GAMO TIMS

GAMO TIMS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from GAMO TIMS, Business Center, Arba Minch'.

  ብሔራዊ ፓርክ ቀጥሎ ሁለተኛው  የማዜ ብሔራዊ ፓርክ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት !! #ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንደሽን ከልብ እናመሰግናለን !!
24/07/2026

ብሔራዊ ፓርክ ቀጥሎ ሁለተኛው የማዜ ብሔራዊ ፓርክ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት !!
#ኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንደሽን ከልብ እናመሰግናለን !!

መብት፣ግዴታውንና አሰራሩን በማወቅ እንኑር የእኛዎች!!የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ መክፈያ ጊዜ! (በህግ ትርጉም)✅ በመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አለኝ።   *** ( ደካማና ያረጀ አመለ...
10/07/2026

መብት፣ግዴታውንና አሰራሩን በማወቅ እንኑር የእኛዎች!!

የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ መክፈያ ጊዜ! (በህግ ትርጉም)

✅ በመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አለኝ።

*** ( ደካማና ያረጀ አመለካከት ውስጥ ያሉ ሰዎች በዚህ ፖስት ምክንያት ልያኮርፉንና ወደላይ ወደታች ልትሉ ትችላላችሁ ግን ያው ሕግ፣ ሕግ ነውና ተፈጻሚ ነት ከለለው የተፃፈ ሰነድ እንጂ ለሠራተኞች የሚፈይደው ነገር የለም)***

!

❶ የደመወዝ መብት

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ፕሮክላሜሽን አዋጅ ቁጥር 1064/2017

🔹 አንቀፅ 55 (1)

➲“ሰራተኛ ለሚፈጽምበት ሥራ ተመጣጣኝ ደመወዝ በወቅቱ የመቀበል መብት አለው።”

👉 ይህ አንቀፅ ደመወዝ መክፈል የመ/ቤት ግዴታ መሆኑን በግልፅ ያሳያል።

❷ የደመወዝ መክፈያ ጊዜ

🔹 አንቀፅ 56 (1)

“የሰራተኛ ደመወዝ በወር አንድ ጊዜ በተወሰነው የመክፈያ ቀን ማለትም በቀን 30 መከፈል አለበት።”

👉 ይህ ማለት፦

ደመወዝ መክፈል አማራጭ አይደለም፡፡
የመክፈያ ቀኑ ሲያልፍ መዘግየት ይቆጠራል፡፡

❸ የደመወዝ መዘግየት ሲኖር

🔹 አንቀፅ 56 (2)

“ደመወዝ በተወሰነው ጊዜ ካልተከፈለ ሰራተኛው ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው።”

👉 ህጉ “ለስንት ቀን መታገስ አለበት” የሚል ጊዜ አልወሰነም።

✔️ ስለዚህ መዘግየት ከመክፈያ ቀኑ ካለፈ ቀጣዩ ቀን ጀምሮ ህገወጥ ነው።

❹ የመ/ቤት ኃላፊነት

🔹 አንቀፅ 13 (1)

➲“መ/ቤት የሰራተኞቹን መብት ማክበርና ማስፈጸም ግዴታ አለበት።”

👉 ደመወዝ መዘግየት የመ/ቤት የህግ ግዴታ መጣስ ነው።

❺ የቅሬታ እና የህግ መንገድ

🔹 አንቀፅ 74 (1)

➲“ሰራተኛ መብቱ ሲጣስ በመጀመሪያ ለመ/ቤቱ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል።”

🔹 አንቀፅ 74 (3)

➲ “ቅሬታው ካልተፈታ ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ወይም ለፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።”

የህጉ ዋና ውሳኔ (ማጠቃለያ)፦በፕሮክላሜሽን 1064/2017 መሠረት፣ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዙ በወሩ መጨረሻ ማለትም በቀን 30 መክፈል አለበት፤ “መታገስ” የሚባል የተፈቀደ ጊዜ የለም። መዘግየት ከዚያው ቀን ጀምሮ ህገወጥ ነው።

ከታማኝ ምንጭ !!

መጤ አረም ተነቀለ
16/06/2026

መጤ አረም ተነቀለ

02/06/2026

ጋሞ ቁጫ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ!!
ጋሞ ቁጫ መሬቱም ህዝቡም ጋሞ ነው
ሌላው ወደ መጣበት ተሸኝቷል

27/05/2026

የአርባምንጭ ከተማ ውብ ገጽታ
GAMO TV

27/05/2026

ቁዴፓ እያለቃቀሰ ነው

27/05/2026

2015/20 የአርሰናል ሆኗል

የስፖርት ዜና፡ የሁለቱ ታዋቂ ሰዎች የጋራ የልደት በዓል! ዛሬ ግንቦት 19 ቀን ለየት ያለ ቀን ነው! በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ደምቆ እየተጫወተ የሚገኘው ብራዚላዊው ኮከብ ማቴውስ ኩኛ (M...
27/05/2026

የስፖርት ዜና፡ የሁለቱ ታዋቂ ሰዎች የጋራ የልደት በዓል!

ዛሬ ግንቦት 19 ቀን ለየት ያለ ቀን ነው! በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ደምቆ እየተጫወተ የሚገኘው ብራዚላዊው ኮከብ ማቴውስ ኩኛ (Matheus Cunha) እና በሀገራችን ስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ስፖርት ጋዜጠኛ አሉላ (ብራንድ) የልደት ቀናቸውን በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ።

ሁለቱ ወዳጆች የማንቸስተር ዩናይትድን መለያ በመልበስ ልዩ ትስስራቸውንና ደስታቸውን ገልጸዋል!

ማቴውስ (Matheus) የማንቸስተር ዩናይትድ እና የብራዚል ብሄራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዛሬ 27ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከብራል።

ጋዜጠኛ አሉላ (ብራንድ) መረጃዎቹ ሁሌም ለየት የሚሉት፣ በኢትዮጵያ ስፖርት ሚዲያ ውስጥ ስሙ የሚነሳው ጋዜጠኛ አሉላ (ብራንድ) ዛሬ 28ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ይዟል።

ለማቴውስ እና ለጋዜጠኛ አሉላ (ብራንድ) መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላቸው እንመኛለን!

በቀጣይም ስኬታማና የደስታ ዘመንን እንዲያሳልፉ ምኞታችን ነው!

🎂 🍰 🧁

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.  የ7ተኛው...
27/05/2026

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሠረት:-
- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GAMO TIMS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share