በመመደብ ለሥራ የሚውለውን ገንዘብ ነጥለው ሥራ መስራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች እድል ማመቻቸት፤ በሌሎች ሃገራት የተለመዱ የንግድ ማህበራት ወደ ሃገራች ማካተት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመሠረተው አባሉ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት በመቅረብ በሚሠጠው መግለጫ መሰረት ነው፡፡ ይህን መግለጫ መመስረቻ ፅሁፍን የተካ ነው፡፡ መግለጫው ማህበሩ ከተለመዱት ዝርዝሮች በተጨማሪ አንድ አባል ብቻ ያለው መሆኑን፣አባሉ የሞተ፣ የጠፋ ወይም በፍርድ የተከለከለ እንደሆነ ስለ ወራሾች ወይም ስለአባሉ ሆኖ ሕጋዊ ተግባራትን እዲፈፅም የታጨው የንብረት ጠባቂ ሰው ስም እና ዕጩ ንብረት ጠባቂው ፍቃደኛ ሆኖ ኃላፊነቱን የተቀበለ መሆኑ ሊያካትት ይገባል፡፡

ዕጩ ንብረት ጠባቂ መሰየም የምስረታ ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ዕጩ ንብረት ጠባቂው ዕጩነቱን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆኑን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ቀርቦ ካላረጋገጠ ማህበሩ ሊመሰረት አይችልም፡፡ አንድ ንብረት ጠባቂ በአንድ ጊዜ ለተለያዩ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሆኑ ማህበራት ንብረት ጠባቂ ሆኖ ሊሾም አይችልም፡፡

አንድ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሌላ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሊያቋቋም አይችልም ይህን ተላላፎ የተቋቋም ማህበር ያገባኛል በሚል ሰው ጠያቂነት ሊፈር እንዲሁም በምስረታው ምክንያት እና በኋላ ለሶስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት አባሉና ማህበሩ በአንድነትና በተናጠል ኃላፊ ይሆናሉ፡፡

አንድ ግለሰብ ነጋዴ (Sole proprietor) ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማህበር መለወጥ የሚችል ሲሆን ግለሰቡ ማህበሩን ከመመስረቱ በፊት ለገባበት ዕዳ ሁሉ ከማህበሩ ጋር በአንድነትና በተናጠል ኃላፊ ይሆናል፡፡
••==•••••===•••====•••===••••••==••==•••===••••••==••
2ኛ. ስለ ማህበሩ ሥራ አመራር እና ኃላፊነት ወሰን
••==•••••===•••====•••===••••••==••==•••===••••••==••
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደ ማንኛውም ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊኖረው ግዴታ ሲሆን ፤ አባሉ ራሱ ወይም ሌላ ሰው የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሊሆን ይችላል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አስኪያጅ በህግ የተሠጠው ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

አባሉ በንግድ ሕጉ ለአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጠቅላላ ጉባዬ የተሠጠው ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ አባሉ በጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣኑ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ቃለጉባዔ ስበሰባው በተደረገ ከሦስት ሣምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በፅሁፍ ተዘጋጅተው የማህበር ማህደሩ ውስጥ ሊቀመጡ እንዲሁም ውሳኔዎቹ የማህበሩን ማቋቋሚያ መግለጫ የሚለውጡ ከሆነ ውሳኔው ከተሠጠበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ይህን ቅድመ ሁኔታ ባይሟላ እንኳን ውሳኔዎቹ በሕግ የሚፀኑ ቢሆንም ጉድለቱ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አባሉና ማህበሩ በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂዎች ናቸው፡፡

ምንም እንኳን የአባሉ ኃላፊነት የተወሰነ (Limited Liability) ቢሆንም አባሉ ወይም በማህበሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር ያለው ሌላ ሰው ማህበሩን፣ ወይም የማህበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ጉዳት ላይ የሚጥል ሕገ ወጥ ድርጊት ሆን ብሎ ከፈፀመ፤ የማህበሩን ንብረትን ከራሱ ንብረት ጋር ከቀላቀለ፤ የማህበሩን እና የራሱን ማንነት ካልነጣጠለ፤ ስለማህበሩ የፋይናንስ አቋም የማህበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ሊያሳስት የሚችል መረጃ ሆን ብሎ ካወጣ፤ ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የማህበሩን ሀብት ለራሱ ወይም ለሦስተኛ ወገኖች የግል ጥቅም ካዋለ፤ በሕግ ሊከፈል ከሚችለው በላይ የትርፍ ክፍያ ከፈፀመ ወይም ተመሳሳይ ተግባራት ከፈፀመ ከማህበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናል ወይም በሌላ አገላለፅ የኩባንያን ጭምብል መግለጥ መርህ ወይም piercing the corporate veil principle ተግባራዊ ይሆናል፡፡
••==•••••===•••====•••===••••••==••==•••===••••••==••
3ኛ. ስለማህበሩ መፍረስ፣
••==•••••===•••====•••===••••••==••==•••===••••••==••
ስለ ማህበራት መፍረስ ከተጠቀሱት ጠቅላላ ድንጋጌዎች በተጨማሪ አባሉ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሂሳቡ ሳይጣራ እንዲፈርስ ከፈለገ ሂሳብ ሳይጣራ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ማህበሩ ሂሳቡ ሳይጣራ የፈረሰ እንደሆነ የማህበሩ ሃብት በጠቅላላው ለአባሉ ይተላለፋል፡፡ በማናቸውም ምክንያት ማህበሩ ከፈረሰ በኋላ ገንዘብ ጠያቂዎች የቀረቡ እንደሆነ አባሉ በግሉ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ማህበሩ ከፈረሰ በኃላ የሚቀርብ ገንዘብ ጠያቂ የሚያቀርበው ጥያቄ ማህበሩ መፍረሱን ካወቀ በአምስት ዓመት ወይም የማህበሩ ሀብት ለአባሉ ከተከፋፈለ በምንም ዓይነት ከአስር ዓመት በኋላ ሊቀርብ አይችልም፡፡

ከላይ በዝርዝር ከተመለከትናቸው ነጥቦች ውጪ ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተደነገጉት ህጎች ለባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም የሚያገለግሉ በመሆኑ ክፍተቶችን ለመሙላት ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

በታክስ ፣ በኦዲት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም ተጓዳኝ ጉዳዮች የምክር አገልግሎት ካስፈለገዎ ይደውሉልን።

05/07/2025

የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 59(3) ላይ የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ የሚገኘው ጥቅም ሀብቱን በማስተላለፍ የተገኘው ዋጋ ሀብቱ በተላለፈበት ጊዜ ከነበረው ዋጋ በልጦ የተገኘው የገንዘብ መጠን አንደሆነ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 (እንደተሻሻለ) አንቀዕ 56(1) ላይ ግብር የሚከፈልበት የካፒታል ሀብት ዋጋ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ የሚደረግበት መሆኑን ያመለክታል፡፡ በዚህ መሠረት ከአክስዮን ማስተላለፍ/ሽያጭ በተገኘ ገቢላይ ቀጥሎ በተመለከተው ቀመር መሠረት ግብር ተሰልቶ መከፈል አለበት፡፡

ሐ = ሀ - ለ
መ = ሐx30%

ለዚህ ቀመር አፈጻጸም፡-
ሀ - አክስዮኑ የተላለፈበት /የተሸጠበት ዋጋ፤
ለ = የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ የታከለበት አክስዮኑ የተገኘበት /የተገዛበት ዋጋ፤
ሐ = ግብር የሚከፈልበት የአክስዮን ሽያጭ ገቢ፤
መ = ከአክስዮን ሽያጭ ከተገኘ ገቢ ላይ የሚከፈል የግብር መጠን ነው፡፡
“ለ” ወይም “የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ የታከለበት አክስዮኑ የተገኘበት /የተገዛበት ዋጋ" የሚሰላው ቀጥሎ በተመለከተው ቀመር መሠረት ነው፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

0911854645

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share