Nadan Initiatives ናዳን የልህቀት ማዕከል

Nadan Initiatives ናዳን የልህቀት ማዕከል በጋራ የማይበገር ማህበረሰብን እንገነባለን! Together we build resilient community!

Nadan Initiatives PLC (ናዳን የልህቀት ማዕከል) is a dynamic research, innovation, and development company driven by a powerful mission: to create, develop, and scale-up soft assets and intangible resources for individuals, organizations, communities, and nations worldwide. We empower individuals and societies through impactful psychosocial well-being and mental health solutions focused on these intangible resources, leading to change, excellence, and development. Nadan Initiatives PLC was established with multi-disciplinary team comprising energetic physicians, psychiatrists, psychologists, nurses, public health specialists, data analysts, sociologists, economists and social workers. Nadan Initiatives PLC envisions being Africa’s leading institute of research, development, innovation and adaptation in community development, psychosocial and health fields, and becoming a center of excellence for initiatives in the industry.
ናዳን ማን ነው?
ናዳን ማህበረሰባቸውን፤ ሀገራቸውን ብሎም ዓለምን በአዎንታዊ መልኩ ለማሻሻልና በሁለንተና ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር እሳቤው፣ ተነሳሽነቱና ቁርጠኝነቱ ባላቸው በተለያየ የሙያ ስብጥርና የስራ ዘርፍ ውስጥ ብዙ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ለማህበረሰብ ለውጥ ያቋቋሙት የሁለንተናዊ ልማት፣ ጥናትና ምርምር ተቋም ነው፡፡
ናዳን ለግለሰቦችና ለተቋማት ልህቀትና የማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ ማበልጸጊያ እንዲሆን የሰዎችን ውስጣዊ አቅም በማሳደግ በሁለንተናዊ ህይወታቸው ማለትም በማህበራዊ፣ ስነልቦናዊ፣ መንፈሳዊ፣ አእምሯዊና አካላዊ ማንነታቸው ጤናማ እንዲሆኑ ለመርዳት፣ ተቋማትም የተቋቋሙለትን ዓላማ እንዲያሳኩ የሚረዷቸውን የእድገትና ልህቀት ጥበቦች ለማበልጸግ፤ ለሀገርና አህጉር አቀፍ እድገት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የተመሰረተ የማህበራዊና የጤና ጉዳዮች ጥናት፣ ምርምር፣ ልማት፣ ማማከርና የስልጠና አገልግሎቶች አቅራቢ የንግድ ድርጅት ነው።
The word 'NADAN' means Solution, New discovery, Innovative Methods in four different languages including Amharic.

አድዋ የታሪክ ድል፣ የነገው ራዕይ!ዛሬ መላው ኢትዮጵያውያን እና ጥቁር ሕዝቦች 130ኛውን የአድዋ ድል በዓል እናከብራለን። አድዋ የወታደራዊ ድል ብቻ ሳይሆን የጽናት፣ የትብብር እና የጥቁር ...
02/03/2026

አድዋ የታሪክ ድል፣ የነገው ራዕይ!

ዛሬ መላው ኢትዮጵያውያን እና ጥቁር ሕዝቦች 130ኛውን የአድዋ ድል በዓል እናከብራለን። አድዋ የወታደራዊ ድል ብቻ ሳይሆን የጽናት፣ የትብብር እና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ምልክት ነው። የእንችላለን፣ የይቻላል፣ የብቃት ማረጋገጫ ዓለማቀፍ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ የታተመ የማይጠፋ፣ የማይደበዝዝ ህልው ሰነድ፣ ቋሚ ህልው ሀውልት ነው።

በናዳን የልህቀት ማዕከል (Nadan Initiatives)፣ የአድዋ ድል ለተልዕኮአችን መሰረት እና መመሪያ ነው። አባቶቻችን ቁርጠኝነትን ወደ ነፃነት እንደቀየሩት ሁሉ፣ እኛም በአመራር ልማት፣ በፈጠራ፣ በምርምር እና ሁሉን አቀፍ ዕድገት የሚያስገኙ ስልቶችንና መፍትሔዎችን በማምጣት ግለሰቦችን፣ ተቋማትን እና ማህበረሰቦችን ለማገዝና ወደዘላቂ ለውጥ እንዲሄዱ ለመርዳት ያለማቋረጥ እንድንበረታ ያነሳሳናል - አድዋ። አድዋ የሚያስታውሰን ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው አእምሮ ሲታነጽ (በጽናትና በአይበገሬነት፣ በውስጣዊ የላቀ የአሸናፊነት ወኔ፣ ለራስ በሚሰጥ ትልቅ ዋጋ)፣ ሥርዓቶች ሲጠናከሩ (መናበብ ሲኖር፣ አነዱ ሰው ባይኖር ሌላው ያለማጓደል እንዲያስቀጥል፣ የወደፊቱን ትልቅ ራዕይ ለማሳካት ታሪክን፣ አሁን ያለን ሀብትና በዙሪያ ያሉ ዕድሎችን የሚጠቀምና ስጋቶችን ቀድሞ የሚከላከል የተሰናሰለ ስርዓት ሲኖር) እና ሰዎች በዓላማ ዙሪያ በጋራ ሲቆሙ መሆኑን ነው።

🎯 ስትራቴጂካዊ አመራር

አድዋ የታላላቅ መሪዎች ጥበብ የታየበት ቦታ ነው። እኛም በናዳን፣ ተቋማት እና መሪዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዘመን የሚመጥን ሁኔታዎችን ያገናዘበ ስትራቴጂካዊ ብቃት እንዲኖራቸው እንሰራለን።

🤝 ተቋማዊ አንድነት

የአድዋ ድል የተገኘው መላው ሕዝብ በአንድ አላማ ስር በመሰለፉ ነው። ናዳን በድርጅቶች ውስጥ የአሰራር እና የአመራር አሰላለፍን (Alignment) በማስተካከል ውጤታማነትን ለመጨመር ይተጋል።

🚀 የማይቻልን የማድረግ ጽናት (Resilience)

አይቻልም የተባለውን በአለም ፊት የቻለች ሀገር ልጆች ነን። በናዳን በኩል የምንሰጣቸው የላቁ መፍትሔዎች፣ ስልጠናዎች እና የአማካሪነት አገልግሎቶች፣ ተቋማትና ግለሰቦች ከተግዳሮቶቻቸው አልፈው አሸናፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በተረጋገጡ መንገዶች ያግዛሉ።

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

At Nadan Initiatives, Adwa deeply informs our mission. Just as our forefathers transformed determination into freedom, we work to transform people, institutions, and communities through leadership development, innovation, mental resilience, and inclusive growth. Adwa reminds us that sustainable transformation is born when minds are empowered, systems are strengthened, and people act together with purpose.

As we honor this historic legacy, we recommit ourselves to building a future shaped by capable leaders, resilient communities, and bold action for Ethiopia and beyond.

Adwa lives on in every act of courage, learning, and transformation.
Activate to view larger image,
No alternative text description for this image

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።..መልካም በዓል!
07/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
..
መልካም በዓል!

Address

Fasilo Sub City, Kebele 04, Lemlemitu Bahrdar Market Center, 4th Floor
Bahir Dar
6000

Telephone

+251927958822

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nadan Initiatives ናዳን የልህቀት ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nadan Initiatives ናዳን የልህቀት ማዕከል:

Shortcuts

Share