አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ስፖርት መምሪያ

አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ስፖርት መምሪያ we promote culture,sport

ታዋቂዎቹ የMMA ቦክስ ፋይቲንግ ተወዳዳሪዎች ሀገረሰላም አርባ (ቦንጆ) እና ቢንያም ሽብሬ አርባምንጭ ከተማ ገቡአርባምንጭ ፥መስከረም 13/2019 ታዋቂዎቹ የMMA (Mixed Martial A...
23/09/2026

ታዋቂዎቹ የMMA ቦክስ ፋይቲንግ ተወዳዳሪዎች ሀገረሰላም አርባ (ቦንጆ) እና ቢንያም ሽብሬ አርባምንጭ ከተማ ገቡ

አርባምንጭ ፥መስከረም 13/2019

ታዋቂዎቹ የMMA (Mixed Martial Arts) ቦክስ ፋይቲንግ ተወዳዳሪዎች ሀገረሰላም አርባ (ቦንጆ) እና ቢንያም ሽብሬ አርባምንጭ ከተማ የገቡ ሲሆን፣ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ተወዳዳሪዎቹ አርባምንጭ ከተማ ሲደርሱ የጋሞ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፣ የአርባምንጭ ከተማ ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎችና አባቶች በተገኙበት ደማቅና ባህላዊ የአቀባበል ስነ-ስርዓት ተደርጎላቸዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የዞኑና የከተማው አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ስፖርተኞቹ ለደረሱበት የስፖርት ደረጃና ላስመዘገቡት ውጤት ያላቸውን አድናቆትና የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ዮ ማስቃላ …ከዘመን ዘመን መሸጋግርን በማስመልከት ችቦ የማብራት ስነስረዓት ተካሂዷል
22/09/2026

ዮ ማስቃላ …ከዘመን ዘመን መሸጋግርን በማስመልከት ችቦ የማብራት ስነስረዓት ተካሂዷል

ሶፌ—ሌላኛው የዮ ማስቃላ ውበት!"​የሶፌ ሥርዓት በጋሞ ባህል የመስቀል በዓል በሚከበርበት ወቅት የሚከናወን ድንቅ ባህላዊ እሴት ነው። በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በሚከ...
22/09/2026

ሶፌ—ሌላኛው የዮ ማስቃላ ውበት!"
​የሶፌ ሥርዓት በጋሞ ባህል የመስቀል በዓል በሚከበርበት ወቅት የሚከናወን ድንቅ ባህላዊ እሴት ነው።

በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በሚከበረው የዮ ማስቃላ በዓል ላይ በዓመቱ ያገቡ አዲስ ሙሽሮች ጸጉራቸውን ቅቤ ተቀብተው፣ በባህላዊ አልባሳት አምረውና ተውበው ጋብቻቸውን ሕጋዊ የሚያደርጉበትን ይህንኑ የሶፌ ሥርዓት ለታዳሚው በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ዮዮ ማስቃላ!" ታላቁን የጋሞ ዮ ማስቃላ በዓል በድምቀት ለማክበር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የመጡ የታደሚዎች ማዕበል ወደ አርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በመጎረፍ ላይ ይገኛል።
22/09/2026

ዮዮ ማስቃላ!" ታላቁን የጋሞ ዮ ማስቃላ በዓል በድምቀት ለማክበር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የመጡ የታደሚዎች ማዕበል ወደ አርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በመጎረፍ ላይ ይገኛል።

“ዮ…… ጋሞ ማስቃላ!” የጋሞ መስቃላ ክብረ በዓልን በደማቅ መልኩ ለማክበር በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የበዓሉ ዝግጅት ተጠናቋል።📣 ነገ ከማለዳ ጀምሮ፣በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታ...
21/09/2026

“ዮ…… ጋሞ ማስቃላ!”

የጋሞ መስቃላ ክብረ በዓልን በደማቅ መልኩ ለማክበር በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የበዓሉ ዝግጅት ተጠናቋል።

📣 ነገ ከማለዳ ጀምሮ፣
በአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እንገናኝ!

🌿 ባህላችንን እናክብር፣
ትውፊታችንን እናስቀጥል!

🔥 ዮ…… ጋሞ መስቃላ! 🔥

ጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን

"የዱቡሻ ስርዓት የአለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የተጀመረው ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛል"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መስከረም 11/2029 ዓ.ም ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ...
21/09/2026

"የዱቡሻ ስርዓት የአለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የተጀመረው ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛል"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

መስከረም 11/2029 ዓ.ም

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በጋሞ ህዝብ የ 'ዮ ማስቃላ' የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ፥ የዘመን መለወጫ በዓል ዋዘማ የተካሄደው የባህልና የቋንቋ ሲምፖዝየም በስኬት ተጠናቋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሲምፖዝየሙ ማጠቃለያ እንደ ዮ ማስቃላ ያሉ በዓሎች ባህልና ቋንቋን ከመጠበቅና ከማሳደግ ባለፈ፥ የሰላም፥ የአንድነት፥ የኅብረት እና የትብብር እሴቶች ተጠቅሞ የልማት ትብብሮችን በማጠናከር የብልጽግና ጉዟችንን ማጽናት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

"ዮ ማስቃላ ለዘላቂ ሰላማችንና እና ልማታችን" በሚል ሀሳብ ለ 17ኛ ጊዜ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው የጋሞ፣ የዘይሴ እና የጊዲቾ የባህል ተቋም ለማደራጀት የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ እና የዞን አስተዳድር በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የጋሞ የእርቅና የአስተዳደር ስረዓት የሆነውን ዱቡሻን በቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመረው ስራ የተለያዩ መንገዶችን በመሻገር ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ቅርሱን በማስመዝገብ ለአለም ማስወቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻ ኢትዮጵያ አንድ ሆና የማንሰራራት ዘመና ላይ መሆኗን ገልፀው የክልላችንን ብሎም የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ አንድነት እና ፍቅርን መርህ በማድረግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዛሬው «ዮ ማስቃላ» የጋሞ ሸማኔዎች የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ላይ ሥዕልን በሽመና ጥበብ ድርና ማግን አዋቅረው ያቀረቡበትን አውደ ርዕይም ተጎብኝቷል

በተጨማሪ " የጋሞ ዞን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየሙ ላይ በድምቀት ተመርቋል።

‎"Yoo Masqalay Polo gakkiza saroteththasinne dichchas" giza kaaran Woganne Doona simpozeemey Arba Minc'e kataman poletet...
21/09/2026

‎"Yoo Masqalay Polo gakkiza saroteththasinne dichchas" giza kaaran Woganne Doona simpozeemey Arba Minc'e kataman poleteththan de'ees.
‎
‎Arba Minc'e: Gustama 11 /2019 M.L
‎
‎Maaraza bolla dugeha Tophphiya kilile ayso aawa Daanna Kabbada Xilahuna gujjidi kilileza dhoqqa kawo ootho kaappota, Gaammo zoonenne Arba Minc'e katama ayso dhoqqa kawo ootho kaappota, Gaammo zoone enc'ereta kawo ootho kaappota, ammano aawata, dere c'imata, dere satanne shoobbettida imaththati beettida.
Gaammo Telebizhiney erisida mala

"የዮ ማስቃላ እሴቶች ለዘላቂ ሰላማችንና ብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል በጋሞ ዞንና በአርባ ምንጭ ከተማ የሲምፖዚየምና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል​አርባ ምንጭ ፦ መስከረም 11/2018...
21/09/2026

"የዮ ማስቃላ እሴቶች ለዘላቂ ሰላማችንና ብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል በጋሞ ዞንና በአርባ ምንጭ ከተማ የሲምፖዚየምና የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል

​አርባ ምንጭ ፦ መስከረም 11/2018 ዓ.ም

​በነገው ዕለት በድምቀት የሚከበረውን የጋሞ ሕዝቦች የዘመን መለወጫ "ዮ ማስቃላ" በዓልን አስመልክቶ፣ በጋሞ ዞንና በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት "የዮ ማስቃላ እሴቶች ለዘላቂ ሰላማችንና ብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል የሲምፖዚየምና የፓናል ውይይት መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

​በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር፣ የወረዳና የከተማ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

​ተሳታፊዎቹ ከፓናል ውይይቱ አስቀድመው ለበዓሉ የተዘጋጁ የተለያዩ ኤግዚቢሽኖችንና የባህል ትርኢቶችን ተዘዋውረው ምልከታ ያደረጉ ሲሆን፣ የዘንድሮው የ"ዮ ማስቃላ" በዓል አከባበር ከፓናል ውይይቱ በተጨማሪ በነዚህና በሌሎች የተለያዩ ህዝባዊ ኩነቶች ታጅቦ በድምቀት መከበሩን የሚቀጥል ይሆናል።

በስመኝ አክሊሉ

“የአዲስ ዓመት ስጦታችን ለስታዲየማችን” በሚል መሪ ቃል የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ፣  የጋሞ ህዝቦች  የዘመን መለወጫ በዓል ታላቁ «ዮ ... ማስቃላ»ን መ...
19/09/2026

“የአዲስ ዓመት ስጦታችን ለስታዲየማችን” በሚል መሪ ቃል የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ፣ የጋሞ ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓል ታላቁ «ዮ ... ማስቃላ»ን መነሻ በማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ Challenge እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

አርባ ምንጭ፦ መስከረም 9/2019 ዓ/ም

የጋሞ ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓል የሆነውን «ዮ ... ማስቃላ»ን ምክንያት በማድረግ፣ ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሚሆን ህዝባዊ የገቢ ማሰባሰቢያ «የዮ ... ማስቃላ! Challenge» ተሳትፎ ጥሪ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ በይፋ ቀርቧል።

«የአዲስ ዓመት ስጦታችን ለስታድየማችን» በሚል መሪ ቃል የተበሰረው ይህ ንቅናቄ፤ ስፖርት ወዳዱ ማህበረሰብ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የዞኑ ህዝብ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የጋሞ ተወላጆችና ወዳጆች በዓሉን ሲያከብሩ የስፖርት ህዳሴው ፕሮጀክት ለአርባ ምንጭ አለም አቀፍ ስታዲየም የሚሆን ስጦታ በማበርከት አሻራቸውን እንዲያኖሩ የቀረበ ታላቅ ጥሪ መሆኑን ዶ/ር መስፍን መንዛ ገልፀዋል።

የአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን በስኬት ለማጠናቀቅና ከተማዋ ደረጃቸውን የጠበቁ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ውድድሮችን እንድታስተናግድ ለማስቻል የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ፣ ህዝቡ በዓሉን ሲያከብር ከሚያወጣው የደስታ ወጪ ጎን ለጎን ለአካባቢው ዘላቂ የልማት ውርስ የሚሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ደ/ሩ አሳስበዋል::

በንቅናቄው መሠረት ማንኛውም በጎ ፈቃደኛና ስፖርት ወዳድ ዜጋ የበኩሉን የአዲስ ዓመት ስጦታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር **1000640532851** ገቢ በማድረግ የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አካል መሆን እንደሚችል ተገልጿል።

የጋሞ ህዝብ ያለውን የቆየ የመረዳዳት፣ የአብሮነትና የማህበረሰብ ልማት እሴት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ፤ የመላው አካባቢው ነዋሪዎች፣ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትና የስፖርት ቤተሰቡ ይህንን ጥሪ በመቀበል የበኩላቸውን አሻራ በማስቀመጥ የስታዲየሙን ግንባታ እውን ለማድረግ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ» የቱሪዝም እና የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ወደ ቱሪዝም ከተማ አርባ ምንጭ ገቡአርባ ምንጭ፣ (መስከረም 6/ 2019 ዓ.ም - ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከቅሩንፉድ ዲጂታል...
17/09/2026

ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ» የቱሪዝም እና የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ወደ ቱሪዝም ከተማ አርባ ምንጭ ገቡ
አርባ ምንጭ፣ (መስከረም 6/ 2019 ዓ.ም -
ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከቅሩንፉድ ዲጂታል ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ብሔራዊ የቱሪዝም እና የቁንጅና ውድድር «ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ» ተወዳዳሪዎች ለአስቻይ የጉብኝትና የይዘት ፈጠራ መርሃ-ግብር አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል።
ተወዳዳሪዎቹ ከተማዋ ሲደርሱ በአርባ ምንጭ ከተማ ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መተኪያ አበበ እና በባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ ደንበላ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የውድድሩ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ «ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ» ከመደበኛ የቁንጅና ውድድሮች በተለየ መልኩ የሀገሪቱን ገጽታ፣ ባህል እና የቱሪዝም ሀብቶች የሚያስተዋውቁ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት ያለመ ዘመናዊ «ሪያሊቲ ሾው (Reality Show)» ውድድር ነው ብለዋል።
በመላ ሀገሪቱ ከተመዘገቡ 700 ተወዳዳሪዎች መካከል ማጣሪያዎችን አልፈው ወደ 60 የወረዱት ተወዳዳሪዎች፣ በየክልሎቹ በመዘዋወር የፈጠራ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን በሶሻል ሚዲያ እና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ለህዝብ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ተወዳዳሪዎቹ በአርባ ምንጭ ቆይታቸው የተሰጣቸውን የፈጠራ ፈተናዎች (Challenges) ለመወጣት የዶርዜ መንደር፣ የአርባ ምንጮችን፣ የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን፣ የአዞ እርባታን እና የጫሞና አባያ ሀይቆችን ይጎበኛሉ።
በእነዚህ መዳረሻዎችና ሌሎች ቱሪዝም መስህቦች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴና የሚያዘጋጁትን ይዘት በቲክቶክ እና በአርትስ ቴሌቪዥን (Arts TV) በማስተላለፍ የከተማዋን የቱሪዝም መስህቦች የሚያስተዋውቁ ይሆናል።
ከአርባ ምንጭ የጉብኝት መርሃ-ግብር በኋላ ተወዳዳሪዎቹ ወደ 20 ዝቅ የሚሉ ሲሆን፣ የመጨረሻው የፍፃሜ ውድድር በመስከረም 29 ቀን በስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል See less

Address

Arbaminch
Arba Mintch
230305

Telephone

+251960490301

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ስፖርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share