Abirham Getahun Tesema

Abirham Getahun Tesema abirham from tilili

18/01/2026

ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለዉ ሰዉ ዕውቀት ቢኖረዉም ጥበብ የለዉም! ምክንያቱም የጥበብ መጀመሪያ
እግዚአብሔርን መፍራት ነዉ
ምሳሌ 1:7

05/01/2026

ዝቅተኛው የአንድ አርሶ አደር የይዞታ ማሳ ስፋት 0.25 ሄክታር ስለመሆኑ የፌደራሉም ሆነ የአማራ ክልል ገጠር መሬት አስ/አጠ/አዋጅ ደንግጓል።
0.25 ሄክታር ማለት፣ በሳይንሳዊ የቅየሳ ልኬታ 2500 ካሬ ሜትር ነው።
ስጦታ ተቀባዩ ከስጦታ ሰጩ ሊቀበልና የይዞታ መብት ሊተላለፍለት የሚገባ የይዞታ መጠን ዝቅተኛውን የማሳ መጠን 0.25 ሄክታር ወይም 2500 ካሬ ሜትር ማሚላት ግዴታ ነው ::
በመሆኑም የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ አረንጓዴ ደብተር ወይም በካዳስተር ልኬታ በካርታ የተደገፈ ካርታ ሊሰጠው የሚገባም ይህንን የይዞታ ጣራያ ሊያሟላም የሚገባው ስለመሆኑ ስንቶቻችን ግንዛቤው አለን?
በልዩ ምክንያት አሳማኝ ተብለው በዝርዝር ከተቀመጡት ልዩ ምክንያቶች በስተቀር 0.25 ሄ/ር ያልሞላ የማሳ መጠን ለሚሰጥ የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ወይም ካርታ የተሳሳተ ማስረጃም ተደርጎ ይወሰዳል።
የተሳሳተ ማስረጃ መስጠት ደግሞ ከበድ ያለ የወንጀልና የፍትሐብሄር ተጠያቂነት ያለው መሆኑን በአዲሱ የገጠ/መ/አስ/አጠ/ አዋጅ በዝርዝር መቀጮ ተደንግጓል!!
በመሆኑም በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ምንጭ የሌላቸው አሉባልታዎችን በጥንቃቄ መመርመር የሚገባ መሆኑን የአበክመ መሬት ቢሮ ያሳስባል።
በቀጣይም ዝክረ ህጉ ታትሞ ለሰፊው ህዝብ እስኪደርስ፣ ደንብና መመሪያዎች እስኪደርሱ፣ በየ ደረጃው ላለው የመሬት ተቋምና ለአጋር ባለ ድርሻ አካላት ስልጠናና የግንዛቤ ፈጠራ እስከሚሰራ
የሚፈልጉትን መረጃም በፈለጉት ጊዜ እንዲያገኙ ተግተን አጫጭር መረጃዎችን በማጋራት በትጋት የመረጃ ምንጭ ሆነን የምናገለግላችሁ ይሆናል።

29/12/2025

Surveying ማለት ምን ማለት ነው?
🏫🏛🏤🏫🏛🏤
surveying ማለት፡ መሬትን መመዛዘን፣ መለካት እና የድንበር መጠን መወሰን የሚያደርገው ሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ ሂደት ነው።
✍️በመንገድ ሥራ፣ ቤት ግንባታ፣ መሬት መመያዣ፣ ንድፍ እና GIS ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው።
🎯 ዋና ዓላማዎቹ
✍️የመሬት ድንበር እና መጠን መወሰን
✍️ለኮንስትራክሽን ንድፍ መዘጋጀት
✍️መሬት ክብደት እና ከፍታ መመዝኘት (Topography)
✍️የመሬት ካርታ ማብራሪያ ሥራ
✍️የተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር
🏗️ የSurvey አይነቶች
1️⃣ Cadastral Survey (የድንበር መመዝኛ)
✅የመሬት መሬት መጠን
✅ድንበር ማረጋገጫ
✅የመሬት መብት መመዝኛ
2️⃣ Topographic Survey
✍️ከፍታ፣ ጎዳና፣ ተራራ እና ቀለም መገምት
✍️ለመንገድ እና ግንባታ አስፈላጊ
3️⃣ Engineering / Construction Survey
✅ቤት
✅የመስመር ቦታ ማስያ
✅Leveling እና Setting out
4️⃣ Geodetic Survey
ትልቅ አፍቃሪ ክልል
GPS / Satellite ቴክኖሎጂ
ሀገራዊ መሬት መመዝኛ
🛠️ ተጠቃሚ መሳሪያዎች
📌Measuring Tape
📌Level እና Staff
📌Total Station
📌GPS / GNSS
📌Theodolite
📌Drone (ለከፍታ ካርታ)
✅በኢንጂነሪንግ ውስጥ አስፈላጊነቱ
✍️የንድፍ ትክክለኛነት ያረጋግጣል
✍️የግንባታ ስራ ስህተት ይቀንሳል
✍️የመሬት ክስተት ግጭት ይከላከላል
✍️ለመንግሥት መሬት መመያዣ ይረዳል
💡 ተግባራዊ ምሳሌዎች
✅የመንገድ ንድፍ
✅የከተማ አቀማመጥ (Urban Planning)
✅የእርሻ መሬት መመዝኛ
✅የእርሻ አካባቢ ካርታ ማዘጋጀት

አዲሱ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አዋጅ  ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?! **************************ስጦታን በተመለከተ* የገጠር መሬት ባለይዞታ ይዞታውን በቤ...
27/12/2025

አዲሱ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አዋጅ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?!
*************************
*ስጦታን በተመለከተ*

የገጠር መሬት ባለይዞታ ይዞታውን በቤተሰብ ሕጉ የስጋ ዘመዳሞች እንዲሁም በውል በተደገፈ የይጦረኛል ስምምነት ውል ለገባለት ማንኛውም ሰው በስጦታ ማስተላለፍ ይችላል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለይዞታዉ በዉል በተደገፈ የይጦረኛል ስምምነት ዉል ለገባለት ለማንኛዉም ሰዉ በስጦታ ማስተላለፍ መብቱ ነው፡፡
ነገር ግን ስጦታ ሲደረግ አካል ጉዳተኞችን እና እድሜያቸዉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን የሚጎዳ ከሆነ በሕግ ፊት ተፈፃሚነት አይኖረዉም፡፡

*የዉርስ መብትን በተመለከተ*

የገጠር መሬት ባለይዞታ ይዞታውን በፍትሐ ብሔር ሕጉ የውርስ ድንጋጌዎች መሰረት ለማንኛውም ሰው ማውረስ ይችላል፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው ገደብ ማለትም የገጠር መሬት ለመውረስ በግብርና ስራ መሰማራት ግዴታ ነው የሚለው ከግምት ውስጥ ሳይገባ አንድ ባለይዞታ መብቱን በየደረጃው ለልጅ፡ ለእናት አባት፡ ለአያት፡ ለቅድመ አያት ማውረስ ይችላል፡፡

በዚህ አዋጅ የመንግስት ሰራተኛ የገጠር መሬት መውረስ ይችላል፡፡ የይዞታ መብትን ለመውረስ የሚከለክሉ አሳሪ ገደቦች በዚህ አዋጅ መሰረት ተነስተዋል፡፡ ባለይዞታው በኑዛዜ ሳያወርስ በሞተ ጊዜ ወይም ኑዛዜው ፈራሽ ከሆነ የፍትሐ ብሔር ሕጉ ያለ ኑዛዜ የውርስ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ሆኖም በኑዛዜ የማስተላለፉ ተግባር አካለ-መጠን ያልደረሰውን የተናዛዡን ልጅ ከሕጋዊ ወራሽነት መብቱ የሚነቅል ወይም የተናዛዡን የትዳር ጓደኛ ሕጋዊ መብት የሚጎዳ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በሕግ ፊት የሚጸና አይሆንም፡፡ባለይዞታው የይዞታና ለተወሰነ ጊዜ ደግሞ የመጠቀም መብቶቹን ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች በኑዛዜ ሊያስተላልፍ ይችላል።

የኑዛዜ አደራረግ “በፍትሀ-ብሄር” ሕግ ውስጥ እንደተደነገገው ኑዛዜ የሚሰጥባቸውን መስፈርቶች ማሟላት የሚጠበቅበት ሆኖ በግልፅ ኑዛዜ የሚደረግ ኑዛዜ ግን አግባብ ላለው የወረዳ ወይም የከተማ መሬት ጽህፈት ቤት ቀርቦ መመዝገብ አለበት፡፡
አዋጁም ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ የገጠር መሬት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም በይዞታ የመጠቀም መብትን ለብድር ዋስትና ከማስያዝ ጋር ተያይዞ የገጠር መሬት ባለይዞታ የመጠቀም መብቱን ለሕጋዊ የፋይናንስ ተቋም ለብድር ዋስትና አድርጎ ማስያዝ እንደሚችል መብት ይሰጣል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት ማኅበረሰቡን የሚጠቅም ሕግ በማጽደቁ ምስጋና ይገባዋል።
የክልሉ የመሬት ቢሮ ይህ አዋጅ ለፍሬ እንዲበቃና የማኅበረሰቡን መብትና ጥቅም እንዲያካትት በረቂቅ ሂደት ባለይዞታውን ጨምሮ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በስፋት ረጂም ጊዜ ወስዶ አወያይቷል።
ይህም ዘመናዊ የሕግ አወጣጥ ስርዓቱን የተከተለ ነው ማለት ይቻላል።

አፈጻጸሙ ደግሞ በቅርቡ በክልል ምክር ቤት በጸደቀው በአብክመ በተሻሻለው የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ እና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ በተቋቋመው መሬት ቢሮ እና በተዋረድ ባሉ የመሬት አስተዳደር ተቋማት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

የአየር ፎቶ ማለት ምን ማለት ነው ?                የአየር ፎቶ ማለት ለመስመራዊም ሆነ ካርታ ስራን በፎቶግራሜትሪ አሰራር ለማዘጋጀት በግብዓትነት የሚጠቅም ከአየር ላይ በአየር ፎቶ...
27/12/2025

የአየር ፎቶ ማለት ምን ማለት ነው ?

የአየር ፎቶ ማለት ለመስመራዊም ሆነ ካርታ ስራን በፎቶግራሜትሪ አሰራር ለማዘጋጀት በግብዓትነት የሚጠቅም ከአየር ላይ በአየር ፎቶ ካሜራ የተነሳ ምድራዊ ገጽታን የሚወክል ምስል ነው፡፡

የአየር ፎቶ መረጃ ጥቅሙ ምንድ ነው?
የአየር ፎቶ መረጃን በመጠቀም ልኬት ለማካሄድ፡-

ማንኛውም ቀያሽ የምድር ቅየሳ መሳሪያ የሆኑትን እንደ ሳውዝ፣ ሶኪያ፣ ለይካ፣ ቶታል እቴሽን የምንላቸውን ሳይጠቀም በፎቶግራሜትሪ ወይም ሪሞት ሴንሲንግ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ተመስርቶ የንድፍ ካርታ ትክክለኛነቱ በተረጋገጠ የካዳስተር መሰረታዊ ካርታ በመጠቀም የካዳስተር ቅየሳ ልኬቱን ማካሄድ ይችላል፡፡

Address

Bahir Dar
055689

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abirham Getahun Tesema posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abirham Getahun Tesema:

Shortcuts

Share