27/08/2025
የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጅ ብንሸልማቸውስ?!
የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስጀመሪያ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር (88 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር) ለቦንድ ግዥ ያወጡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ - የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አልአሙዲ!!
***
- የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ሽፋን የነበረው ቴሌቶን በሚሊኒየም አዳራሽ መካኼድ ጀመረ፣
በወቅቱ እጅግ ሪከርድ የተባለ የቴሌቶን ገቢም ተገኘ። ቃልም ተገባ። በዕለቱ ብቻ ከቴሌቶኑ ከ1 ቢሊዬን ብር በላይ ተገኘ። ተዓምር ተባለ።
ሼክ አል-አሙዲ በቴሌቶኑ መድረክ ነበሩ። ለህዳሴው ግድብ የሚገዙት የቦንድ መጠንም እየተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ሼክ አልአሙዲ ማይኩን ጨበጡ። "ይህን ቀን ካየሁ በኋላ ብሞትም አይቆጨኝም። ያለምንም ጥርጥር እንገነበዋለን። ዛሬ ቦንድ ሳይሆን በቴሌቶኑ ቃል የተገባውም እስኪሰበሰብ 1 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ልስጣችሁ እና ቶሎ ስራውን ጀምሩ።.... የጎደለ ነገርም ካለ አለሁ" ብለው ቃል ገቡ። በወቅቱ 1.5 ቢሊዬን ብር ወደ 88 ሚልየን ዶላር ይገመት ነበር። የእሳቸው ቆፍጣና ውሳኔ ደስታና መነቃቃትን መፍጠርም ቻለ።
ሼክ አሊ አል-አሙዲ በአጠቃላይ ከ10 ቢሊዬን ብር በላይ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዥ ፈፅመዋል። ይህም በደማቅ አሻራ ወርቃማ ታሪክ ባለቤት ያደርጋቸዋል።
እንዲህ ያለ ሀገር ወዳድ ማግኘት እድለኝነት ነው። ሀገር ድህነትን ለማሸነፍ በምትሻው ሰዓት በተግባር ጀግና ሆኖ የተገኘ ሀገር ወዳድ!!!
የኢትዮጵያ መንግሥት የክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲንን በግድቡ ምረቃ ወቅት ብሔራዊ ጀግና አድርጎ ዕውቅና ሊሰጣቸውና ሊሸልማቸው ይገባል እላለሁ። እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Source: Abd እና እሱባለው ካሳ