Melese terefe

Melese terefe this page very important all fridom & peace people

05/02/2023

"ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። የሙታንን መነሳት ተስፋ እናደርጋለን። የሚመጣውንም ህይወት ለዘለአለሙ አሜን!!!" መለሰ ኢትዮጵያ

05/02/2023
05/02/2023

ዋ ብልፅግና ያልታደልከው እኛም ጩሀን ነበር አንተም ማስመሰልክን ቀጠልክ ውጤቱን ጠብቅ ያልነቃህ ንቃ

ቤተ ክርስቲያን  ከፍቷት እኔ የት ልኖር
04/02/2023

ቤተ ክርስቲያን ከፍቷት እኔ የት ልኖር

31/01/2023

ኦ ር ቶ ዶ ክ ስ ሀ ገ ር ና ት

እሷን አትንኩብን

እንዲሁ ዝም ብዬ ሳስበው ይሔንን ባንዴራ  የኢፌዲሪ መንግስት አልፈለገውም  ስለዚህ ይህንን  ባንዲራ የፌደራል መንግስት ተብየው  የማይፈልገው  የህዝቡንም ድምፅ ጀሮ ዳባ ልበስ ካለ የክልል ...
31/01/2023

እንዲሁ ዝም ብዬ ሳስበው ይሔንን ባንዴራ የኢፌዲሪ መንግስት አልፈለገውም ስለዚህ ይህንን ባንዲራ የፌደራል መንግስት ተብየው የማይፈልገው የህዝቡንም ድምፅ ጀሮ ዳባ ልበስ ካለ የክልል ባንዲራ እንዲኖር ባልፈቅድም ባለ ጊዜዎች እስካሉ ድረስ ይሄንን ባንዲራ የአማራ ክልል መለያ ቢሆንስ ምን ነበር

23/01/2023

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

| መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-

1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።

2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

(ኢኦተቤ ቴቪ)
ብቸኛው ጋዜጠኛ

23/01/2023

ብልፅግና አሻጥርህ ግልጽ ነውና ሳንነሳ ተነስ በቃህ

23/01/2023
 #ባሕርዳር‼️*****ባሕር ዳር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ናት። በጣና ሀይቅ በስተደቡብ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ባህርዳር ከኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከአዲስ አበባ ከተማ በ565...
13/01/2023

#ባሕርዳር‼️
*****
ባሕር ዳር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ናት። በጣና ሀይቅ በስተደቡብ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ባህርዳር ከኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከአዲስ አበባ ከተማ በ565 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምሥራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡

ባሕርዳር በታላቁ ጣና ሀይቅና በአባይ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ፣ ለእንግዶችና ለጎብኝወች እጅግ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀይማኖታዊ ታሪካዊ የተፈጥሮና ሰውሰራሽ የቱሪስት መዳረሻ ቦታወች፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ሪዞርቶችና ሎጅዎች መገኛ እንዲሁም እንግዳ ተቀባይ የሆነ ህዝብ መኖሪያ በመሆኗ የኢትዮጵያ ሪቪዬራ በመባል ትታወቃለች፡፡

👉የባሕርዳር የተፈጥሮ ስጦታ ጣና ሀይቅ፦

የጣና ሀይቅ በኢትዮጵያ ትልቁ ነው። ሀይቁ ሀይቅ ብቻ ሳይሆን አባይ ወንዝ መነሻ የሆነ አስደናቂ የተፈጥሮ ስጦታ ነው ። የከተማዋና የጣና ሀይቅ ዳርቻወች ልምላሜ፣ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው የአእዋፍ ዝማሬዎች እና በጣና ሐይቅ ውስጥ የሚገማሸሩ ጎማሬዎችና የተለያዩ እንስሳት ትእይንት እይታዎች ማራኪ ናቸው።

ጣና በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ከሰኔ 1 ቀን እስከ ሰኔ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባኤውን ያካሄደውና የብዝኃ ሕይወት ጉዳይን የሚመረምረው ዓለም አቀፉ ምክር ቤት ጣና ሐይቅን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኒስኮ በያዘው ብዝኃ ህይወት ክምችት በቅርስነት መዝግቦታል።

ጣና በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይዟል።ገዳማቶች በ14ኛ ምእት ዓመት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ባመነኮሷቸው ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሠረቱ ናቸው።

👉ከገዳማቶች መካከል፦
✔️ደብረ ማርያም፣
✔️ክብራን ገብርኤል፣
✔️ዑራ ኪዳነምህረት፣
✔️መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ፣
✔️አቡነ በትረ ማርያም፣
✔️አዝዋ ማርያም፣
✔️ዳጋ ኢስጢፋኖስ፣
✔️ይጋንዳ ተለሃይማኖት፣
✔️ናርጋ ስላሴ፣
✔️ደብረ ሲና ማርያም፣
✔️ማንድባ መድኃኒዓለም፣
✔️ጣና ቂርቆስ፣
✔️ክርስቶስ ሳምራ ገዳም፣
✔️ራማ መድሕኒ ዓለም፣
✔️ኮታ ማርያም…እና ሌሎችም ገዳማቶች ይገኙበታል።

👉ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት፦
❶ አቡነ ታዴዎስ~ደብረ ማርያም መሥራች
❷ አቡነ ዘዮሐንስ~የክብራን እና የእንጦስ ገዳም መሥራች
❸ አቡነ በትረማርያም~የዘጌ ጊዮርጊስ መሥራች
➍ አቡነ ኂሩተ አምላክ~የዳጋ እስጢፋኖስ መሥራች
➎ አቡነ ኢሳይ~የመንዳባ መድኃኔዓለም መሥራች
❻ አቡነ ዘካርያስ~ደብረ ገሊላ መሥራች
❼ አቡነ ፍቁረዮሐንስ~ጣና ቂርቆስ መሥራች ናቸው።

👉ጣና ቂርቆስ፦

ጣና ቂርቆስ ታቦተ ጽዮን ለ800 ዓመታት ያረፈችበት፣ ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ የተቀበረበት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ወር ከ10 ቀናት የተቀመጠችበት ገዳም ነው። ቅዱስ ያሬድ ምልክት የሌለውን ድጓ የጻፈባትና መጽሐፉና መስቀሉ የሚገኝበት ገዳም ነው።

👉ዳጋ እስጢፋኖስ፦

ዳጋ እስጢፋኖስ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በአቡነ ሒሩት አምላክ የተመሠረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ ውኃ ዘመን የሰው ዘር በኖኅ መርከብ አማካይነት መዳኑን ለማመልከት በመርከብ ቅርፅ የተሠራ ነው።

✔️የዐፄ ዳዊት (1374-1406 ዓ.ም)፣
✔️የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም)፣
✔️የዐፄ ሱስኒዮስ (1600-1625 ዓ.ም.) እና
✔️የዐፄ ፋሲል (1625-1660 ዓ.ም) አስክሬን ሳይፈርስ በክብር የሚገኘው በዚሁ ገዳም ነው።

ደብረ ማሪያም ገዳም የደብረ ማርያም ገዳም በጣና ዘጌ ባሕረ ገብ መሬት ይገኛል። ገዳሙ በጣና

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918208934

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Melese terefe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Melese terefe:

Share