12/05/2026
ኢንተርፕራይዛችን ከሲዳማ ክልል ውጪ በመውጣት ሰርቶ ያስመረቀው ፕሮጀክት
**************
ሲደማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በሲዳማ ክልል ውስጥ በሚሰራቸው ሥራዎች ብቻ ሳይወሰን ከክልሉ ወጭ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ ውሃና ሳቴሸን ፕሮጀክት በማማከር ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ/ም ለምረቃ አብቅቷል፡፡
ውጤታማ የነበረው የፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥር እና ከንትራት አስተዳደር ሥራችን ፕሮጀክቱ በላቀ ጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ሚና ተወጥቷል፡፡ ለዚህ ጥረት ውጤት የፌደራል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጌዲኦ ዞን መስተዳድር እንዲሁም ከከተማ አስተዳሩና ከነዋሪው ከፍተኛ ምስጋናና የሞራል ስንቅ አግኝተናል፡፡
ተቋማችን ከተመሠረተ አጭር ዕድሜ ብቻ ያስቆጠረ ቢሆንም ወደ አጎራባች ክልሎች ወጥቶ የመወዳደር፣ ገቢ የመሰብሰብ እና የመፈጸም አቅም መፍጠር ችሏል፡፡ የተቋማችን ጠንካራ የመፈጸም አቅም የክልላችን መንግሥት አፈጻጸም ጥንካሬ ነጻብራቅ ምስል ነው፡፡ ጠንካራ ክልል ጠንካራ ተቋማትን ይወልዳል፡፡