06/05/2026
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
ዛሬ በተካሄደው 6ኛው ዘመን 6ኛው መደበኛ የትግራይ ምክር ቤት ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በአብዛኛው ድምፅ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተመርጠዋል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ ወይዘሮ ኪሮስ ሐጎስ አፈ-ጉባኤ፣ ወይዘሮ ምህረት በርሄ ደግሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተሰይመዋል።
ምክር ቤቱ ስራውን በይፋ የጀመረው የፕሪቶሪያው ስምምነት በፌደራል መንግስቱ በኩል ተጥሷል በሚል ሲሆን፣ አዲሱ ፕሬዝዳንትም እስከ ቀጣዩ ስብሰባ ድረስ በአስፈፃሚው አካል ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያና ሹመት እንዲያደርጉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ይህ እርምጃ በትግራይ ፖለቲካዊ መድረክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዴት ሊያመራው እንደሚችል የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።