Mekdes Abebaw

Mekdes Abebaw To become financial freedom!

12/02/2023

ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ ተስፋ አድርግ።ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው!ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው ። ሕይወትህ መከራ ችግር ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን።በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው።በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ስራ በደስታም ኑር ።
#ሜሎሪና

11/02/2023

ቀንህን የሚያሳምረው ወይ የሚያበላሸው የምትሰማው ዜና፣ የሰዎች ሁኔታ ወይ የአየር ሁኔታው ከሆነ በቃ የስሜትህን ሪሞት ለሌሎች አስረክበሀል።
ባንተ ስሜት የሚያዙት እነሱ ናቸው፤ ከፍ ዝቅ እያረጉ አንዴ የሚያስደስቱህ አንዴ የሚያስከፉህ እነሱ ናቸው። ወዳጄ የስሜትህን ሪሞት ማስመለስ አለብህ!

ሲፈልግህ ብቻ ከሚያስታውስህ  ባገኘህ አጋጣሚ ስለድክመትህ ብቻ የሚያወራልህ  አንተን ከራሱ ጋ  ከሚያወዳድርህ  የሌሎችን ሚስጥር ለ አንተ ከሚነግርህ ስለሰወች መጥፎ ነገር ከሚያወራህ በችግር...
15/10/2022

ሲፈልግህ ብቻ ከሚያስታውስህ ባገኘህ አጋጣሚ ስለድክመትህ ብቻ የሚያወራልህ አንተን ከራሱ ጋ ከሚያወዳድርህ የሌሎችን ሚስጥር ለ አንተ ከሚነግርህ ስለሰወች መጥፎ ነገር ከሚያወራህ በችግርህ ጊዜ አብሮህ ከማይሆን ሰው ጋ ..
እራስክን አርቅ!!!

22/07/2022

👉 ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ , ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀት ይዘህ አትሄድም , በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ , በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ።indeed

(መርበብት )

22/07/2022

"Your success and happiness lies in you. Resolve to keep happy, and your joy and you shall form an invincible host against difficulties.” – Helen Keller

06/07/2022

👉“ወይ የሆንከውን ምሰል፤ አልያም የመሰልከውን ሁን”። አብዛኛውን ጊዜ የምንናገረውን አይደለንምና። የምንመስለው እና እውነተኛው ማንነታችን ክፍተት አለበት። ይህ ክፍተት የሌለበት አንድም ባይኖርም፤ እራስን እየፈተሹ መጓዙ ግን ክፍተቱን እያጠበበው ይሄዳል። ሰው ለፍጹምነት መጓዝ የለበትም፤ ፍጹም ንጹህ መሆን ለሰው የተሰጠ አይደለምና፤ በቆሸሹ ቁጥር መንጻት ግን ባህሪያችን ሊሆን ይገባዋል። የሆንነውን ለመምሰል፤ አልያም የመሰልነውን ለመሆን ሁሌም ወደውስጣችን ልናይ ይገባናል።

06/07/2022

አንድ ቀን ደስታ ቤቴ ይገባል ብለህ ደስታህን አትግፋ፣ ዛሬ ደስተኛ የምትሆንበት አንድ ነገር ይኖራል። የአሁኑን ደቂቃ በጥልቀት መመልከት ከቻልክ ሁል ጊዜም የሚያስደስት ነገር አታጣም ፡፡

06/07/2022

ሰው ማለት እኮ የትዝታውና የትውስታው ድምር ነው። ሕይወት የመርሳትና የማስታወስ ሚዛን ናት። መርሳት ያለብንን መርሳት ሲያቅተን ሕይወታችን ይመሳቀላል... ደግሞ ማስታወስ ያለብንን የሕይወት ልምዶች ጠቃሚ ሰዎችና ነገሮች ከረሳን ...የእኛነታችን መለያና የስብእናችን ድንበር ይጠፋና ሌላ ሰው እንሆናለን::

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekdes Abebaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share