19/04/2023
"የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጫምባላላ በዓል አቃፊነቱን፣ባህላዊ እሴቱንና ትውፊታዊ ድምቀቱን በጠበቀ መልኩ እየተከበረ ይዘልቃል:-"አቶ አብርሃም ማርሻሎ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ
በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
አቶ አብርሃም ማርሻሎ ለመላው ብሔሩ ተወላጆች፣ለመላው የክልሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት የሲዳማ ብሔር ጠበብት አባቶቻችን በተፈጥሮ ከፈጣሪያቸው ባገኙት እውቀትና ጥበብ በሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ በዓል የሆነውን ፊቼ ጫምባላን ቀናቶችንና ወራቶችን በመቁጠር የሚደርሱበት ድንቅ የዘመን አቆጣጠር ስርዓት ነው።
ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ጠበብት አባቶቻችን ከቅድመ በዓሉ አስቀድመው በመፆምና ወደ ፈጣሪያቸው የፀሎት ምልጃን በማቅረብ ለሰው ልጆች፣ለሀገር መሪዎችና ለሁሉም ፍጥረታት ፈጣሪ ሰላምን፣ጤናንና ፍቅርን እንዲሰጥ የሚለምኑበት ባህላዊ ክዋነና እሴት ነው።
ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ ፍቅርን መተሳሰብን፣መቻቻልንና ይቅርታን የያዘ እንደመሆኑ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ የተራራቁ የሚቀራረቡበትና የተቀያየሙ ወገኖች ይቅር የሚባባሉበት የእርቅና የሰላም የፍቅር በዓልም እንደሆነ አቶ አብርሃም ተናግረዋል።
እኛ ኢትዮጵያውያን በባህሉም ሆነ በመንፈሳዊ ስርዓቶቻችን ለህዝቦች ሰላምን፣ፍቅርንና አብሮነትን ከፈጣሪ የሚንለምንና የሚንመኝ በመሆናችን በማናቸውም ምክንያቶች የሚፈጠሩ ግጭቶችንና አለመግባቶችን ተመካክረንና ተነጋግረን እየፈታን ታላቋን ኢትዮጵ እስከ ዛሬ አዝልቀናል። አሁን ላይ በሀገራችን ያለውም የሰላም አየር የሀገራችንን አንፃራዊ ሰላም ያሰፈነ በመንፈሳዊና ባህላዊ ትውፊቶቻችንና እሴት ጥረቶች የተገኘ ሲሆን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረውም ግጭት ረግቦ መላው ህዝባችን የትንሳኤ በዓልን ጨምሮ በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበውን ፊቼ ጫምባላላ በዓልን ከሁሉም የሃገራችን ክፍል በመሰባሰብ በጋራ የሚያከብርበት አጋጣሚ መፈጠሩ የዘንድሮውን የበዓሉ አከባበር ለየት ያደርገዋል።
ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ አስደማሚ እሴት ፣ታሪክ እና ወግ በመያዙ በዩኔስኮ መዝገብ ላይ በማይዳሰስ ቅርስነት በመስፈር ከብሔሩና ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ሀብትም በመሆን መመዝገብ ችሏል።
ፊቼ- ጫምባላላ የሲዳማን ህዝብ ታሪክ ፣ባህልና እሴት የሚገልፅ ቱባ ባህል ሲሆን ከአሮገዉ ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገሪያው ባህል የማንነቱ መገለጫና መድመቂያ ተደርጎ የሚወሰድ ውብና ሳቢ ባህላዊ ክዋኔ ነው።
በሲዳማ ብሎም በዓለም ዘንድ በጉጉት ለሚጠበቀው የፊቼ-ጫምባላላ በዓል እንኳን አደረሰን በማለት የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጫምባላላ በዓል ትውፊታዊ ድምቀቱን በጠበቀ መልኩ በትውልድ ቅብብሎሽ የዘለቀ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ድንቅ ባህላዊ እሴት ልንጠብቀውና ልንከባከበው ለቀጣይ ትውልድም በክብር ልናሻግረው ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም አቶ አብርሃም አክለውም እንዳሳሰቡት ፊቼ ጫምባላላ በዓል ህብረ-ብሄራዊነት፣አብሮነት፣ፍቅርና መቻቻል ልዪ መገለጫው በመሆኑ ለበዓሉ ድምቀት የሚገባውን ጥበቃ ክብካቤና ጥንቃቄ በማድረግ ሊናከብረው ይገባልም በማለት አሳስበለዋል።
# Ayidde Cambalaall!!
# በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን!!
# መልካም የፊቼ ጫምባላላ በዓል!!
# Fichee Jeejji Jeejji !!
በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት
ሚያዝያ 10-2015 ዓ.ም
ሀዋሳ