27/08/2018
ውድ የባህር ዳር የባጃጂ አሽከርካሪዎች፤ የምንወዳቸው ወንድሞቻችን ወደቤታችንና ቤታቸው እየመጡልን ነው፡፡ ስለኛ የጮሁና የተንገላቱት እነ ሙሉቀን ተስፋውና የልሣነ ዐማራ ቡድኖች ሲመጡልን እንዴት ነው የምንቀበላቸው? ጀግናን የሚያውቅና የሚያከብር ጀግና ነው፡፡ እኛም የዘመናችንን ጀግኖች በክብር፣በፍቅርና በድል እንቀበላቸዋለን፡፡ ሁላችንም የባጃጅ አሽከርካሪዎች ጓደኞቻችንን እየያዝን በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ሠንደቃችንን በመያዝ እንገኝና በአማራነት ዝማሬ አጅበን ይዘናቸው እንመጣለን፡፡ የሚደርሱበትን ቀንና ሰአት እዚሁ የምንገልፀው ይሆናል፡፡