Dynamic General Business Group

Dynamic General Business Group Dynamic General Business Group General Business Agent

Dynamic Logistics Supply and support services
11/02/2022

Dynamic Logistics Supply and support services

11/02/2022
30/10/2020

[ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጥቅምት 21 ሰማያዊ ጨረቃና 4 ፕላኔት]
✍️ በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
💥 ሰማይን መመርመር ለምትፈልጉ ጥቅምት 21 ቅዳሜ ማታ ምርጥ ምሽታችሁ ይሆናል፡፡ ሙሉዋ ጨረቃ ቀይዋ ፕላኔት ማርስን ከጐንዋ አድርጋ በምሥራቅ በምሽት ሰዓት ላይ ብቅ ትላለች፡፡ በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ታላቁ ፕላኔት ጁፒተርና ቀለበታማዋ ፕላኔት ሳተርን ጐንና ጐን ሆነው ደምቀው ይታያሉ፡፡

💥 በባሕር ማዶ ሥነ ፈለክ የጥቅምት 21 የቅዳሜዋ ሙሉ ጨረቃ Blue Moon (ሰማያዊ ጨረቃ) በመባል ትታወቃለች፡፡ ለጨረቃ ሥያሜ መስጠት በሁሉም የተለመደ ነው፤ ጨረቃችን የሁሉም ለሁሉም ነችና፡፡ ስለዚህ ሁሉም እንደ ትውፊታቸው ይገልጽዋታል፡፡

💥 ለምሳሌ በኢትዮጵያ የሥነ ፈለክ ብራና መጻሕፍት ላይ የጨረቃ 8 ሥያሜዎችን ስንመለከት፦
1. ጨረቃ
2. ወርኅ
3. ቀመር
4. አሶንያ
5. ብናሴ
6. ኤራእ
7. ዕብላ
8. ሶልያና ተብላለች፡፡

💥 በሌላ ሀገራት ያሉ ሰዎች የጥቅምት 21 ሙሉ ጨረቃ Full Moon “ሰማያዊ ጨረቃ” ማለታቸው ጨረቃ ሰማያዊ ትሆናለች ማለት አይደለም፡፡ እንደ ጎርጎርዮሳዊው የወራት አቆጣጠር በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ስለሚሆን ነው፡፡ ይኸውም ኦክቶበር 1 ላይ የመጀመሪያዋን ሙሉ ጨረቃ በመቀጠል ኦክቶበር 31 ላይ ደግሞ ሌላኛዋን ሙሉ ጨረቃ ሲያዩ ይህን ስያሜ ይሰጣሉ፡፡

💥 ጨረቃ ጠፍ ሆና ተወልዳ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወይም በዐሥራ አራተኛው ቀን ጨረቃ ከፀሐይ በተቃራኒ በኩል ትሆንና የፀሐይ ብርሃን ሙሉ ለሙሉ ያርፍባታል፡፡ ይህም ደረጃ ሙሉ ጨረቃ (full moon) ይባላል፡፡ በዚህ የሙሉ ሰሌዳ ወቅት መሬት መሓከል ስትሆን ጨረቃና ፀሐይ በተቃራኒ ስለሚሆኑ ልክ ፀሐይ እንደጠለቀች ጨረቃ ሙሉ ሆና በምሥራቅ ትወጣለች፡፡ ልክ ፀሐይ እንደወጣች ደግሞ ጨረቃ በምዕራብ በኩል ትጠልቃለች ማለት ነው፡፡

💥 ጥቅምት 21 ላይ ቀኗን ጠብቃ ሙሉ ጨረቃ የምትሆነው በየ19 ዓመት ነው፤ በየ19 ዓመቱ ሙሉ ጨረቃ በተመሳሳይ ቀን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም የሜቶኒክ ዑደት (ዐውደ አበቅቴ) ይባላል፡፡ ከጌታ ልደት በፊት 432 ላይ የግሪኩ ሜቶን ከ19 ዓመት በኋላ ጨረቃ ልኬቷን ትደግማለች ይላል፡፡ ነገር ግን ትንሽ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ከጨረቃ ምሕዋራዊ ጊዜ ጋርና ሠግር ጊዜያት ጋር በተያያዘ የቀናት ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡

💥 ይህ የ19 ዓመት ዑደት በጎርጎርዮሳዊ የዘመን ቀመር ከዚህ በኋላ በ2039፤ በ2058፤ በ2077፤ በ2096 ላይ ነው፡፡ እንግዲህ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ1925 እና በ1944 ላይ ጥቅምት 21 ላይ ሠርቷል፡፡ በርግጥ በየ19 ዓመት የሚከሰት ክስተት ነው። እንደ ጀሩሳሌም ፓስት ዘገባ ከሆነ ግን የሰማያዊ ጨረቃ በሁሉም የሰዓት ዞኖች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሲከሰት ያሁኑ ነው ይላል፡፡ በ1944 ላይ 2ተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ነበር፤ ይህስ ምን ሊያመጣ ይችላል? አልታወቀም፡፡ የጀሩሳሌም ፓስት ዘገባን ያንቡ
https://www.jpost.com/health-science/2020-features-a-blue-moon-on-halloween-in-multiple-time-zones-644425

💥 ጀሩሳሌም ፓስት በመቀጠል ከዚያ ሙሉ ጨረቃ ከጥቅምት 21 (ኦክቶበር 31) ወደ ጥቅምት 22 (ኖቬምበር ፈርስት) ሄዶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ (በ1963, 1982, እና 2001) በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ አሁን ግን ጥቅምት 21/ 2013 ወይም ኦክቶበር 31/ 2020 ላይ በሁሉም ዓለም ያሉ የጥቅምት 21 ሙሉ ጨረቃን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ይመለከታል ይላል ዘገባው፡፡

💥 ሌላው ጥቅምት 21 ቅዳሜ ፕላኔት ኡራኑስ ወደ መሬት ቀረብ የምትልበት ሲሆን በ1.75 ቢሊየን ማይልስ ርቀት፤ 2.81 ቢሊየን ኪ.ሜ. ትቀርባለች፡፡ በፀሓይ መላ ገጽዋ ብሩህ ይሆናል፤ ኡራኑስን በቴሌስኮፕ ለማየት ምርጡ ቀን ነው፡፡ በርቀቷ ምክንያት ትንሽ ሰማያዊ-አረንጓዴ መስላ ሞስት ፓወርፉል በሆነ ቴሌስኮፕ ጎልታ በርታ ትታያለችና ተደሰቱባት፡፡

💥 በመሆኑም ቅዳሜ ማታ ላይ በመላው ዓለም ያላችሁ ደመና ከሌለ ሙሉ ጨረቃን ፎቶ እያነሣችሁ በአስተያየት መስጫው ላይ አካፍሉን፡፡

💥 ከ3000 ዓመት በኋላ በቅርቡ በሰማይ ስለሚከናወን ዓለምን ወደ ሌላ መስመር ስለሚለውጣት እጅግ አስገራሚ ክስተት በ You Tube
https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
ላይ አቀርብላችኋለሁ፡፡

💥 በተጨማሪም አንድሮሜዳ በቅርቡ ወደ ቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ማለቷ አይቀርምና የድንቁርና ጠላት የሆነው የእውቀት ሻሻቴ ይፈሳልና ስለሁኔታው ወደ ፊት እገልጽላችኋለሁ፡፡

[እውቀት፣ እውነት፣ እምነት፣ አመክንዮ ሰውን በትክክል አቅጣጫ ይመራሉና ከድንቁርና ጋር መቼም አንተባበርም፡፡]
💥 መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

Address

Kality
Addis Ababa

Telephone

+251929930740

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dynamic General Business Group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dynamic General Business Group:

Share