31/05/2026
በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊው በታጣቂዎች ተገደሉ
በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ያረጋል በታጣቂዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።
ወረዳው ባወጣው አጭር መግለጫ አቶ ተመስገን "የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት በስራ ተጠምደው ለእረፍት ትናንት ማታ ወደ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ በሰርጎ ገብ ታጣቂዎች ጥይት ተመተው ገና በ40 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን" አሳውቋል።
"አቶ ተመስገን እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር ወረዳውን በልማት መስክ ለማሰጠቀም፣ የወረዳው ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ አመራር" እንደነበሩ በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።
መግለጫው የገዳዮቹን ማንነት "ሰርጎገብ" ከማለት ውጭ በግልፅ አልጠቀሰም።
የአመራሩ ስርዓተ ቀብር በአንጎት ወረዳ አሁን ተገኝ ከተማ በሚገኘው ተከስቴ ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት መፈፀሙ ተሰምቷል።
ምንጭ :- EthioTube
Hawassa City