Beautiful Ethiopian Women Detect languageየ ኢትዮጵያ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Beautiful Ethiopian Women Detect languageየ ኢትዮጵያ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች

Beautiful Ethiopian Women Detect languageየ ኢትዮጵያ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች

የተሰበረው ማሰሮ እና ወንዙ አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ አባባ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ የድሮ የሸክላ ማሰሮ ውስጥ ውሃ ሊቀዳ ሲል፣ ማሰሮው ከታች በኩል በትንሹ ተሰንጥቆ ውሃ ያንጠባጥብ ነበር። እኔም...
28/05/2026

የተሰበረው ማሰሮ እና ወንዙ
አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ አባባ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ የድሮ የሸክላ ማሰሮ ውስጥ ውሃ ሊቀዳ ሲል፣ ማሰሮው ከታች በኩል በትንሹ ተሰንጥቆ ውሃ ያንጠባጥብ ነበር። እኔም ይሄን አይቼ፡-
​"አባባ፣ ይሄ ማሰሮ እኮ ተሰንጥቋል፤ ውሃ አይዝልህም። ዝም ብለህ ለምን ትደክማለህ? ጣለውና አዲስ እንግዛ" አልኩት።
​አባባ ቀና ብሎ አየኝና፣ "አይ ልጄ፣ መቼም ቢሆን የተሰበረ ወይም የጎደለ ነገርን ወዲያውኑ አትናቀው፤ የራሱ የሆነ ጥቅም አለው" አለኝ።
​እኔም እየሳቅኩ "የተሰበረ ማሰሮ ምን ጥቅም አለው አባባ?" አልኩት።
​አባባም "ና እስኪ አብረን ውሃ እንቅዳ" አለኝና ወደ ወንዙ ሄድን። ማሰሮውን ሞልተን ወደ ቤት በምንመለስበት መንገድ ላይ፣ አባባ መንገዱን እንድመለከት ነገረኝ።
​በመንገዱ በአንድ በኩል (ሙሉው ማሰሮ በነበረበት ወገን) መሬቱ ደረቅና ምንም የሌለበት ነበር። በተሰበረውና ውሃ በሚያንጠባጥበው ማሰሮ በኩል ግን መንገዱ በሙሉ በሚያማምሩ አበቦችና አረንጓዴ ሳሮች አጊጧል።
​አባባ ቆመና ወደ አበቦቹ እያመለከተ እንዲህ አለኝ፦

​"አየህ ልጄ? ይህ ማሰሮ የተሰበረ መሆኑን አውቃለሁ። ነገር ግን በየቀኑ ከወንዝ ስንመለስ እሱ ያንጠበጠበው ውሃ ነው ይህንን ደረቅ መንገድ ወደ ውብ የአትክልት ስፍራ የቀየረው። ሙሉው ማሰሮ ራሱን ብቻ ነው የጠቀመው፤ የተሰበረው ግን መንገዱን በሙሉ አሳመረው።

​በዚህ ምድር ላይ ፍፁም የሆነ ሰው የለም። ሁላችንም የየራሳችን 'ስብራት'፣ ድክመትና ጉድለት አለብን። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የሌሎችን ስብራት ብቻ እያዩ ያገላሉ፣ ይንቃሉ። ፈጣሪ ግን በእኛ ስብራት ውስጥ እንኳን ሌሎችን የሚጠቅም ትልቅ በረከት ያስቀምጣል።"
​ትክክል መሆኑ ገባኝና ዝም አልኩ። አባባም ማሰሮውን መሬት ላይ አስቀምጦ የመጨረሻውን ምክር ሰጠኝ፦
​"ልጄ! ሰዎችን በጉድለታቸው አትመዝናቸው። የአንተንም ስብራት አይተህ ተስፋ አትቁረጥ። ዋናው ነገር ባለን ጉድለት ውስጥ እንኳን ለዓለም የምናበረክተው መልካም ነገር መኖሩ ነው። ፍፁም ለመሆን አትልፋ፣ ጠቃሚ ለመሆን ግን ትጋ።"
​ብሎኝ ማሰሮውን ይዞ ወደ ቤት ገባ።
​ይህ ታሪክ ደግሞ የሰዎችንም ሆነ የራሳችንን ድክመትና ስብራት በተለየ ዐይን እንድንመለከት ያስተምረናል።

ያልተከፈለው እዳ​አንድ ቀን አመሻሽ ላይ አባባ ከቤት ውጭ ተቀምጦ ሳለ፣ በአካባቢያችን የሚኖር አንድ በጣም ሀብታም እና ተሰሚነት ያለው ሰው በድንገት በሞት ማረፉን የሚናገር የለቅሶ አዋጅ በ...
28/05/2026

ያልተከፈለው እዳ

​አንድ ቀን አመሻሽ ላይ አባባ ከቤት ውጭ ተቀምጦ ሳለ፣ በአካባቢያችን የሚኖር አንድ በጣም ሀብታም እና ተሰሚነት ያለው ሰው በድንገት በሞት ማረፉን የሚናገር የለቅሶ አዋጅ በሜጋፎን ተሰማ። የሟቹን ስም ስሰማ ደነገጥኩና ወደ አባባ ዞሬ፡-
​"አባባ፣ እገሌ እኮ ሞተ! በጣም ትልቅ ሰው ነበር... እግዚአብሔር ይማረው" አልኩት።
​አባባ ግን ብዙም ሳይደነግጥ፣ አይኖቹን ወደ መሬት ሰቅስቆ "አዎ፣ ትልቅ ሰው ነበር። ግን ያልከፈለው ትልቅ እዳ ነበረበት" አለኝ።
​እኔም ግራ በመጋባት "እዳ? አባባ እሱ እኮ ሚሊየነር ነው! የትኛውን ፎቅ፣ የትኛውን መኪና አላየህም? እሱ ለማን እዳ ይኖረዋል?" አልኩት።
​አባባ በቀስታ ፈገግ አለና ወደ እኔ ተጠግቶ እንዲህ አለኝ፦

​"ልጄ፣ ሰዎች እዳ ሲባል የሚታያቸው ብርና ቁስ ብቻ ነው። እሱ ግን የራሱን ህይወት ሳይኖር፣ ለሌሎች ሰዎች እይታ ሲል የኖረው ህይወት እዳ ነበረበት።

​ያንን ሁሉ ፎቅ የሰራው እሱ ፈልጎት ሳይሆን፣ ሰዎች 'ሀብታም ነው' እንዲሉት ነበር። ያንን ሁሉ ውድ መኪና የሚነዳው ተመችቶት ሳይሆን፣ ሰዎች 'የተሳካለት ሰው ነው' ብለው እንዲያደንቁት ነበር። ሁልጊዜ ሰዎችን ለማስደሰትና የሰዎችን ምስጋና ለመግዛት ሲሮጥ፣ ራሱን ረሳው።
​ዛሬ በድንገት ሲሞት ያ አጨብጫቢ ሁሉ 'ነፍስ ይማር' ብሎ ወደየቤቱ ይበተናል። እሱ ግን ለሰዎች አስተያየት የከፈለውን እድሜና የራሱን እውነተኛ ደስታ መልሶ ማግኘት አይችልም። ይህንን እዳ ሳይከፍል (ራሱን ሳይሆን) አለፈ።"
​በአባባ ንግግር ደንግጬ ዝም አልኩ። አባባም ትከሻዬን መታ አድርጎ የመጨረሻዋን የወርቅ ምክር ሰጠኝ፦
​"አየህ ልጄ፣ በዚህ ምድር ላይ ስትኖር ለሰዎች እይታ ብለህ የምትከፍለው ዋጋ ሁልጊዜ 'ኪሳራ' ነው። ሰዎች ዛሬ ያወድሱሃል፣ ነገ ይረሱሃል። ለማንም ሳትኖር፣ ለፈጣሪህና ለራስህ እውነተኛ ማንነት ኑር። የሰዎች አድናቆት ጊዜያዊ ጣፋጭ መርዝ ነው፤ ራስህን መሆን ግን ዘላለማዊ ሰላም ነው።"
​ብሎኝ፣ የለመደባትን ጸሎቱን ለማድረስ ወደ ውስጥ ገባ።
​ይህ ታሪክም እንደ መጀመሪያው ታሪክ ሁሉ፣ እኛነታችንን በሰዎች ሚዛን ላይ ሳናስቀምጥ፣ በራሳችን እውነተኛ ማንነት መኖር እንዳለብን በጥልቀት ያስገነዝበናል
ከተመቻቹ #ሌላ በለህ ጻፍልኝ

 #ጤዛው ፍቅሬ #ክፍል 4ጢርርር ... ጢርርርር..." ጥሪዉ (ደዋዩ) ማን እንደሆነ ለማየት ስልኩን ከሱሪዉ ኪስ አወጣና አየ፡፡ "Hamza" ይላል፡፡ ስልኩን ሳያነሳዉ ድምፁን ቀነሰና ጥሪዉ...
28/05/2026

#ጤዛው ፍቅሬ
#ክፍል 4
ጢርርር ... ጢርርርር..." ጥሪዉ (ደዋዩ) ማን እንደሆነ ለማየት ስልኩን ከሱሪዉ ኪስ አወጣና አየ፡፡ "Hamza" ይላል፡፡ ስልኩን ሳያነሳዉ ድምፁን ቀነሰና ጥሪዉን ድምፅ አልባ አደረገዉ፡፡ ንዴቱ ዉስጡን እያላወሰ ነበርና አይኑን ማጉረጥረጡን ቀጠለ፡፡....."ማን ነዉ የደወለዉ?" አላት፡፡ እጆቹን ጨብጦ ለቡጢ እያዘጋጃቸዉ፤ ሁኔታዉ ከሚስቱ ፊት ሳይሆን ከደመኛዉ ሊበቀለዉ ከሚፈልገዉ ሰዉ ፊት የቆመ ይመስላል፡፡ ፎዚያ ፈራችዉ፡፡ በዚህ ንዴቱ መምታት ከጀመራት እንደማያቆም ታዉቋት ትርበተበት ገባች፡፡ ወደ'ሷ ጠጋ እያላት ጥያቄዉን ደገመዉ፡፡ .."ማን ነዉ የደወለዉ?... እ...?..." ፡፡ ምን ብላ ትመልስ?፡፡ ተደዉሎላት ሳይሆን ደዉላ ነዉ፡፡ 'ሀምዛ ነዉ ብለዉስ?.. ከ'ሱ ጋር ይጠረጥረኝ ይሆን?... የሚዋደዱ ጓደኛሞች በ'ኔ ምክንያት ቢጣሉስ?" እያለች ዉስጧን በስጋት ሞላችዉ፡፡ በዚሁ መካከል ሀምዛ ቅድም ደዉሎ ስላልተነሳለት በድጋሚ ለሀቢብ ደወለ ... "ጢርርርር... ጢርርርር...." የፎዚን ንዴት ስልኩ ላይ ሊወጣዉ ይመስል እጆቹን በሃይል ወደ ኪሱ ልኮ ስልኩን አወጣና አረንጓዴዉን ተጭኖ..." ሄሎ ..." አለ፡፡.."ሄሎ ... ሃቢብ ብደዉልልህኮ አታነሳም" የሀምዛ ድምፅ ነበር፡፡ ከመበሳጨቱ የተነሳ ያሁኑ ደዋይ ማን እንደሆነ አላወቀዉም ነበር፡፡.."እ... አንተ ነህ እንዴ ሃምዛ...".."ስልክ ቁጥሬ ቢጠፋህ መቼም ድምፄ አይጠፋህም!" እሱ ራሱ ሃምዛ መሆኑን እያረጋገጠለት ነበር፡፡.."እ...ለማንሳት አልተመቸኝም ነበር" አለዉ፡፡.."ከፎዚ ጋር በምን ተጋጭታችሁ ነዉ?".."ማን ነገረህ?" ብሎ በቤቱ ዉስጥ አንገቱን አዟዙሮ ተመለከተ፡፡ 'ይሄ ሰዉዬ ተደብቆ እያየኝ ነዉ እንዴ?' ብሎ አሰበ፡፡
መጥፎ የሚሰራ ሰዉ እንኳን ሌላ ሰዉ ራሱንም ይጠራጠራል፡፡ ስራዉ እንደ ቂል አደረገዉ፡፡.."ፎዚ አሁን ደዉላልኝ ነበር፡፡"
ስልኩን ከጆሮዉ ስር 'ራቅ እያደረገ ወደ ኃላ እንደማፈግፈግ ብሎ ፎዚን በቆመችበት ትቷት ወደ መኝታ ክፍሉ ተመለሰ፡፡ .."እና... ምን አባቷ ወደ አንተ አስደወላት..." አለዉ፡፡ የተጠራጠረ ይመስላል፡፡ 'ግንኙነት አላቸዉ ማለት ነዉ' ሲል አሰበ፡፡ 'በዚህ አይነትማ እስከዛሬ የምነግረዉን ለሷ ይነግራት ነበር ማለት ነዉ!' ... 'ቆይ ግን... ምንድን ነዉ ግንኙነታቸዉ?'፡፡ ሀምዛ ማሜን እየመከረዉ ነዉ፡፡ 'አትጣሉ...' እያለ የጓደኝነቱን ይነግረዋል፡፡ ሀቢብ ግን አልሰማዉም፡፡ እንደዉም ይባስ ብሎ ሀምዛን ከፎዚ ጋር መጠርጠር ይዟል፡፡ ካፉ አላወጣዉም እንጂ 'እሰራለሃላችኃለሁ' እያለ ከንፈሩን በቁጭት ይነክሳል፡፡.."እሺ በቃ አንጣላም ... ስንገናኝ እናወራለን!" ብሎት ስልኩ ተዘጋ፡፡ ሀቢብ ፎዚን ጠልቷታል እንዳይባል ይቀናባታል፤ ይወዳታል እንዳይባል ደግሞ ያሰቃያታል፡፡ ነገረ ስራዉ ሁሉ 'እሱ እንዲህ ነዉ!' ብሎ ለመወሰን ይከብዳል፡፡
... ፎዚያ እራሷን ማስጨነቁን ተያያዘችዉ ..'ቆይ ሀቢብ ሊጠላኝ የቻለበት ምክንያት ምን ይሆን?' ብላ እርግጠኛ ሁና መመለስ በማትችለዉ ጥያቄ ራሷን ታፋጣለች፡፡ 'ያ የበፊቱ ፍቅርስ የት ገባ?' ...'ሶፊ ስለ ሀቢብ ጥሩነት እንጂ አንድም ቀን መጥፎነቱን አዉርታኝ አታዉቅም ነበር፡፡ ፍቅር መስጠት እንደሚችል እንጂ ልቡ በጥላቻ የጠቆረ መሆኑን አልነገረችኝም ነበር፡፡' ነበር...
ነበር ...
ነበር... እያለች እራሷን ወደ ኃላ እየጎተተች ሀቢብን የተዋወቀችበትን የምርቃን ጊዜዋን አማረረች፡፡ ያን በደስታ የተፍነከነከችበ

 #ጤዛው ፍቅሬ #ክፍል 3...ፎዚ 'አሁን ደግሞ ምን አጠፋሁ?' ብላ የሀቢብ ሁኔታ አስጨነቃት፡፡ ከእለት ወደ እለት ለሷ ያለዉ ጥላቻ እየጨመረ መሄዱ ሃሳብ ገባት፡፡ እንዲህ አምራና ተዉባ ስ...
28/05/2026

#ጤዛው ፍቅሬ
#ክፍል 3...ፎዚ 'አሁን ደግሞ ምን አጠፋሁ?' ብላ የሀቢብ ሁኔታ አስጨነቃት፡፡ ከእለት ወደ እለት ለሷ ያለዉ ጥላቻ እየጨመረ መሄዱ ሃሳብ ገባት፡፡ እንዲህ አምራና ተዉባ ስጠብቀዉ 'የኔ ቆንጆ ዛሬ ደግሞ ይበልጥ አምሮብሻል' እንዲላት ነበር የፈለገችዉ፡፡ እሱ ግን ማሞገስ፤ ዉበት ማድነቅ የሚባለዉ ሃሳብ ሊመጣለት ቀርቶ እሷን መሸሽና እንደ ቆሻሻ ይርቃታል፤ ይፀየፋታል፡፡
ለዚህ ነገር መፍትሄ ማበጀት እንዳለባት አምና የሀቢብን የልብ ጓደኛ ሀምዛን ማማከር እንዳለባት ወሰነች፡፡ ምክንያቱም ሀቢብን ወደ ቀድሞዉ ፍቅሩ መመለስ ካልቻለች ትዳራቸዉ ገደል ስር እንደበቀለ ዛፍ በጊዜ ቆይታ ብዛት ተመንጉሎ እንደሚወድቅ ታዉቋታል፡፡
በፀብ የጠነከረ ትዳር፤ በንትርክ የተገነባ ፍቅር፤ በመቃቃር የተዋቀረ መዋደድ እንደሌለ ታዉቃለችና፡.. ሀምዛ የሀቢብ የልብ ጓደኛዉ ነዉ፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች (ሀቢብና ሀምዛ) መካከል ሚስጥር የሚባል ነገር የለም፡፡ እናም የሀቢብን የባህሪ መቀየር ሀምዛ ሊያዉቀዉ ይችላል በሚል ስልኳን አነሳችና የሃምዛን ቁጥር ጽፋ ደወለች፡፡ ስልኩ እየጠራ ነዉ፡፡ ሀምዛ ስልኩን አነሳና የፎዚ ጥሪ እንደሆነ በቁጥሩ ስላወቀ....." ሄሎ ፎዚ..." አላት፡፡.."አሰላሙዓለይኩም ሀምዛ... እንዴት ነህ?" ድምፅዋ ለቅሶዋን አቋርጣ የደወለች ሀዘንተኛ አስመስሏታል፡፡.."ወአለይኩም ሰላም ፎዚ ...ምን ሁነሻል?" ብሎ ጠየቃት፡፡
ልትደብቅዉ ያልቻለችዉ የዉስጥ ሀዘን እንዳለባት ያስታዉቅባታል፡፡ ፎዚም እየሆነች ያለችዉንና የሀቢብን የባህሪ መቀየር ለመንገር ስለደወለች ልትደብቀዉ ወይም በዝምታ ልታልፈዉ አልፈለገችም፡፡ ለሃምዛ ከመንገሯ በፊት ግን ዉስጧ ያለዉን ስሜቷን ትንፋሿ ቀድመዉ ነገሩት፡፡
"እህህህህ..." አለች፡፡ ሳታስበዉ ነበር በረጅሙ የተነፈሰችዉ፡፡ .."ምነዉ ፎዚ?... ከሀቢብ ጋር ተጣላችሁ እንዴ?" ብሎ ከምትቀዝፈዉ የሀሳብ ባህር ዉስጥ አናጠባት፡፡.."ሀምዛ... (ብላ ጠራችዉና ለማዳመጥ ዝግጁ እንደሆነ ስታዉቅ ተንፈስ ብላ ንግግሯን ቀጠለች... ).. ከሀቢብ ጋር እንደምንጣላ ታዉቃለህ እንዴ?" ብላ ጠየቀችዉ፡፡ ሀምዛ ያላሰበዉን ጥያቄ ስትጠይቀዉ ደንገጥ አለና....." ፎዚ ... ሀቢብ ጓደኛዬ እንደሆነ ታዉቂ የለ? ሁሌም ቤቱ ዉስጥ ስለተፈጠረዉ ነገር አይደብቀኝም" አላት፡፡.." ለምን ተገናኝተን አናወራም?" ብላ የትዳሯን አሳሳቢነትና አስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ ልትነግረዉ ፈለገች፡፡ በዚሁ ቅፅበት ግን ሀቢብ ሌላዉን ሁሉ የስልክ ንግግር ሳይሰማ "ለምን ተገናኝተን አናወራም?" የምትለዋን ቃል ሰይጣን ለጆሮዉ አቀበለዉ፡፡ ..."ምን? ... ከማን ጋር ነዉ የምትገናኘዉ?" ብሎ ጋደም ካለበት አልጋ ዘሎ ተነሳና ፎዚያ ወዳለችበት ክፍል ተጣደፈ፡፡ ልክ እሷ ጋር እንደደረሰ ከሀምዛ ጋር የሚገናኙበትን ቦታና ሰአት ተነጋግረዉ ስልኩን እየዘጋችዉ ነበር፡፡ እሷ ጋር እንደደረሰ አይኖቹ ሊወጡ ምንም አልቀራቸዉም፡፡ አፈጠጠባት፡፡ ፎዚ ፈራችዉ፡፡ ምን ትበለዉ? ምታወራዉ አጣች፡፡ ፊቷ የቆመዉ የምትወደዉና ዛሬ ቢቀየርም ድሮ የሚወዳት ባልሽ አልመስልሽ አላት፡፡ እሷን ለመደብደብ፤ ህይወቷን ለማበሳቆል፤ ትዳሯን ለማተራመስ፤ ኑሮዋን ለማዘባረቅ የተላከ 'ሰይጣን' ተመሰለባት፡፡ ሀቢብም ንዴቱ ምንም ሊያነጋግረዉ አልቻለም፡፡ አይኖቹ የሆነ ኢንች ያክል ቦታቸዉን ለቀዉ ወደ ፊት ወጣ ያሉ ይመስላሉ፡፡ ጉንጮቹ ተለጠጡ፤ ግባሩ ላይ የተጋደሙት መስመሮች የዘጠና አመት አዛዉንት አስመሰሉት፡፡

የትም ያልተነበበ ሊነበብ የሚገባው ልብ አንጠልጣይ.....ታሪክ          አፍቃሪዋ ነርስ😍😍😍ክፍል:-1ቀይቡኒ አባያ ከ ጥቁር ኪማር ጋር ለብሳ ወደ መናፈሻው ታመራላች ሆስፒታሉ ዉስጥ ጓደ...
25/05/2026

የትም ያልተነበበ ሊነበብ የሚገባው ልብ አንጠልጣይ.....ታሪክ

አፍቃሪዋ ነርስ😍😍😍
ክፍል:-1
ቀይቡኒ አባያ ከ ጥቁር ኪማር ጋር ለብሳ ወደ መናፈሻው ታመራላች ሆስፒታሉ ዉስጥ ጓደኛዋን ፈልጋ ስላጣች ምን አልባት እዛ ትሆናለች ብላ ነው ሩጫ ባልተናነሰ አረማመድ ስትራመድ ግራ የገባው ዶክተር
" ሲስተር ሲስተር......... " እየሮጠ ተከተለት አጠገቧ ሲደርስ
"ኢፍቱ " ብሎ የለበሰችውን ነጭ ጋውን ጎተት አደረገ ደንገጥ ብላ ዞረች
"ምነው በሰላም ነው????" አላት እያለከለከ
"ዳኒዬ ሰላም ነው ትንሽ ራሴን ስላመመኝ ለማረፍ ብዬ ነው " ብላ አረጋግታው ወደ መናፈሻው አመራች

**
ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነው ቦታው ዝም ያለ እና ደስየሚል አየር አለው ለ አይን ሲታይ የሆነ ሚያረጋጋ ሀይል አለው ካነጠፈችው መስገጃ ላይ ተደፍታ እንደ ዝናብ እምባዋን እያንጠባጠበች ታነባለች በመሀል ኢፍቱ መታ ተጠመጠመችባት ግንባሯን ከ መስገጃው ላይ አንስታ የ ጓደኛዋ እቅፍ ዉስጥ ገባች ተቃቅፈው ለ ደቂቃዎች አለቀሱ ከ እቅፏ እያወጣቻት ፊቷ ላይ ያለውን እምባ መጠራረግ ጀመረች
"የኔ አፍቃሪ ሴት ዉሀ ጠጪ" ብላ አጠገቧ የነበረውን ሀይላንድ ከፍታ ሰጠቻት በ እምባ የታጠበውን ፊቷን በ ውሀው ታጥባ ከዛን ጠጣች ፊቷ ፍም ሆኗል እራስ ምታቷ እየጨመረ ነው ኢፍቱ እሷን ምታረጋጋበት ቃላት ስላጣች ዝም ብላ ከ ሷ ጋር ታነባላች ትንሽ አሰበች እና ስልኳን ከፍታ "ʙᴇɴɪᴍ✨" ተብሎ ተፅፎ ወዳለው ደወለች
"አሳላሙ አለይኩም ሀዩ "
"ዋለይኪ ሳላም ሀቢብቲ "
"ሀዩ በአላህ ሆስፒታል ነን ለ ሮዚ ደውለሽ አብራችሁ ኑ "
"አዲስ ነገር አለ ወይስ ምን ተፈጥሮ ነው ድምፅሽ ልክ አይደለም "
"ብታይ ዶክተሩ ፍቅረኛ አለው " ኢፍቱ ምን እንደምትል ግራ ሲገባት እንዲ ብላ ስልኩን ዘጋች ሀያት ፋርማሲ ስለሆነች ለ ሮዛ ደውላ እንድትመጣ ነገረቻት እስከዛ መድሀኒቶችን ማስተካከል ጀመረች

*
መካከለኛ ስፋት ያለው እና ለእይታ ሚያምር ፋርማሲ ነው ጃዕፈር የ ፋርማሲው ባለቤት ነው ከወንድሙ ጋር የ ሂሳብ ቦታ ቁጭ ብለው እያወሩ ነው ሀያት ከነሱ ፊት ለ ፊት ከላይ የተደረደሩትን መድሀኒቶችን ላስቲክ ወንበር ላይ ቆማ አንስታ እያፀዳች ነው ጃዕፈር ጀርባውን ሰቷት ኢምራን ደሞ ፊት ለፊቱ ሆና እያያት ነው ከላይ ተደርድሮ ያለውን ለማንሳት ስትን ጠራራ ወንበሩ ፕላስቲክ ስለሆነ አዳለጣት ብቻ ወድቃ እራሷን መሬት ላይ አገኘች ጃዕፈር ደንግጦ ሲዞር ሀያት መሬት ላይ ተዘራለች ኢምራን ክትክት ብሎ ይስቃል ጃዕፈር ግራ ገባው ሊያነሳት ብሎ እሷን መንካት አይችል ግራ ሲገባው
"ሀዩዬ በርቺ " ይላታል
" ጃ.. ደና ነኝ " ከወደቀችበት እየተነሳች ምን እንደ ሆነ ጥፍሯን ስለመታት በጣም አመማት አልቻለችም አለቀሰች
"ሀዩ " አላት እያዘነ
"ደና ነኝ አለች አይደል በቃ ተዋት" አለ ኢምራን ከ ሩቅ እያያቸው
"ልክ ነው አትጨነቅ ደሞ ሮዚ እየመጣች ነው የዚኔ ደርሳለች" አለች እምባ እየተናነቃት ተስተካክላ ወንበር ላይ ተመቀመጠች ትንሽ ቆይታ ሮዛ መታ
"አሳላሙ አለይኩም " እያለች ገባች
"ዋለይኪሳላም ነይ ነይ ጊቢ " አላት ጃዕፈር
"ምነው ምን ሆነሽ ነው?" ምታለቅሰዋን ሀያትን ስታያት ደንግጣ ሀያት ሮዛን ስታያት አልቻለችም በቃ አለቀሰች ሮዚም አቅፋ አባበለቻት
"ምን እንደ ህፃን ያነፋርቅሻል በቃ ጠንከር በይ " ኢምራን ለቅሶዋ ስልችት ስላለው
"ሁሌም አላህን ምለምነው አንተ ስታለቅስ ሶፍት እንዳቃብልህ ነው" አለች ምርር እያላት
"ምኞት አይከለከልም" አላት የ ፌዝ ሳቅ እየሳቀ
"ሀዩ በቃ ወደ ቤት ጊቢ እና ዕረፊ " አላት ጃዕፈር በ ኢምራን ንግግር እየተናደደ
"እሺ " አለች ሮዚ ጃዕፈርን እያየች ፈገግ አለች ሀያት ህመሙ ስለ ለቀቃት ሮዛን ተደግፋ ተነሳች
"ደሞ..." አለች ሀያት ወደ ጃዕፈር እየዞረች
"አፍቃሪዋ ልቧ ተሰብሯል መሰለኝ "
"ያቺ ሚስኪን ልብ ተሰበረች?" ጃዕፈር ሮዛን እና ሀያትን ተራበተራ እያየ
"በቃ ነገ እናወራለን" ሀዩ ቦርሳዋን ይዛ ከ ሮዛ ጋር ወደ መኪናዋ ሄደች

"እኔ ምን እንደ ሚገርመኝ ታውቃለህ እቺ ልጅ ግን እንዴት ነው መኪና የኖራት?"
ኢምራን ሀያትን የግርምት እይታ ከሩቅ ሆኖ እያያት
"ሰርታ ነው ወንድሜ በጣም ጎበዝ ልጅ ናት "
ጃዕፈር የወደቁትን መድሃኒቶችን እያነሳሳ

ይቀጥላል..........

??ሞት እና ሴትን አታሳድድ፤ ሁለቱም በጊዜያቸው ይመጣሉ!በህይወት ጉዟችን ላይ ልንገነዘባቸው የሚገቡ ሁለት ታላላቅ እውነታዎች አሉ። ሞት እና ሴት (ወይም የህይወት አጋር)። ሁለቱንም ለማግኘ...
19/04/2026

??ሞት እና ሴትን አታሳድድ፤ ሁለቱም በጊዜያቸው ይመጣሉ!
በህይወት ጉዟችን ላይ ልንገነዘባቸው የሚገቡ ሁለት ታላላቅ እውነታዎች አሉ። ሞት እና ሴት (ወይም የህይወት አጋር)። ሁለቱንም ለማግኘት መሮጥም ሆነ ማሳደድ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም ሁለቱም የራሳቸው የሆነ የማይታጠፍ ቀጠሮ አላቸው።
ለምን?
• ሞት፦ ማንም ሳይጠራው፣ ማንም ሳይፈልገው ቀጠሮውን ጠብቆ ይመጣል። እሱን በመፍራት ወይም በማሳደድ የምንቀይረው ነገር የለም።
• ፍቅር (ሴት)፦ እውነተኛ ፍቅርና ትዳር ደግሞ በሩጫና በማሳደድ የሚገኝ ሳይሆን፣ ፈጣሪ በፈቀደውና ጊዜው ሲደርስ የሚከሰት ተአምር ነው። ራስህን/ሽን ለቁምነገር ስታዘጋጅ፣ የሚገባህ/ሽ ሰው ሳይታሰብ ከፊትህ/ሽ ይቆማል።

አታሳድድ ሞትን፣ አታሳድድ ሴት፣
ሁለቱም ይመጣሉ፣ በጊዜያቸው ፊት።
አንዱ የህይወት ማብቂያ፣ አንዱ የህይወት መጀመሪያ፣
አንዱ የመቃብር፣ አንዱ የቤት መሟያ።
አትድከም በከንቱ፣ አትሩጥ አትኳትን፣
ጊዜው ሲደርስ ያውቃል፣ ያንተን ደጃፍ ማንኳኳትን።
ታገስና ጠብቅ፣ በዝምታ ሆነህ፣
የሚገባህ ይመጣል፣ ጊዜውን ጠብቆልህ።

ባጭሩ...
ራስህን/ሽን አታድክም/ሚ፤ የማይቀረውን ሞት በመፍራት ወይም የህይወት አጋርን በማሳደድ ከመጨነቅ ይልቅ፣ ዛሬህን በአግባቡ ኑር/ሪ። በጊዜው የሚመጣውን በጸጋ ለመቀበል ራስህን/ሽን ማነፅ ላይ ትኩረት አድርግ/ጊ።
ትዕግስት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ናት!

💍 የትዳር እድሜን የሚያረዝሙ 7 ወርቃማ ምስጢሮች ​ክፍል አንድ💋💋👌​ትዳር ማለት ዝም ብሎ አብሮ መኖር ሳይሆን፣ በየቀኑ የሚገነባ ትልቅ ህንጻ ነው። ብዙ ጥንዶች ትዳር ውስጥ ከገቡ በኋላ "...
19/04/2026

💍 የትዳር እድሜን የሚያረዝሙ 7 ወርቃማ ምስጢሮች
​ክፍል አንድ💋💋👌

​ትዳር ማለት ዝም ብሎ አብሮ መኖር ሳይሆን፣ በየቀኑ የሚገነባ ትልቅ ህንጻ ነው። ብዙ ጥንዶች ትዳር ውስጥ ከገቡ በኋላ "ፍቅራችን ለምን ቀዘቀዘ?" ወይም "መግባባት ለምን አቃተን?" ብለው ይጠይቃሉ። እውነታው ግን፣ ትዳር እንደ አበባ ውሃ ካልጠጣ ይጠወልጋል። ለረጅም ዘመን በፍቅር እና በሰላም አብሮ ለመቆየት እነዚህን 7 መሰረታዊ ነጥቦች ማወቅና መተግበር አስፈላጊ ነው፦
​1. "መግባባት የትዳር ኦክስጅን ነው" (Effective Communication)
አብዛኛው ጸብ የሚመጣው ካለመነጋገር ነው። ስሜታችሁን ሳይሸሽጉ፣ በግልጽ እና በሰከነ መንፈስ ተነጋገሩ። "ይገባታል" ወይም "ይገባዋል" ብላችሁ አትገምቱ። በዝምታ ከመብገን፣ በግልጽ ጠይቆ መረዳት የትዳርን እድሜ ያረዝማል።
​2. "ይቅርታ የማለት እና የመርሳት ጥበብ" (The Art of Forgiveness)
ፍፁም ሰው የለም፤ በትዳር ውስጥ ስህተት አይጠፋም። ነገር ግን ትላንት የሆነውን ነገር ዛሬ ለጸብ ምክንያት አታድርጉት። ይቅርታ ስትባባሉ ከልብ ይሁን፣ እናም ያንን ስህተት ደግማችሁ አታንሱት። ትዳርን የሚገነባው "ይቅር ባይነት" እንጂ "ቂም" አይደለም።
​3. "አድናቆትን አትሰስቱ" (Express Gratitude)
ትናንሽ ነገሮችን ማድነቅ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። "ምግቡ ጣፋጭ ነው"፣ "ለቤታችን የምታደርገው ጥረት ይገርመኛል"፣ ወይም "ስለረዳሽኝ አመሰግናለሁ" የሚሉ ቃላት የትዳር አጋራችሁ ዋጋ እንዳለው እንዲሰማው ያደርጋሉ። አድናቆት ፍቅርን ያድሳል።
​4. "ጓደኝነትን ቅድሚያ መስጠት" (Be Best Friends First)
ከፍቅረኛነት ባለፈ ጓደኛሞች ሁኑ። አብራችሁ ሳቁ፣ አብራችሁ ተጫወቱ፣ ሚስጥራችሁን ተጋሩ። በትዳር ውስጥ ጓደኝነት ሲኖር፣ አስቸጋሪ ጊዜያትን ማለፍ በጣም ቀላል ይሆናል። አጋርሽን እንደ የቅርብ ጓደኛሽ ካየሽው፣ መተማመናችሁ ይጨምራል።
​5. "ከሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ተጠንቀቁ" (Protect Your Privacy)
በትዳራችሁ መሃል የሚፈጠርን ችግር በሁለታችሁ መካከል ብቻ ለመፍታት ሞክሩ። ቤተሰብም ሆነ ጓደኛ በየቀኑ የቤታችሁን ምስጢር እንዲያውቁ አታድርጉ። የትዳር አጥር መጠበቅ ያለበት በሁለታችሁ ጥረት ነው።
​6. "ለአጋራችሁ ጊዜ ስጡ" (Quality Time)
ልጆች፣ ስራ እና የኑሮ ሩጫ ትኩረታችሁን ሊወስዱት ይችላሉ። ነገር ግን ለትዳር አጋራችሁ ብቻ የሚሆን ልዩ ጊዜ ይኑራችሁ። ስልካችሁን አጥፍታችሁ፣ አይን ለአይን ተያይታችሁ የምታወሩበት ጊዜ ፍቅራችሁ እንዳይቀዘቅዝ ያደርጋል።
​7. "በትናንሽ ነገሮች ፍቅርን መግለጽ" (Small Gestures)
ፍቅር ሁሌም ትልቅ ስጦታ አይፈልግም። በስራ መሃል "አስብሃለሁ" የሚል አጭር መልእክት መላክ፣ አበባ መግዛት፣ ወይም እጅ ለእጅ ተያይዞ መራመድ ትልቅ ትርጉም አላቸው። እነዚህ ትናንሽ ድርጊቶች "አሁንም እወድሃለሁ" የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ።
​ለተከታዮቻችን፦
"እናንተስ በትዳር ውስጥ የትኛው ነጥብ ይበልጥ ወሳኝ ይመስላችኋል? ትዳር ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የእናንተ ምስጢር ምንድነው? ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን።"
​ክፍል ሁለት .......y

19/04/2026

ትዳር እና የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት፡ ሰላምን የመመለስ ጥበብ ✍🏽
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የዚህ ገጽ ቤተሰቦች፤
ዛሬ በብዙዎቻችን ቤት ውስጥ ስላለው፣ ነገር ግን በግልጽ ስለማንነጋገረው አንድ ትልቅ አሳሳቢ ጉዳይ ሀሳቤን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ጉዳዩ የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት በትዳር ውስጥ የሚፈጥረው ቀውስ ነው።
ትዳር የሁለት ሰዎች የህይወት ዘመን ቃል ኪዳን ነው። ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ የራሱ የሆነ የቤት ምስጢር፣ የግል ቦታ እና የጋራ ውሳኔዎች አሉት። ሆኖም ግን፣ "የሚስት ቤተሰብ ነን" ወይም "የባል ቤተሰብ ነን" የሚሉ ወገኖች፣ ድንበርን ባለማወቅ በሌላ ሰው የግል ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የትዳርን ሰላም እያደፈረሱ፣ የብዙዎችን ትዳር እስከ መፍረስ ደረጃ እያደረሱት ይገኛሉ።
በትዳር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩት ቤተሰቦች ለራሳቸው መሆን የማይገባውን ቦታ በመስጠት፣ የትዳር አጋሮች እንዲሰግዱላቸው ይፈልጋሉ፣ ይህም እጅግ የሚያሳዝን ነው። አክብሮት በጋራ የሚሰጥ እንጂ የሚለመን አይደለም። ሰላም በሌለበት ቤት ውስጥ መኖር ደግሞ የነፍስን ጤንነት ይጎዳል።
ብዙ ጊዜ ትዳር ውስጥ ሰላም የሚጠፋው በምክንያት ነው። ለምሳሌ፦
• የመግባባት ክፍተት፡ መነጋገር ሲያቅት፣ ትናንሽ ነገሮች እየተከማቹ እንደ ቦምብ ይፈነዳሉ።
• የጋራ አላማ አለመኖር፡ የት መድረስ እንደምትፈልጉ አንድ አቋም ከሌላችሁ፣ ትዳሩ ያለ መሪ ይሆናል።
• መከባበር መጥፋት፡ አንዱ ሌላውን እንደ "በታች" ወይም "ተጠቂ" ሲያየው ሰላም በፍጹም አይገኝም።
እውነተኛ ቤተሰብ ለትዳር አጋሮች አርአያ መሆን፣ ማማከርና ማበረታታት እንጂ በግል ህይወታቸው ውስጥ እየገቡ እንደፈለጉ መናዘዝ የለበትም።
ስለዚህ፣ ይህንን ችግር ለመፍታትና የቤታችንን ሰላም ለመመለስ እንደ መፍትሔ የማያቸው ጥቂት ነጥቦች እነዚህ ናቸው፦
1. የድንበር (Boundaries) ማበጀት
የትዳር ጓደኛሞች በመካከላቸው ሊኖራቸው የሚገባው የግል ቦታ (Private space) መኖር አለበት። ድንበርን የማስከበር ኃላፊነት ግን የጥንዶቹ ራስ ነው። የትዳር ጉዳዮች በባለቤቶች መካከል ብቻ መወሰን እንዳለባቸው መግባባት ላይ መድረስና የቤት ውስጥ ምስጢሮችን ወይም አለመግባባቶችን ለውጭ ሰዎች (ቤተሰብን ጨምሮ) አሳልፎ አለመስጠት ተገቢ ነው።
2. የጋራ አቋም መያዝ
የትዳር ጓደኛሞች የየቤተሰቦቻቸውን ጣልቃ ገብነት በአንድ ላይ ሆነው በጨዋነት ግን በጥብቅ ማስቆም አለባቸው። አንደኛው ወገን ለቤተሰቡ ሲያደላ፣ ሌላኛው ወገን ይጎዳል። ስለዚህ ጥንዶች ለቤተሰቦቻቸው አክብሮት ቢኖራቸውም፣ ትዳራቸው ግን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ቀዳሚ ተቋም መሆኑን ማሳወቅ አለባቸው።
3. መከባበር በጋራ የሚመጣ መሆኑን ማሳየት
አንድ ሰው አክብሮት የሚፈልግ ከሆነ፣ መጀመሪያ አክብሮት መስጠት እንዳለበት መረዳት አለበት። የጥንዶቹ ኃላፊነት በጨዋነት "ይህ ድርጊታችሁ ቤታችንን እየረበሸ ነውና እባካችሁ በነጻነት እንኑር" ብሎ መናገር ነው።
4. በራስ ላይ ማተኮር
የማይማሩ፣ ስነ-ስርዓት የሌላቸው እና የሌላውን ቤት ለማፍረስ የሚሞክሩ ሰዎችን ለመለወጥ መሞከር ብዙ ጊዜ ጉልበትን ከማባከን ውጪ ውጤት አያመጣም። ለእንደዚህ አይነቶቹ ምላሽ አለመስጠትና ርቀት መፍጠር ሰላምን ለመጠበቅ ይረዳል።
ማጠቃለያ
ትዳር እርስ በርስ መረዳዳት፣ መከባበር እና መተማመን ካልሆነ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት እንጂ ትዳር ሊባል አይችልም። ትዳር የፈጠራ ስራ ነው። ሰላም ካልፈጠሩበት በስተቀር በራሱ ጊዜ ሰላማዊ አይሆንም። ትዳርን ለማዳን፣ ጊዜያዊ ርቀት መፍጠር (ለምሳሌ፦ ከቤተሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ) አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
በእናንተ እይታስ፣ የትዳር አጋሮች ከቤተሰብ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው እንዲኖሩ ምን መደረግ አለበት? የትዳርን ድንበር ለማስከበር ባለቤቶች ምን አይነት አቋም ቢወስዱ ውጤታማ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ሀሳባችሁን በኮሜንት ላይ አካፍሉኝ።
አመሰግናለሁ።

ሉና እና የልብ ጓደኛዋ ሚያ ምግብ በልተው እንደጨረሱ፣ ሚያ "ዛሬ እኮ ልደትሽ ነው፤ እስቲ አሪፍ ነገር ጋብዢኝ" አለች። ሉናም በደስታ "እንዴታ!" ብላ የሁለቱን ሂሳብ ከፈለች።ከቀናት በኋላ...
02/01/2026

ሉና እና የልብ ጓደኛዋ ሚያ ምግብ በልተው እንደጨረሱ፣ ሚያ "ዛሬ እኮ ልደትሽ ነው፤ እስቲ አሪፍ ነገር ጋብዢኝ" አለች። ሉናም በደስታ "እንዴታ!" ብላ የሁለቱን ሂሳብ ከፈለች።

ከቀናት በኋላ ሁለቱ ጓደኛሞች ሱፐርማርኬት ውስጥ ሲገበያዩ፣ አንድ መልከ መልካም ወጣት ካሸር አካባቢ ሆኖ ፈገግ አለላቸው።
ሉና በሹክሹክታ፣ "ዋው! ይሄ ልጅ በጣም ያምራል" አለች።
ሚያ ግን "ተረጋጊ፣ እኔ ሄጄ አናግሬው አመቻችልሻለሁ" ብላ ወደ ልጁ ሄደች።

ወጣቱም "ሃይ፣ ጓደኛሽን ወደድኳት። ፍቅረኛ ወይም ባል አላት?" ሲል ጠየቀ።
ሚያ ግን ዋሸች። "እንዴታ! እሷ እኮ የታጨች ናት። እኔ ሚያ እባላለሁ፣ ነጻ ነኝ። ስልኬን መውሰድ ትችላለህ" አለችና ስልክ ተለዋወጡ።

ሚያ ወደ ሉና ስትመለስ፣ ሉና በጉጉት "እ... ምን አለ?" በማለት ጠየቀቻት::
ሚያም ኮስተር ብላ "ተይው ባክሽ፣ ያገባ ሰው ነው። እርሺው" በማለት ዋሸቻት::

ከዚያም ሸመታውን ቀጠሉ። ሚያ ውድ የሆኑ ሽቶዎችን እና ወይኖችን ለራሷ ቅርጫት ውስጥ ጨመረች። ክፍያ ቦታ ሲደርሱም ሚያ በፈገግታ "ሉና፣ ዛሬ እኔ ነኝ የምከፍለው" አለች።

ከዛም ልክ እንደሚከፍል ሰው በማድረግ ካርዷን ልታወጣ አስመስላ ስልኳን አወጣችና "ቆይ... ስልክ እየተደወለልኝ ነው፣ መመለስ አለብኝ" ብላ ወደ ውጭ ወጣች። ይህንን ያደረገችው ሉና እንድትከፍልላት በማሰብ ነበር።

ሉናም በየዋህነት "እሺ ሂጂ ችግር የለውም እኔ እከፍላለሁ" አለች።

ሆኖም ሚያ እንደወጣች ገንዘብ ተቀባይዋ ለሉና፣ "እመቤቴ፣ አንቺ የዘወትር ደንበኛችን ስለሆንሽ አንድ ነገር ልንገርሽ። ቅድም ጓደኛሽ ለዛ ልጅ 'እሷ እጮኛ አላት' ብላ ዋሽታዋለች። ለታማኝነትሽ ይሆን ዘንድ ይህንን ስጦታ ያዢልኝ" አለቻት።

ሉናም ይሄንን ስትስማ ደነገጠች! "ምን? እጮኛ አላት አለችው?" በማለት በልብ ጕደኛዋ ክህደት ተበሳጨች::

ወዲያውኑም ዞራ ሚያን ተመለከተቻትና ለካሸሯ፣ "እሺ፣ አመሰግናለሁ። የሁለቱንም ሂሳብ ጓደኛዬ ሚያ ትከፍላለች" ብላ ፈገግ እያለች ለሚያ ምልክት ሰጥታት ወጥታ ሄደች።

ሚያም የውሸት ስልክ ጥሪዋን ጨርሳ በደስታ ወደ ውስጥ ገባች። እቃዎቿን ይዛ ለመውጣት ስትሞክር፣ ካሸሯ በጩኸት "የእኔ እህት! ወዴት ነው የምትሄጂው? ሂሳብ አልከፈልሽም!" አለቻት::

ሚያም በጣም ደነገጠች። መልሳም "ምን ማለትሽ ነው? ጓደኛዬ ከፍላለች እኮ!" አለች::

ካሸሯም "አይደለም! የሷንም ጨምሮ አንቺ እንደምትከፍይ ነው የነገረችኝ። ክፈይ!" አለች::

ሚያም በድንጋጤ እና በንዴት ተቃጠለች። አማራጭ ስላልነበራት የተከመረውን ሁሉም ሂሳብ ከፈለች።

--------------- --------------- ---------------

አብሮህ የሚስቅ ሁሉም ጓደኛ አይደለም።

ምቀኛ ጓደኛ እድልህን ይዘጋል፣ ኪስህንም ያራቁታል።

02/01/2026

Big shout out to my newest top fans!በጣም ነው ማመሰግነው Halima Abdu, Yabibal Yab, Birhanu Siyoum, Yordi Mekonnen, Nuriya Melese, Biqila Gammachu, Ane Abo, ያቺው አፍቃሪ ኔነኝ, Samri Yabatwa, Hani Ye Gebreal Lij, Miki Mayko, ብዙነሽ ታምሩ, Yeneblot Abene Tegegne, Mahi Mahi, ዝምታ ነው መልሴ, Hiwot Fikadu, Lielt Megrsa Abebe, W Menzewa W Menzewa, Seli Aweke

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beautiful Ethiopian Women Detect languageየ ኢትዮጵያ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Beautiful Ethiopian Women Detect languageየ ኢትዮጵያ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች:

Share