Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር

Ethiopian Construction Network  የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር Your Universal Commercial Solution © +251913044262

🟢 ማስታወቂያየጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለወጣላችሁ ዕድለኞች በሙሉሐምሌ 28/2018 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቅድመ ቆጣቢዎች የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ተካሂዶ 367 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅድመ ቆ...
29/08/2026

🟢 ማስታወቂያ

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለወጣላችሁ ዕድለኞች በሙሉ

ሐምሌ 28/2018 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቅድመ ቆጣቢዎች የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ተካሂዶ 367 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅድመ ቆጣቢዎች ዕጣ የወጣላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡

እነዚህም ቤቶች ዕጣ ለደረሳቸው ቅድመ ቆጣቢዎች መተላለፍ ስላለባቸው የሚከተሉትን መረጃዎች በማሰባሰብና በማሟላት በግንባር እየቀረባችሁ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

1. ለዚሁ አላማ የተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብተር ኮፒ
2. የምትኖሩበት ወረዳ መታወቂያ ኮፒ
3. የጋብቻ ሁኔታ የሚገልጽ ሰርቲፊኬት ኮፒ
4. የቅድመ ቆጣቢነት ማረጋገጫ ቢጫ ካርድ
5. አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ

የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

🟢 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ መመሪያAddis Ababa City Administration Building Permit and Control...
29/08/2026

🟢 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ መመሪያ
Addis Ababa City Administration Building Permit and Control Authority
Building Guidelines and Standards Directive
መመሪያዎችን ያንብቡ ይፈትሹ። ካላስፈላጊ ኪሳራ ፣ ቅጣት እና እንግልት ከመሳሰሉ ነገሮች ይጠበቁ። መረጃዎን አዘውትረው በማዳበር ተጋላጭነትዎን እያደር ይቀንሱ። ለሌሎችም እንዲዳረስ ሼር ያድርጉ። መልካምነት መልሶ ይከፍላል።
ሙሉውን መመሪያ በቀላሉ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ በ PDF ማግኘት ይችላሉ።
ሰብስክራይብ በማድረግም የተለያዩ መረጃዎችን ያግኙ።
Full directive is available in PDF on our Telegram channel.
https://t.me/etcnhq
ማንኛውንም ንብረት እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ተሽከርካሪዎችን መግዛት መሸጥ መከራየት ማከራየት በሎቤድ ማስጫን ሲፈልጉ እንደተለመደው ይደውሉልን።
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

29/08/2026

ስለኮሚሽን ሠራተኞች በማህበራዊ ሚዲያ የሚነዛው ጅምላ ሥም ማጥፋት ተገቢነት የለውም። ከዓለም ስቶክ ማርኬቶች እስካንድ ክፍል ቤት ፈላጊና ተፈላጊን የሚያሳልጥ የተከበረ ሙያ ነው። በርካታ ክፍተቶች ቢኖሩም።

•  የፌደራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ•  FDRE Public Procurement and Property Administration Proclamation •  የጨረታ እና ሥራ ገጽ...
22/08/2026

• የፌደራል መንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ

• FDRE Public Procurement and Property Administration Proclamation
• የጨረታ እና ሥራ ገጽን መጎብኘት አይርሱ
ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page
ሙሉውን አዋጅ PDF
Full proclamation is available in PDF on our Telegram channel.
በቀላሉ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ሰብስክራይብ በማድረግም የተለያዩ መረጃዎችን ያግኙ።
https://t.me/etcnhq
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

• የፌስቡክ ማኅበር (ግሩፕ) አባል ሆነዋል? አባል ይሁኑ። መረጃ ይለዋወጡ ፤ ሥራ፣ሙያ፣ንግድዎን ያስተዋውቁ ፤ ገቢ እና ገበያዎን ያሳድጉ።• Have you joined our Facebook g...
20/08/2026

• የፌስቡክ ማኅበር (ግሩፕ) አባል ሆነዋል? አባል ይሁኑ። መረጃ ይለዋወጡ ፤ ሥራ፣ሙያ፣ንግድዎን ያስተዋውቁ ፤ ገቢ እና ገበያዎን ያሳድጉ።

• Have you joined our Facebook groups? Join, share information, advert your businesses and service.

Facebook groups,

• Ethiopian Commercial Network™

• Construction Technology & Management Professionals - COTMp

• Construction Ethiopia Network

Also visit some of our,

pages,

• Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር

• ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page

• Ethiopian Agriculture Network የኢትዮጵያ ግብርና አውታር

• Ethiopian Industry Network የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አውታር

• Ethiopian Mines Network የኢትዮጵያ ማዕድን አውታር

• The Capital Market Network Stockመርካቶ

Subscribe to the central Telegram channel,

• https://t.me/etcnhq
.. and more networks. Designed for Your universal commercial solution.

Contact :

WhatsApp

• 091 304 4262

Call / SMS / Viber / WeChat... :

• +251 913 04 42 62

ቴዎድሮስ ፡ Mr. Tewodros
( Teddy™Viber ፡ ቴዲ™ቫይበር )
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ጥሪ አቅርቧል። ለመሆኑ የሥራ ተቋራጮች መመ...
15/08/2026

ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ጥሪ አቅርቧል።

ለመሆኑ የሥራ ተቋራጮች መመልመያና የሥራ ስምሪት መመሪያው ምን ይላል? መመሪያው እና ማስታወቂያው እንደሚከተለው ቀርቧል።

ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መነሻ

1. ለስራ ተቋራጮች ምዝገባ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፡-

ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ለ) በምዝገባው ወቅት የሰነዶቹን ዋና እና አንድ የማይመለስ ቅጂ በአካል የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ፣ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ተወካይ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ከደረጃ 1-4 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ(GC) እና ( BC )ህንፃ ተቋራጭ እንዲሁም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC) ደረጃ 5 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ ።

3. ከቅዳሜ 9 /12/2018 ዓ/ም (ከጠዋቱ 2፡30) ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት( እስከ ሀሙስ 14/12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 11፡30) በአካል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል በሚገኝ አዳራሽ ላይ ምዝገባ በማድረግ መረጃዎቹ መሟላታቸው በመዝጋቢው ሲረጋገጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል።

4. ተገቢውን ሰነድ በማቅረብ የምዝገባ ሂደቱን በሚገባ ያሟለ ተቋራጮችን በተመለከተ ምዝገባው በተጠናቀቀ በ 24 ሰዓት ውስጥ በቀን 15/12/2018 ዓ/ም በተቋሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ እና በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ ቦርድ 11ኛ ወለል የሚለጠፍ ይሆናል፡፡

5. ተቋራጮች የቅድመ ምዝገባ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ቀን 27/12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 11:30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተቋራጮች ለምዝገባ እና ለቴክኒካል ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር ለደረጃ 1 ብር 7,500 (ሰባትሺ አምስት መቶ ብር ) ፣ ለደረጃ 2 ብር 6,500 ( ስድስት ሺ አምስት መቶ ብር ) እና ለደረጃ 3 ብር 5,500 አምስት ሺ አምስት መቶ ብር ) ፣ ለደረጃ 4 ብር 5,000 (አምስት ሺ ብር ) ፣ ለደረጃ 5 ብር 4,500 አራት ሺ አምስት ብር ) መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
**

አድራሻ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ተማ ወረዳ 01
በተለምዶ ባምቢስ አከባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ ላይ 11ኛ ወለል እንገኛለን።
ነሀሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሙሉውን መመሪያ PDF
በቀላሉ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
https://t.me/etcnhq
ማንኛውንም ንብረት እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ተሽከርካሪዎችን መግዛት መሸጥ መከራየት ማከራየት በሎቤድ ማስጫን ሲፈልጉ እንደተለመደው ይደውሉልን።
0913044262 ቴዎድሮስ (Teddy™Viber)
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

Check this out !Our tender page is updating... ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page https://facebook.com/ecntenderRe...
11/08/2026

Check this out !
Our tender page is updating...
ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page
https://facebook.com/ecntender
Rent, sell, and buy anything with us

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የኩነት ማኔጅመንትና ማርኬቲንግ ክፍል በሚከተሉት አለምአቀፍ የንግድ ትርኢቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸዉን የንግዱን ማህበረሰብ አባላት እየመዘገ...
11/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የኩነት ማኔጅመንትና ማርኬቲንግ ክፍል በሚከተሉት አለምአቀፍ የንግድ ትርኢቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸዉን የንግዱን ማህበረሰብ አባላት እየመዘገበ ነዉ።
Canada Construction Expo
Germany Business Forum
Pakistan International Trade Fair
በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት የሚያዘጋጃቸዉን የንግድ ትርኢቶችንና ባዛሮችን ከተለያዩ ኩነት አዘጋጆች ጋር በትብብር መስራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከም/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት የምትፈልጉ ኩነት አዘጋጆች በተያያዘዉ የጥሪ ደብዳቤ መሠረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
Ethiopian Chamber of Commerce
ስልክ፡ +251115514005
የማመልከቻ ቅጹን PDF በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ሰብስክራይብ በማድረግም የተለያዩ መረጃዎችን ያግኙ።
https://t.me/etcnhq
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

🔴 ካሣ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጡ አዋጅ ፣ ደንብ እና መመሪያዎች ምን ይላሉ? የብዙኅን አንገብጋቢ ጥያቄ ፤ የአሳዛኝ ውጣ ውረድ ምንጭ እና መልስ ጭ...
08/08/2026

🔴 ካሣ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጡ አዋጅ ፣ ደንብ እና መመሪያዎች ምን ይላሉ?
የብዙኅን አንገብጋቢ ጥያቄ ፤ የአሳዛኝ ውጣ ውረድ ምንጭ እና መልስ ጭምር የሆነው ይህ መረጃ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ Share በማድረግ ይተባበሩ። መልካምነት ለራስ ነው።
🔴 ሀ፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ፤
🔴 ለ፤ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈል ካሳ እና ተነሺ ስለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፤
እና
🔴 ሐ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲለቀቅ ካሳና ምትክ የሚሰጥበት እና የልማት ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት መመሪያ
🔴 ሀ፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1161/2011 ፤
መንግስት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች መሬትን መጠቀም አስፈላጊ ስለሆነ፤
የአገሪቱ ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና የነዋሪዎቹም ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ በከተሞች ፕላን መሠረት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማት አስፈላጊ በመሆኑ፣እንዲሁም በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች መሬት አዘጋጅቶ ማቅረብ በማስፈለጉ፤
የመሬት ይዞታ እንዲለቅ ለተደረገ ባለይዞታ ተገቢና ተመጣጣኝ ካሣና የተነሽ ድጋፍ ለመክፈል ግምት ውስጥ መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎችን ለይቶ መወሰን በማስፈለጉ፤
ካሣውን የመተመን፣ የመክፈል እና ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋም ሥልጣንና ኃላፊነት ያለባቸውን አካላት በግልጽ ለይቶ ለመወሰን በማስፈለጉ፤
በነባሩ ሕግ ያጋጠሙ የሕግ ክፍተቶችን ሌሎች የመሬት ይዞታ ለማስተካከልና የሚለቀቅበትን እና ካሣ የሚከፈልበት ሥርዓቱን ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ከይዞታ መነሳትና ካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ ስለሚኖር የቅሬታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት በግልጽ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤
የፌደራል መንግሥት የመሬት አጠቃቀም ሕግ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 51(5) በመደንገጉ፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቅ ንብረትን በሚመለከት ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ እንዲከፈል በአንቀጽ (8) በመደንገጉ እንዲሁም ተነሺዎች በመንግስት ዕርዳታ እንዲቋቋሙ በአንቀጽ 44(2) የተቀመጠውን መሠረተ ሀሳብ በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (2)(ሀ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
🔴 ለ፤ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈል ካሳ እና ተነሺ ስለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 472/2012 ፤
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 5 እና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበትን እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 አንቀጽ 26(1) መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡
🔴 ሐ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲለቀቅ ካሳና ምትክ የሚሰጥበት እና የልማት ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት መመሪያ ቁጥር 79/2014
ሙሉ አዋጅ ደንብ እና መመሪያዎቹን በ PDF በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
Full proclamation, regulation and directive are available in PDF on our Telegram channel.
https://t.me/etcnhq
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

🚦🚥 የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ የደንብ 557/2016 ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አስኪጸድቅ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማገድ ለጊዘው እንዲቆም ተደረገ‎.‎(ት/ማ/ባ ነሀሴ/2...
07/08/2026

🚦🚥 የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ የደንብ 557/2016 ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አስኪጸድቅ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማገድ ለጊዘው እንዲቆም ተደረገ
‎.
‎(ት/ማ/ባ ነሀሴ/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማጅመንት ባለሰልጣን የደንብ ተላላፊዎችን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መቀበልም ሆነ ሰሌዳ መፍታት ሳያስፈልግ የዲጂታል የትራፊክ ቁጥጥር እና ቅጣት ማስፈጸሚያ ሲስተም ስርዓት በመዘርጋት የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጣር የወጣውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 የቅጣት አወሳሰንን እየተገበረ ይገኛል፡፡
‎.
‎በመሆኑም ከደንቡ ተግባር ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በደንብ መተላላፍ የነጥብ ጣሪያ ደርሰው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስድና እና ነጥባቸው ሳይሞላም አስቀድሞ ስልጠና ወስደው ነጥብ የሚቀንስላቸው ደንብ ተላላፊዎች በደንቡ አንቀት 96 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ በሁለቱም የእውቅና ክህሎት ስልጠና ወስደው የወሰዱበትን ማረጋጋጫ ሲያቀርቡ እግዱ እንደሚነሳ ይደነግጋል፡፤
‎.
‎ይሁን እንጂ ከአፈጻጸም አንጻር ይኸው አገራዊ ደንብ /በሌሎች ክልልች ተግባራዊ ባለመደረጉ እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚያሽከረክሩ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ብቻ መተግበሩ በደንብ ተላላፊዎች ዘንድ የፍትሀዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡
‎.
‎ባለሰልጣን መ/ቤቱም ይህንኑ የፍትሀዊነት ጥያቄ ለመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት ባሳወቀው መሰረት አና ተቋሙም ችግሩን በመረዳት በቀን 23/11/2018 በቁጥር 1904/18 በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡
‎.
‎በምላሹም ከደንብ ትግበራ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ደንብ ተላላፊዎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና የሚያገኙበትን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መመሪያ ሲዘጋጅ መቆየቱን አመላክቷል፡፡
‎.
‎እንዲሁም መመሪያውም ያለበትን ሂደቶች አልፎ በአሁኑ ወቅት ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩንና በሌሎች ክልሎችም ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ሲባል ለጊዜው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃዱን የማገዱ ተግባር አንዲዘገይ በማለት አሳውቋል ፡፡
‎.
‎በመሆኑም የደንብ መተላለፉ የገንዘብ ቅጣቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ጸድቆ እስኪላክ ድረስ የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ ለጊዜው በነጥብ እና በቆይታ /ሳይከፍል 6 ወር የቆየ/ ከዚህ በፊት የታገዱትም ሆነ በቀጣይ የሚታገድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ መቆሙን እንገልጻለን፡፡ ክእግዱ መቆም በስተቀር ደንብ ተላላፊዎች ያሉባቸውን የቅጣት ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
‎.
‎የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
‎.
‎ሙሉውን ደንብ PDF
‎በቀላሉ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
‎ሰብስክራይብ በማድረግም የተለያዩ መረጃዎችን ያግኙ።
‎.
‎Full Regulation is available in PDF on our Telegram channel.
‎.
‎https://t.me/etcnhq
‎.
‎Stay tuned.
‎Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

Address

Home
Addis Ababa
00251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር:

Shortcuts

Share