Debrebirhan Investment consultancy service

Debrebirhan Investment consultancy service Invite to Invest @ Debrebirhan

02/02/2026

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባለፈው በጀት ዓመት አመቱን ሙሉ ከሰራው አረቦን በግማሽ ቢሊየን የበለጠ አረቦን በስድስት ወራት ብቻ መስራት ቻለ፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቷል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቤል ታደሰ እንዳሉት ÷ በግማሽ ዓመቱ የተገኘው ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት በዓመቱ ከተገኘው የበለጠ ነው፡፡

የተቋሙን የአሰራር ሥርዓት ለማዘመንና ለማሻሻል የሰው ሃይል አቅምን ማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ላይ በትኩረት መሰራቱን አመልክተዋል፡፡

የድርጅቱ የገበያ ድርሻ አሁን ላይ 45 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የገለጹት አቶ አቤል÷ ለዘንድሮው የላቀ አፈጻጸም ማሻሻያው ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል፡፡

50 ዓመታትን በመድን አገልግሎት የዘለቀው ድርጅቱ ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦው እያበረከተ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-

06/04/2025
እንኳን ለ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የእድገት ዓመት ይሁንልን::  Happy New Year 2017   # 🇪🇹
10/09/2024

እንኳን ለ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የእድገት ዓመት ይሁንልን:: Happy New Year 2017 # 🇪🇹

12/12/2023
01/06/2023

ኮምፒውተር ሳይንስ፣ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም ተዛማጅ የትምህርት መስክ የተመረቀች ስራ ፈላጊ Inbox ስልክ ቁጥር ወይም መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት  ቢሮ  ባዘጋጀዉ  '' ኢትዮጵያ ታምርት '' መድረክ  ላይ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት በዚህ ዓመት  ፦  -  '' ኢትዮጵያ  ታምርት'' ፎረም  በ...
25/02/2023

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ባዘጋጀዉ '' ኢትዮጵያ ታምርት '' መድረክ ላይ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት በዚህ ዓመት ፦
- '' ኢትዮጵያ ታምርት'' ፎረም በማዘጋጀት
- ኢንተርናሽናል ኤክስፖ በማዘጋጀት
- ፕሮጀክቶችን ወደ አፈፃፀም በማስገባት
- የነበሩትን ማነቆዎች በመፍታት
- ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢ በመፍጠር ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት በማሳየት ከክልላችን ከተሞች ቀዳሚዉን ስፍራ በመያዝ ተሸላሚ ሆኗል።

ስለሆነም የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ሰላም ወዳድ ሁሌም ለሰላም ዘብ የምትቆሙ የዉቧ ደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎቹ በሙሉ ለዚህ ዉጤት መምጣት የእናንተ ድርሻ የጎላ ነዉና እንኳን ደስ አላችሁ።

አቶ ብርሃን ገ/ህይወት
የደ/ብ/ከተማ ኢ/ኢ መምሪያ ሀላፊ

በበጀት አመቱ ተከታታይ 6 ወራት ለ 188 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሠጠቱን እንዲሁም ለከተማው የ24 ቢሊዮን ብር ካፒታል ወደ ከተማው ማምጣት መቻሉን የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር...
24/02/2023

በበጀት አመቱ ተከታታይ 6 ወራት ለ 188 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሠጠቱን እንዲሁም ለከተማው የ24 ቢሊዮን ብር ካፒታል ወደ ከተማው ማምጣት መቻሉን የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በ6 ወራት የተሠሩ ዋና ዋና ተግባራትን ያመላከተ የአፈጻጸም ግምገማ አድርጓል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሂዎት፣ የመምሪያው ባለሙያዎች ተገኝተው የኢንቨስትመንቱን ፋይዳና ግብ ያመላከተ የአፈጻጸም ምልከታ ነው ያካሄደው።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሂዎት በ6 ወራት የተሠሩ ዋና ዋና የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ መምሪያ ተግባራትን በሪፓርት ሰነዳቸው ለባለድርሻ አካላቱ አቅርበዋል።

በከተማችን የኢንቨስትመንት ማነቃቃትን ይበልጥ ለማጠናከር ኢንተርናሽናል ኤክስፖ አንዱ ማሣያ ነው በዚህ ኤክስፖም የውጭ ባለሀብቶችን መሣብ ተችሏል፣ የውጭ ዲፕሎማቶች በከተማችን መጥተው የልማት አቅሞችን ለመፍጠር ቃል ገብተዋል፣ ከፍተኛ የሀገራችን አመራሮች በከተማችን ተገኝተው የኢንዱስትሪውን እድገትን ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት መሠጠቱን የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሂዎት በሪፖርታቸው አንስተዋል

የከተማውን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ለማነቃቃትና ፕሮሞሽኑን ለማጉላት ከ500 በላይ ባለሀብቶች ያካተተ ኢትዮጵያ ታምርት ፎረም በከተማው በድምቀት ተካሂዷል ብለዋል።

ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊው አቶ ብርሃን ገብረሂዎት እንዳሉትም በደብረብርሃን ከተማ በምግብ ማቀነባበር በጨርቃጨርቅ በመድሃኒት እንዲሁም በመጠጥ ዘርፍ የተሠማሩ ከ 80 በላይ በስራ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን አንስተው እነዚህ ኢንዱስትሪዎችም ለ25 ሺ ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፈጠሩን አብራርተዋል።

በከተማችን በማምረት ላይ ያሉ 6 ኢንዱስትሪዎች 12 ሚሊዮን 529 ሺ ዶላር ለሀገር እድገት ማስገኘታቸውን ነው ያነሡት

በከተማው ከ525 በላይ በቅድመ ግንባታ፣ በግንባታ እንዲሁም በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙም ነው የተናገሩት አቶ ብርሃን ገብረሂዎት

በዚህ 6 ወራት ለ 188 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሠጠቱን እንዲሁም ለከተማው የ24 ቢሊዮን ብር ካፒታል ወደ ከተማው ማምጣት መቻሉንም ነው አቶ ብርሃን ገብረሂዎት በሪፖርታቸው የገለጹት

ከሌሎች የሀገራችንና የክልላችን ከተሞች የሚገኙ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያዎች ከደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ልምድና ተሞክሮ ቀምረው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል አቶ ብርሃን ገብረሂዎት

ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣ 24 ኢንዱስትሪዎችን በቋሚ ክትትልና ድጋፍ ወደ ስራ ማስገባት ፣ ለረዥም ጊዜ መሬትን አጥረው የተቀመጡ ባለሀብቶች በመለየት እርምጃ መውሰድ ፣ በክልል ድጎማ የሚሰራውን የኢንዱስትሪዎችን የመንገድ መሠረተ ልማት ማስጀመር የሚሉትን ዋና ዋና ተግባራትን የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊው አቶ ብርሃን ገብረሂዎት እንዲሁም የመምሪያው ባለሙያዎች በጋራ አቋም በቀጣይ ለመፈጸም እንደሚያስፈልግ በአቅጣጫቸው አንስተዋል።

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debrebirhan Investment consultancy service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Debrebirhan Investment consultancy service:

Share