SA Business and Management Consultancy

SA Business and Management Consultancy SA Business and Management consultancy service offer business plan, project feasibility study, proj

06/08/2022
06/08/2022

We are Consult
Potential investment area
Conduct investment feasibility study
Business plan
Socioeconomic and busline surveys

30/11/2021

Breaking news and analysis from TIME.com. Politics, world news, photos, video, tech reviews, health, science and entertainment news.

05/02/2021

የሚሸጥ ኮንደምንየም ቤት
42 ካሬ ባለ አንድ መኝታ
14 መጨረሻ (ወደ ፍኖተ መስመር ላይ)!!!

ጥንቃቄ ለአዲሱ 10 ብር እና ለአሮጊው 100 ብር (በተለይ በገጠር.  ....)
03/10/2020

ጥንቃቄ ለአዲሱ 10 ብር እና ለአሮጊው 100 ብር (በተለይ በገጠር. ....)

እንኳን ለብረሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!!
26/09/2020

እንኳን ለብረሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!!

24/09/2020

!
*****
የብር ኖት ቅየራ (demonetization) ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች፣ ጥቅሞችና ተግዳሮቶች:- የብር ኖት ቅየራ (demonetization) ማለት በፊት ህጋዊ ሆኖ አገልግሎት ላይ የነበረን የብር ኖት ሙሉ በሙሉ ከገበያ በማስወጣትና ህጋዊነቱን በማንሳት በምትኩ አዲስ ህጋዊ የብር ኖት ማተምና በኢኮኖሚው እንዲሰራጭ ማድረግ ማለት ነው፡፡


የብር ኖት ቅየራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ሲኖሩት በዚህች አጭር ፅሁፍ ፖለቲካዊ ምክንያቱን ለጊዜው ተወት አድርጌ በኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ላይ አተኩራለሁ፡፡ ምክንያቶቹ እንደ ሃገራት ነባራዊ ሁኔታ የሚወሰን ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

#አንደኛው፦ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ተብሎ በዋናነት የሚጠቀሰው በተለያየ ምክንያት ገንዘብ ወደ ኢኮኖሚው በብዛት ሲገባ (excessive money supply) እና በኢኮኖሚው የሚዘዋወረውን ገንዘብ (black money) ብሄራዊ ባንክ መቆጣጠር ሲያቅተው የብር ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ለምን የተባለ እንደሆነ በአንድ በኩል መንግስት የበጀት እጥረት ሲገጥመው ብር እያተመ ወይ ደግሞ በብድር ወደ ኢኮኖሚው ያስገባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህገ ወጦች ሀሰተኛ ብር እያተሙ ወደ ሲስተሙ ያስገባሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በኢኮኖሚው የሚዘዋወረው ገንዘብ ከመብዛቱ የተነሳ የዋጋ ንረት ያመጣል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ለመቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል፡፡

#ለምሳሌ:- ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው መንግስት እያተመ በኢኮኖሚው ከረጨው ገንዘብ ውስጥ 113 ቢሊየን ብር ከሲስተሙ ውጭ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ከ2 አመት በፊት አስታውቆ ነበር፡፡ ይህን ያክል ብር ከብሄራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጭ ሆነ ማለት ደግሞ ለተለያዪ ህጋዊ ላልሆኑ ስራዎች ማለትም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፤ ህገ ወጥ ንግድ፤ ህገ ወጥ የእፅ ዝውውር፤ የሽብር ተግባር፤ ወዘተ ይሰራበታል፡፡ እነዚህና መሰል ተግባራት ተደማምረው መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችል የኑሮ ውድነት ይፈጠርና ዜጎች ችግር ውስጥ ይጥላል፡፡ ይህን ለመታደግ መንግስት ብር ኖት ሊቀይር ይችላል፡፡ እኛም ሀገር ዋናው ምክንያት ይህ ነው፡፡

#ሁለተኛው፦ የሃሰተኛ ብር ኖት በኢኮኖሚው ሲዘዋወር እሱኑ ለመከላከል የብር ኖቱን በሃሰት እነዳይታተም የሚያስችሉ ዘዴዎችን (security features) ለማሻሻል የብር ኖት ይቀየራል፡፡ በእኛ ሃገርም መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አይታወቅ እንጂ ህገ ወጦች የሃሰተኛ ብር እያተሙ ሲያሰራጩ እንደነበር በየጊዜው በፖሊስ ሲገለፅ ነበር፡፡

#ሶስተኛው፦ በሙስናና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ብር ከሲስተሙ ውጭ በቤታቸው በማከማቸት የመንግስትን ግብር የሚያጭበረብሩ፣ አለአግባብ ኢኮኖሚውን በማወክ የኑሮ ውድነት የሚፈጥሩ ሰዎችን ለመቆጣጠር የብር ኖት ይቀየራል፡፡ እኛም ሀገር ብዙ ህጋዊ ሌቦች ብራችንን ዘርፈው ሲጫወቱበት እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን፡፡

#አራተኛው፦ ባህላዊ የገንዘብ አጠቃቀማችን (traditional banking system) እና ገንዘብ በቤት የማስቀመጥ ባህላችን (cash based economy) እንዲሁም የአራጣ አበዳሪዎችን ተግባር ለመግታትና የፋይናንስ ስርአቱን ዘመናዊና ከተቻለም ዲጂታል (cash less economy) ለማድረግ ሲፈለግ የብር ኖት ሊቀየር ይችላል፡፡ በእኛም ሀገር እነዚህ ችግሮች ጎልተው ይታያሉ፡፡

#አምስተኛው፦ የገንዘብ አጠቃቀምን አቃፊ ለማድረግ በተለይም አይነ ስውራንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ምልክት በብር ኖቶች ላይ ለማካተት ሲፈለግ ብር ሊቀየር ይችላል፡፡


የብር ኖት ቅየራ ጠቀሜታዎች እንደተቀየረበት አላማ የሚወሰን ቢሆንም በዋናነት የሚከተሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
1. በኢኮኖሚው የሚዘዋወረውን ህገወጥና ከመጠን በላይ የሆነ ገንዘብ በማጥራት የዋጋ ንረትን መቆጣጠር እንዲሁም የገንዘብ አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል፡፡ ባንኮችም ተንቀሳቃሽ ገንዘብ (liquidity problem) እጥረት አይገጥማቸውም፡፡

2. ህገ ወጥነትንና ሙስናን በማስወገድ የመንግስትን የግብር መጠን መጨመር፣ የቁጠባ መጠንን ማሳደግ፣ በባንኮች የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን መጨመርና ብሎም ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ይቻላል፡፡ መንግስት የሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል፣ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት የበጀት እጥረት አይገጥምም፡፡

3. ብሄራዊ ባንክም ይሁን መንግስት የሚያወጣቸው የፊስካልም ሆነ የገንዘብ ፖሊሲዎች ኢኮኖሚውን በአግባቡ ለመቆጣጠር ያስችላሉ፡፡ እስካሁን በነበረው ሁኔታ የሚወጡ ፖሊሲዎች ውጤታማ ያልነበሩት ከብሄራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጭ ተደብቆ ሲዘወር በነበረው ህገ ወጥነት ምክንያት ነው፡፡

4. የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ማለትም የሰዎች መፈናቀል፣ ግድያ፣ እርስ በርስ ግጭት ያስቆማል፡፡

5. ሃሰተኛ ብርን ከሲስተም እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎችን ከመሸወድ ያድናል፡፡ ኢኮኖሚውም ውጤታማ ይሆናል፡፡

6. በአብዛኛው መደበኛ ባልሆነው የፋይናንስ ስርአት (informal banking system) ሲጠቀሙ የነበሩ ወደ መደበኛው ይመጣሉ፡፡ እንደ አራጣ አበዳሪዎች እና ህገ ወጥ ገንዘብ አዟሪዎች ያሉ አካላትን ወደ ሲስተም ለማምጣት ያግዛል፡፡


የብር ቅየራን ፖለቲካዊ አድርጎ የማየት፦ ይህ ማለት ብርን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል፡፡ #ለምሳሌ፦ የብር ለውጡን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ሲያደርግ የነበረው ጠ/ሚንስትሩ ነበር፡፡ ውሳኔው ፖለቲካዊ ቢሆንም ጎልቶ መውጣት ያለበት ኢኮኖሚያዊ አላማው መሆን አለበት፡፡

ለብር ኖት ቅየራ የተሰጠው ጊዜ፦ በእኛ ሀገር ሁኔታ 3 ወር ተሰጥቷል፡፡ በእኔ እምነት ሊያንስ ይችላል፡፡ አንዳንዶች አጭር ጊዜ መሰጠት ነበረበት ይላሉ፡፡ እኔ ግን የሌሎችን ሀገራት ተሞክሮ ስናይ 3 ወር ያንሳል፡፡ ማህበረሰባችን ስለ ገንዘብ አጠቃቀም፤ ስለ ባንክ አካውንት፤ ስለ ቁጠባ፤ ወዘተ ብዙ ማወቅ ያለበት ጉዳዮች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ በተለይ በገጠሩ ማህበረሰብ በደንብ በዘመቻ መልክ ካልተቀሰቀሰ ያለውን ገንዘብ ቶሎ ወደ ባንክ አምጥቶ ይለውጣል ብየ አላምንም፡፡ በርግጥ ጊዜ በተሰጠ ቁጥር ህገ ወጦች ብዙ መላ ይዘይዳሉ፡፡ ሆኖም ግን ጊዜው አጠረም አላጠረም ተንኮል መስራት የሚፈልግ መስራቱ አይቀርም፡፡ ልቡና ይስጠው እንጂ፡፡

200 ብር ኖት አሁን መሰራጨት የለበትም ባይ ነኝ፡፡ ለተንኮለኞች ገንዘብ ለመሰብሰብና ደብቆ ለማስቀመጥ (cash hoarding) ማመቻቸት ስለሆነ፡፡

የውጭ ምንዛሬ እጥረት የባሰ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎች በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ገንዘብ ሳይሆን የውጭ ሃገር ገንዘብን (ዶላርን) እየገዙ ሊያስቀምጡ ይችላሉ፡፡

በብር ቅየራ ወቅት የባንክ ሰራተኞች ታማኝነት፣ የህጎች በአግባቡ መፈፀምና የፀጥታ አካላት ትብብር ወሳኝ ይሆናል፡፡ በሂደትም ተቋማዊ አደረጃጀቱ እየተጠናከረ መሄድ ይኖርበታል፡፡

በህይወቴ ከማውቃቸው ትጉ እና በእውቀት ከሚያስተምሩ አስተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ዶክተር ካሳ ተሻገር (KT Alemu) ነው የፅሁፉ ባለቤት።

Birr notes (old and New)
23/09/2020

Birr notes (old and New)

file:///C:/Users/OWNER/Desktop/NBE/birritu-128.pdf
23/09/2020

fil:///C:/Users/OWNER/Desktop/NBE/birritu-128.pdf

23/09/2020

https://nbebank.com/wp-content/uploads/2019/04/BANKING-BUSINESS-592.pdf

23/09/2020

?
*******
የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትም ሆነ መዳከም ከሚለካባቸው መሰረታዊ ሁኔታዎች ውስጥ ዋናው የገበያ ስርዓቱቴ ያለበት ሁኔታ ነው፡፡ የገበያ ሁኔታ የመንግስትን ጥንካሬ እና ድክመት ማሳያ ነው! ምክንያቱም የገበያ መውደቅ (Market Failures) ከመንግስት ስርዓት መዳከም (Government Failures) ጋር እኩል አደገኛ እና ተመጋጋቢ በመሆናቸው ነው!

በቅድሚያ በአንድ ሀገር ውስጥ ገበያ የተረጋጋ ነው (Market Success) በተመሳሳይ ጠንካራ መንግስት አለ የሚባለው ምን ሲሟላ ነው እንደሆነ እንይ…….

የምርት እና አገልግሎት አቅርቦት፤ ለምርት እና ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አቅርቦት እና ፍላጎት በገበያ ብቻ ሲመራ ( #ለምሳሌ፡- አምራቾች ለምርት የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት በቀላሉ ፍታዊ በሆነ ዋጋ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፈለጉትን ያህል መግዛት እና ማምረት ሲችሉ እንዲሁም ያመረቱትን በገበያ ፉክክር ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በውድድር በተገቢው ዋጋ መሸጥ ሲችሉ ማለት ነው)፡፡

ስለ ማንኛውም ገበያ አቅርቦት፤ ፍላጎት፤ ዋጋ፤ ቦታ፤ ወዘተ አምራቾችም ሆኑ ሸማቾች ተገቢውን መረጃ Perfect information ሲያገኙ፤ ግብይቶች እና ድርድሮች በቀላሉ በማንኛውም ቦታ መከናወን ሲችሉ (Transactions are facilitated)፤ ፍታዊ ክፍፍል፤ የገበያ ደህንንት (Insurance is a very important commodity in a world of uncertainty)፤ ምክንያታዊ የሆነ ዋጋ፤ ወዘተ ሲኖር ማለት ነው፡፡

……
በየትኛውም ገበያ (ማለትም በሰራተኛ ገበያ (Labor Market)፤ በገንዘብ ገበያ (Money Market)፤ በቁሳቁስ ገበያ (Goods Market) እና በአገልግሎት ገበያ (Service Market) ላይ የፍላጎት እና የአቅርቦት አለመመጣጠን ሲኖር፤

በግለሰቦች ተጠቃሚነት ወይም ጉዳት እና በማህበረሰብ ጥቅም ወይም ጉዳት መካከል ሰፊ ልዩነት ሲፈጠር ( #ለምሳሌ፡- አንድ ፋብሪካ በሰዎች መኖሪያ አካባቢ የከፈተ ባለሃብት በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎች ጤንነት ሳይጠነቀቅ አካባቢውን እየበደለ ለራሱ ብቻ ተጠቃሚ ሲሆን ማለት ነው! ምክንያቱም የባለሃብቱ ትርፍ የሚመጣው የነዋሪዎቹ ጤና ተቃውሶ ስለሆነ)፤

ጥቂቶች የተቆጣጠሩት ገበያ ሲበዛ ወይም Absence competition ሲኖር (ፉክክር የሌለበት ገበያ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ እንዲፈጠር ያደርጋል ይሄ ደግሞ ለምርት የማይገባ/የተጋነነ ዋጋ እንዲጠየቅ ያደርጋል)፤ የመንግስት ጥብቅ የገበያ ቁጥጥር ሲኖር (ገበያ መመራት ያለበት በፍላጎት እና በአቅርቦት መርህ መሆን አለበት (Adam Smith’s Famous doctrine of ‘invisible hand’))፤

ስለ ማንኛውም ገበያ አቅርቦት፤ ፍላጎት፤ ዋጋ፤ ቦታ፤ ወዘተ አምራቾችም ሆኑ ሸማቾች ተገቢው መረጃ ማግኘት ሲያቅታቸው ወይም Information failure ሲኖር (የገበያ ሰንሰለት መርዘም፤ ተገቢ ያልሆነ የምርት መደበቅ እና የደላሎች መበራከት ሲፈጠር)፤ ወዘተ፡፡

በዓለም ላይ ሁለት አይነት የገበያ መውደቅ አለ! አንደኛው ኢኮኖሚው ምንም አይነት ምርት እና አገልግሎት ለገበያው ማቅረብ ሳይችል ሲቀር (Complete market failure) ሲሆን ሁለተኛው ገበያው ቢኖርም ከፍላጎት አንጻር በቂ ያልሆነ ምርት በተጋነነ ዋጋ ሲያቀርብ ማለት ነው (Partial market failure)፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው ሁኔታ በአብዛኛው ወደ Complete market failure የሚያደላ ይመስለኛል ምክንያቱም ተፈላጊውን ምርት በሀገር ውስጥ አለማምረት ብቻ ሳይሆን ከውጪም ሀገር ገዝቶ ማስገባት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

Government Failures የሚለካው መንግስት በገበያው ውስጥ ባለው ጣልቃ ገብነት መጠን እና ገበያው እንዳይወድቅ ባደረገው ጥረት እና በተሳካለት ልክ ነው! ምክንያቱም መንግስት ገበያውን በረጅሙ ለራሱ ለገበያው እና ለግል ሴክተሩ በመስጠት ሌሎች መሰረታው ስራዎች ላይ ባለው ተሳትፎ ይለካል ( #ለምሳሌ፡- በዜጎች መካከል የሚኖርን የሃብት ክፍፍል ልዩነት ማጥበብ፤ ነጻ እና በጤናማ ፉክክር ላይ የተመሰረተ የገበያ ምህዳር በመፍጠር፤ የሸማቾች እና የአምራቾች ደህንነትን በማስጠበቅ፤ የመሰረተ ልማት ግንባታን በማሳደግ፤ የዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥ (በሰላም ወቶ መግባት፤ ማምረት፤ መሸጥ፤ መዘዋወር፤ ሃብት ማፍራት፤ ወዘተ)፤ ወዘተ ሲቻል ነው፡፡ ከላይ በተጠቀሱት መለኪያዎች መንግስትም ገበያም በተመሳሳይ ግራፍ እየወረዱ ነው!

👉Telegram:-
https://t.me/wasealpha
👉Facebook:-
https://www.facebook.com/EconomistWasyhun/?modal=admin_todo_tour

Address

11
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SA Business and Management Consultancy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SA Business and Management Consultancy:

Share