Izz trading ኢዝ ትሬዲንግ አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Izz trading ኢዝ ትሬዲንግ አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ

Izz trading ኢዝ ትሬዲንግ አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ ኢዝ ትሬዲንግ፦አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ
0904-922222. telegra

07/08/2026
04/08/2026

የብሄር ወይስ የእምነት ማንነት ይበልጣል?
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል
📶📶📶📶📶
ዛሬ የማነሳው ሀሳብ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ እጅግ ሲበዛ ወሳኝ ጉዳይ ነው።ስለሆነም እያንዳንዱ ሰው አንብቦ እንዲጨርስ እመኛለሁ።
ያለስሜታዊነት ጉዳዩን በጥልቀት ለመረዳት እንዲረዳኝም እፈልጋለሁ። ለሌሎች እንዲያጋራና በያለበት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እንዲወያይም እጋብዛለሁ።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
የተሰማችሁንም በነጻነት ከስር አስፍሩ። ይህንን ገፅ ፊሎው ያላድጋችሁ አደርጉ። የዩቲዩብ ቻናሌንም ከሥር በአስተያየት መስጫ ላይ ያለውን ሊንክ በመጫን ሰብስክራይብ አድርጉ! መልካም ንባብ።

የእምነት ብዝሃነት እና በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መግቢያ ማንነትን በብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ ድንበር ብቻ ገድቦ በማስፈሩ፣ የዜጎችን መንፈሳዊ እሴትና ሀገራዊ ታሪክ ከባለቤትነት ማዕከል አቀጭጯል።

ቀጥተኛው እንድምታውም የሀገሪቱ መሥራች፣ ባለቤትና ሕገ-መንግሥቱ ባለቤትም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብቻ ናቸው። በዋናነት ሕልውና ያላቸው እንዲሁም በሕገ-መንግሥቱ የተጠቀሱትን የሀገሪቱን ሥልጣን ሳከፋፍል በዋናነት በትኩረት የምመለከተው ብሔር ብሔረሰቦችን ብቻ ነው ማለቱ ነው።

አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለሃይማኖትና ለእምነት ማኅበረሰቦች የሚከተለውን ግልጽ መልዕክት ያስተላልፋል፦

"እንደ ሀገር መሥራችና ባለቤት አላውቃችሁም፤ መብቱ እንደሚጠበቅ አንድ አካል ግን መብታችሁን እጠብቃለሁ። በሀገር ባለቤትነት፣ በአገር መሥራችነትና በሕገ-መንግሥቱ ባለቤትነት እውቅና የምሰጣችሁም እንደ እምነት ተደራጅታችሁ የቆማችሁበትን ትታችሁ ሁላችሁም ወደየብሔራችሁ ሄዳችሁ በብሔራችሁ በኩል ተሰልፋችሁ ስትመጡ እንጂ፣ የራሳችሁ ፍላጎትና ግብ እንዳላችሁ የእምነት ማኅበረሰቦች አይደለም" የሚል ነው።

በሕገ-መንግሥቱ ላይ "እምነትንና ሃይማኖትን በግል መብት ደረጃ አረጋግጣለሁ። ከፈለጋችሁ የጋራ የሃይማኖት አስተዳደር ተቋም ማቋቋም ትችላላችሁ፤ እርሱን የማድረግ መብታችሁን እጠብቃለሁ።"

ከዚህ እይታው የተነሳ ሕገ-መንግሥቱ እንደ ግል አማኝም ሆነ አማኞች የሚያቋቁሙት የሃይማኖትና የእምነት ማኅበረሰብ አልያም ተቋሞች ጉዳይ የሚያነሳው እንደ አንድ ተራ የመብት ጉዳይ ነው።

ይህም ሕገ-መንግሥቱን ማን እንዳቋቋመ፣ ሀገር የማን እንደሆነች እና ሥልጣን ለነማን እንደ ሚከፋፈል፣ ሀገሪቱንም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን እንደ መሠረት (የግንባታ ጡብ፣ አሃድ) አድርገው የገነቡት ሉዓላዊ ፍጹም መብት ያላቸው ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብቻ መሆናቸውን ከመግቢያው እንስቶ የሚገባቸውን ካከፋፈላቸው በኋላ ነው።

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 8 ሥር የሀገሪቱ የሥልጣን ባለቤቶች "ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች" ብቻ እንደሆኑና ሕገ-መንግሥቱም የዚሁ ሉዓላዊነታቸው መግለጫ እንደሆነ ተደንግጓል።

ይህ ድንጋጌ የሥልጣንና የሉዓላዊነትን ምንጭ ሙሉ በሙሉ በብሔር ማንነት ላይ ብቻ በመገደብ ፣ የእምነት ማኅበረሰቦችን ከሕገ-መንግሥታዊ ባለቤትነት ውጪ ያደርጋቸዋል።

በዚህ መዋቅር ምክንያት፣ የእምነት ማኅበረሰቦች በፖለቲካው መድረክ እውቅና የሚያገኙት በብሔር ስብጥራቸው ልክ እንጂ፣ የራሳቸው ሀገራዊ ፍላጎትና ድምፅ እንዳላቸው ማኅበረሰቦች ተቆጥረው የሁሉም እምነትና ሃይማኖት ባለቤቶች በሀገሪቱ የስልጣን ሲከፋፈል በቁጥራችን ልክ ተገቢ ዉክልና ይኑረን አልያም የኛ እምነት ተከታዮች በመንግሥት ዉስጥ ተገቢውን ዉክልና አላገኙም ማለትን መንግሥት በተባለው መዋቅር ዉጪ ስለሆኑ ሃይማኖት በመንግሥት ጣልቃ አይገባም በመንግሥታዊ አሰራር ጣልቃ ገባችሁ የሚል አፍ ማስዘጊያ ነጥብ ይመዘዛል።

ይህም እምነትንና አማኞችን የማምታት አካሄድ ነው። አማኞች አማኝ ስለሆናችሁ ብቻ በሀገራችሁ እኩል የመወከል መብት የላችሁም እንደማለት ነው።

"የብሄር መብት ከእምነት መብት ይበልጣል!"
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

አሁን በሥራ ላይ ባለው የሀገራችን ሕገ-መንግሥት ውስጥ በብሔር ማንነት እና በእምነት ማኅበረሰቦች መካከል ያለው ሕጋዊ የደረጃ ልዩነት ቀደም ብለን ከጠቀስናቸው በተጨማሪ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ ይታያል።

በአንቀጽ 39 ሥር ያሉ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንኳ በፍጹም የማይገደቡ ሆነው ሲደነገጉ፤ በአንቀጽ 27 የተቀመጠው የእምነት ማኅበረሰቦች ነፃነት ግን በአንቀጽ 93(4) መሠረት በአስቸኳይ ጊዜ ሊታገድ ወይም ሊገደብ የሚችል መብት ተደርጎ ተቀምጧል።

ይህም ሕገ-መንግሥቱ ለብሔር ስብስቦች የማይደፈር ፖለቲካዊ ዋስትና ሲሰጥ፣ የእምነት ማኅበረሰቦችን መብት ግን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠ ሕጋዊ ልዩነት መፍጠሩን ያሳያል።

የእምነት ማኅበረሰቦች የአገር መሠረት መሆናቸውን በፍጹም አያረጋግጥም። በመሆኑም የእምነት ማኅበረሰቦችን ብዝሃነት በሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ማስፈር የብሔር ፖለቲካን ጠባብነት የሚያለዝብ፣ ምእመናንን ከጥቃት የሚታደግና እውነተኛ አገራዊ ባለቤትነትን የሚያጸና እርምጃ ነው።

ይህ ማሻሻያ "አገር የማን ናት?" ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ፣ ኢትዮጵያ የብሔር ብቻ ሳትሆን የመላው እምነት ማኅበረሰቦችም የጋራ ሀብትና መኖሪያ መሆኗን በይፋ የሚመልስ አዲስ ሀገራዊ ውል ይፈጥራል።

ይህ ማሻሻያ ለሁሉም ሃይማኖቶች እና ዜጎች የሚያስገኛቸው ዋና ዋና ጥቅሞችና ሀገራዊ ዕድሎች በሚከተሉት ነጥቦች ይብራራሉ፦

ሀ) የሥልጣን፣ የታሪክና የባለቤትነት መሥራችነት ተጽዕኖ
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

1) የ"መጤነት" ወይም "መብቱ የሚጠበቅለት" (ከጠባቂው ባለሀገር ሳይሆን ከሚጠቅለት) የመሆን ስሜትን ያስቀራል፦
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

በአንቀጽ 11 እና 27 ብቻ ሲቀመጥ መንግሥት "መብታችሁን እጠብቃለሁ፣ ጣልቃ አልገባባችሁም" ይላል። ይህ ማለት ግን አገሪቱ ስትቆረቆርና ስትገነባ የእምነታችሁና የመንፈሳዊ እሴታችሁ አስተዋጽኦ አለበት ማለት አይደለም። ዜጎች መንግሥት የሚጠብቃቸው እንጂ የሀገሪቱ ባለቤት እንደሆኑ አይሰማቸውም።

2) ሙሉ አገራዊ ባለቤትነት ይሰጣል፦
📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶
በመግቢያው ላይ "እኛ የብዙ እምነቶች ባለቤቶች የሆንን..." ተብሎ ሲጀምር፣ አገሪቱ ገና ስትመሠረት የሁላችንም እምነት፣ ታሪክና መንፈሳዊ እሴት መሠረት እንደሆነ ያውጃል። የትኛውንም ሃይማኖት "የአገሪቱ ዋና ባለቤት" ሌላውን ደግሞ "መጻተኛ" የማድረግ ጎጂ አስተሳሰብን ያስቀራል።

3) የሁሉም እምነቶች እኩል እውቅና፦
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

የአገሪቱ መሠረት በሁሉም ሃይማኖቶችና እምነቶች እኩል አስተዋጽኦ የተገነባ መሆኑ በመግቢያው ደረጃ ይፋዊ እውቅና ያገኛል።

4) ሕገ-መንግሥታዊ የጋራ ውል ይፈጥራል፦
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
ሁሉም ሃይማኖተኞች ሕገ-መንግሥቱን የእነሱም እምነትና ማንነት ያካተተ እውነተኛ አገራዊ ውል እንደሆነ አምነው እንዲቀበሉት እና የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ለ) ምእመናንን ከብሔር ፖለቲካ ጥቃትና ተጽዕኖ ይታደጋል
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

1) የነባሩ ሕገ-መንግሥት መግቢያ እጥረት፦ ነባሩ መግቢያ "እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች..." ብሎ ብቻ ስለሚጀምር፣ የአገራችን ፖለቲካ በብሔር ላይ ብቻ እንዲጠብ አድርጎታል። በዚህ ምክንያት በየአካባቢው የብሔር ግጭቶች ሲነሱ፣ በብዙ ቦታዎች አብረው የሚጠቁት መስጊዶች፣ ቤተክርስቲያናት እና ምእመናን ናቸው። አንቀጽ 27 እና 11 ይህንን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም።

2) ሀገራዊ ማንነትን ከብሔር ባሻገር ያሰፋል፦
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
በመግቢያው ላይ ሲካተት አገራዊ ማንነታችን በብሔር ብቻ ሳይሆን በሃይማኖትና በልዩ ልዩ እምነቶችም የተገነባ መሆኑን ያውጃል። ይህም ማንነትን ከብሔር ድንበር በላይ በማስፋት፣ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል የሚኖርን ዜጋ በሃይማኖታዊ ማንነቱ ምክንያት ከሚደርስበት የብሔር ፖለቲካ ጥቃትና ተጽዕኖ ሕገ-መንግሥታዊ ከለላ ይሰጠዋል።

ሐ) በአናሳነት ለሚኖሩ ዜጎች ሙሉ ከለላ ይሆንላቸዋል
📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶

1. ተራው እውነታ፦ በአንድ አካባቢ ወይም ክልል የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች በቁጥር አናሳ በሚሆኑበት ጊዜ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ቦታ ከመስጠት፣ መስጊድ ወይም ቤተክርስቲያን ከማሸግ እና በዓላትን ከከልከል ጋር በተያያዘ ተጽዕኖ ያደርጉባቸዋል።

2. ለመታገል ሰፊ ሕጋዊ መብት ይሰጣል፦ አናሳ የሆኑት ምእመናን "እኛም እኮ የዚህች አገር መሥራችና ባለቤቶች ነን" ብለው በአካባቢው ባለሥልጣናት ላይ ጠንካራ ሕገ-መንግሥታዊ መሟገቻ ያገኛሉ።

ፍርድ ቤቶችም ቢሆኑ ጉዳዩን ሲያዩ እንደ አንድ ቀላል የዜጎች አቤቱታ ሳይሆን፣ የአገሪቱን መሠረታዊ እሴት የመጠበቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተረድተው ለምእመናን ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት ይገደዳሉ።

መ) የቅዱሳት ቦታዎች፣ ቅርሶች፣ የጸሎት ቦታዎች
እና የበዓላት አደባባያዊ ጥበቃ ይረጋገጣል
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

1) የነባሩ ሁኔታ ስጋት፦ ታሪካዊ ገዳማት፣ መስጊዶች፣ አድባራት፣ ቅርሶች እና አደባባያዊ በዓላት በየቦታው ከቦታ ወረራ፣ ይዞታ ከልካይነት እና ከፖለቲካዊ ጫና ጋር የተያያዘ ስጋት ይደቀንባቸዋል።

2) የመጨረሻ ጠንካራ መከላከያ ይሆናል፦ እነዚህ ሁሉ የሃይማኖት ሀብቶች፣ ይዞታዎችና በዓላት የአንድ ቡድን ብቻ ሳይሆኑ የመላው አገሪቱ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶች ተደርገው በመግቢያው መንፈስ ስለሚጠበቁ፣ በማንኛውም የመንግሥት አካል የሚደረጉ የቦታ ወረራዎችንና ከልካይነቶችን በሕግ ለማስቆም የሚያስችል መከላከያ ይሆናል።

ሠ) ለፍትህ ሥርዓቱ ቁልፍና መሪ የመተርጎሚያ መመሪያ ይሆናል
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

1) የሕጎችና የውሳኔዎች መመዘኛ መሆኑ፦ መግቢያው የሕገ-መንግሥቱ መንፈስና አቅጣጫ ስለሆነ፣ ማንኛውም በፓርላማ የሚወጣ ሕግ ወይም ደንብ ከሕገ-መንግሥቱ መግቢያ መንፈስ ጋር ከተጋጨ ውድቅ ይሆናል።

2) የዳኞች መሪ መመሪያ፦ ሕገ-መንግሥት ተርጓሚ አካላት እና ፍርድ ቤቶች አሻሚ ሕጎችን ወይም የሕግ ክፍተቶችን ሲተረጉሙ፣ የሃይማኖት ነፃነትን፣ ገለልተኝነትን እና እኩልነትን በሚደግፍ መልኩ እንዲወስኑ ግልጽ መመሪያ ይሰጣቸዋል።

ረ) የመንግሥትን ገለልተኝነት በግልጽ ያጠናክራል
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅

1) ጣልቃ ገብነትን ይገድባል፦ በመግቢያው ላይ የእምነት ብዝሃነትን መደንገግ መንግሥት ለአንድ የተወሰነ ሃይማኖት ወይም እምነት ወገንተኛ እንዳይሆን ያደርጋል።

2) የውስጥ ነፃነትን ያከብራል፦ መንግሥት በማናቸውም የሃይማኖት ተቋማት የውስጥ አስተዳደር ወይም የመንፈሳዊ ውሳኔዎች ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ሕገ-መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ይገድባል።

ሸ) በፖለቲከኞች ፍላጎት የማይቀያየር ዘላቂ ጥበቃ ይሰጣል
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

1) በአንቀጽ 11 እና 27 ብቻ ሲቀመጥ፦ በዋናው ክፍል ያሉ አንቀጾች በፖለቲካዊ ውሳኔዎች፣ በፓርላማ ወይም በሕግ አውጪው ምክር ቤት ድምፅ በቀላሉ ሊሻሻሉ ወይም አፈጻጸማቸው ሊዳከም ይችላል።

2) በመግቢያው ላይ ሲካተት፦ የመግቢያው ይዘት የሀገሪቱ መሠረታዊ ውል በመሆኑ፣ እሱን መለወጥ አገሪቱን እንደ አዲስ እንደ መሥራት ይቆጠራል። በመሆኑም በመግቢያው የተቀመጠ እሴት ከፖለቲካ ተለዋዋጭነት የተጠበቀ፣ ከፖለቲካ ውሳኔ ነፃ የሆነ የማይናወጥ ጥበቃ ያገኛል።

ቀ) ማኅበራዊ፣ ባህላዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጥቅሞችን ያጎለብታል
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

1) የሁሉንም ሃይማኖተኞችንና ኢ-አማኞችን የሕሊና ነፃነት ያከብራል፦ "እምነት" የሚለው አቃፊ ቃል መጠቀሱ የትኛውንም ሃይማኖት የሚከተሉትን እንደሚያስከብር ሁሉ፣ የሕሊና እና የፍልስፍና ነፃነትን በማረጋገጥ የዜጎችን እኩልነት በሙሉ ደረጃ ያረጋግጣል።

2) በሃይማኖቶች መካከል ገንቢ ውይይት ይፈጥራል፦ እያንዳንዱ የእምነት ተቋም ሀገሪቱን የመመሥረት እኩል ባለቤት መሆኑ ሲረጋገጥ፣ በሃይማኖቶች መካከል የሚኖረው ግንኙነት ከስጋት፣ ከበላይነት ስሜትና ከፉክክር ወጥቶ ወደ ሀገራዊ ልማትና ሰላም ግንባታ ይሸጋገራል።

3) የሃይማኖት ጽንፈኝነትንና ጥላቻን በሕግ ያክሽፋል፦ በሃይማኖት ስም የሚደረጉ ጥላቻዎችን፣ የፅንፈኝነት ቅስቀሳዎችን እና ጥቃቶችን ሕገ-መንግሥታዊ ውልን እንደመጣስ ቆጥሮ በሕግ ለመጠየቅ ጠንካራ መሠረት ይጥላል።

4) የጋራ ሀገራዊ ማኅበራዊ እሴቶችን ያጎለብታል ፦ በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ያሉ የጋራ በጎ እሴቶች (እንደ ሰላም፣ ፍቅር፣ መተዛዘን፣ መረዳዳት) ለአገራዊ እድገትና ለስነ-ምግባር ግንባታ እንዲያውሉ ያመቻቻል።

5) ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ይረዳል፦ አገሪቱ የፈረመቻቸውን የዓለም አቀፍ የሕሊና እና የእምነት ነፃነት ድንጋጌዎች በሕገ-መንግሥቷ መግቢያ ላይ በማንጸባረቅ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት የምታከብር ዲሞክራሲያዊት ሀገር መሆኗን እንድታረጋግጥ ይረዳታል።

"ምን እያልኩ ነው?"
🔴🔴🔴🔴🔴🔴

እዚህ ላይ በግልጽ ሊሰመርበት የሚገባው ዋና ነጥብ፣ የኔ ነጥብ እስልምናን፣ ክርስትናን ወይም ሌሎችንም እምነቶች የመንግሥት ሃይማኖት ማድረግ ወይም በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ እንደ ብሄሩ ሁሉ በሃይማኖት ፓርቲ ይደራጅ ወይም ፖለቲካው በሃይማኖት ይሁን እያልኩ አይደለም። ወይም መንግስታዊ ሃይማኖት አልያም ሃይማኖታዉ መንግሥት ይኑረንም እያልኩ አይደለም።


እያልኩ ያለሁት እንደ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣ ሙስሊም ማኅበረሰብ እና ሌሎችም የእምነት ማኅበረሰቦች በኢትዮጵያ ሀገራዊ ባለቤትበት፣ ሀገራዊ ግንባታ ውስጥ ያላቸውን ድርሻና ታሪካዊ ባለቤትነት ሕገ-መንግሥታዊ እውቅና እንዲያገኝ ነው።

ይህ እውቅናስ በተግባር የሚገለጸው እንዴት ነው?
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

1) በሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ የጋራ ባለቤትነት ሲረጋገጥ፦ ሀገሪቱ ስትመሠረት እና ስትገነባ የብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆን የበርካታ እምነቶች መንፈሳዊ እሴትና ታሪክ መሠረት መሆኑ በይፋ ሲታወቅ ነው።

2) የታሪክና የሞራል ባለቤትነት እውቅና ሲሰጥ፦ የእምነት ማኅበረሰቦች የሀገሪቱ የሞራል፣ የሰላም እና የአብሮነት ምሰሶዎች መሆናቸው በሕግና በፖሊሲ ደረጃ ሲከበር ነው።

3) ተቋማዊ ጥበቃ እና ፍትሃዊ ዋስትና ሲኖር፦ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የእምነት ማኅበረሰቦች፣ የጸሎት ቦታዎች፣ ቅርሶችና በዓላት እንደ አንድ የጋራ ሀገራዊ ሀብት ተቆጥረው ጠንካራ ሕገ-መንግሥታዊ ከለላ ሲያገኙ ነው።

4) ፍትሃዊ የሥልጣን ውክልና ሲረጋገጥ፦ ፖለቲካው በዜጋም ይሁን በብሄር ብሄረሰብ በዉጤት ደረጃ በሁሉም የእምነት ማኅበረሰቦች መካከል ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል በተግባር እውን ሲሆን ነው።

5) እኩል የሀብት እና የኢኮኖሚ ክፍፍል ሲደረግ፦ የሀገሪቱ ሀብትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለሁሉም የእምነት ማኅበረሰቦች በእኩልነት ሲዳረስ ነው።

6) ሁለንተናዊ እኩል ውክልና ሲሰጥ፦ በሀገሪቱ ማናቸውም አጠቃላይ ጉዳዮችና መዋቅሮች ውስጥ የእምነት ማኅበረሰቦች እኩል ተሳትፎና ውክልና ሲረጋገጥ ነው።

ይህ አካሄድ መንግሥት “ሁሉም እምነቶች በእኔ ዘንድ እኩል ናቸው” ከሚል ባዶ የቃል ንግግር ባለፈ፤ በሚያወጣቸው አዋጆች ፣ፖሊሲዎች፣ እና ደንቦች፣ እንዲሁም ሹመቶችና የፓርላማ ተመራጭ እጩዎች፣ወዘተ ሁሉ በብሔር ማንነት ብቻ ከሚደረግ የእኩልነት እና አሳታፊነት በተጨማሪ በእምነት ማኅበረሰቦች መካከልም ፍትሃዊነት መስፈኑን ለመፈተሽ ይገደዳል። ይህ ደግሞ በመንግሥት ላይ እውነተኛ ኃላፊነትን የሚጥልና፣ ሃይማኖቶች በቃላት ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ሕጋዊ ግዴታ በእኩልነት እንዲስተናገዱ የሚያስገድድ ጠንካራ መሠረት ይፈጥራል።

ቸር እንሰንብት!

⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

የአሕመዲን ጀበል የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ! ሊንኩ ከሥር በአስተያየት መስጫው ስር ተጠቅሷል።👇
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

03/08/2026

ተራራውን ዙሪያውን እንጠብቀዋለን እንጂ አንገፋውም ። ኡስታዝ አህመዲን ለማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈውን መልዕክት ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ መስጠት ለአሚሮቻችን ለውዶቻችን የመታዘዛችን መለኪያ ነው። በጀማል በሺር ላይ ተቃውሟችንን በፍጥነት እንዳደረግነው ሁሉ የለቀቅናቸውን ቪዲዮ አና ፅሁፍ ከፖስታችን ላይ በፍጥነት በማንሳት ለኡስታዛችን ጥሪ ያለንን ክብር እንድናረጋግጥ ለሙስሊም አክቲቪስት ጀግኖች ሁሉ እኔም ጥሪ አቀርባለሁ።

01/08/2026

በዚህ ቪዲዮ (In this video):—📚 የዚህ ፕሮግራም ሙሉ ክፍሎች (Full Playlist):[...

01/08/2026

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Izz trading ኢዝ ትሬዲንግ አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Izz trading ኢዝ ትሬዲንግ አረቢያን መጅሊስ ምንጣፍ መጋረጃ:

Shortcuts

Share