Smart-Link Internet Cafe and Print Advert

Smart-Link Internet Cafe and Print Advert GÉNÉRAL IT SOLUTION... AND PRINT ADVERT

23/09/2023

የዘመናችን (የወቅቱን ፈተናዎች) መረዳት ለተሳነን እኛ።
ጸብ ፣ ግጭት፣ ጥላቻን ለተላመድነው እኛ።

መጪዉን ዘመን ለመረዳት ቀርቶ ፣ ያለንበትን በቅጡ ላላወቅነው እኛ። ትላንትን በመልካም በመከባበር በመተሳሰብ አድገን እና ኖረን ። ጥቂቷን መዋደድ ለተጠየፍነው እኛ።
ቀጣይ ትውልድ (እኛ የፈጠርነው ትውልድ ምንን እንደምናወርሰው ላላወቅን ፣ ላላሰብንን ላልተገነዘብነው እኛ።
የዘመናችን 5 አስፈሪ ወይም አስጊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አጠር አርገን በገመትነው በጠረጠርነው መጠን ከ5ኛ ወደ አንደኛው ለማሳየት እንሞክራለን ።

5. internet Surveillance

◽️ ኢንተርኔትን በመጠቀም በስልኮቻችን ፣ በታብሌቶቻችን ፣ በላፕቶፖቻችን ልንሰለል እና የግል Privacy ልናጣ እንችላለን። አብዛኞቹ የሞባይል አምራቾች የራሳቸውን Privacy Policy ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች የኛን ሚስጥራዊ መረጃዎች በመንግስታት ተገደው ሊሰጡ ይችላሉ።

🔺ለምሳሌ፡ ስንቶቻችን የስማርት ስልኮች ተጠቃሚ ነን። ስማርት ስልኮች ቢያንስ 2 ካሜራ (የፊትና የኋላ) የGPS መሳሪያ አላቸው። እነዚህን መሳሪያዎች በመጠቀም ብቻ የት እንዳለን ማን እንደሆንን የእለት ተእለት ኑሮአችን ጭምር ሊታይ ይችላል። ማን ያውቃል ይህንን ፖስት በምታነቡበት ሰአት እራሱ የሆነ ሰው ሰልፊ ካሜራችሁን በመጠቀም እያያችሁ ይሆናል።

4. Robotic Solders

◽️ ሰውሰራሽ ወታደሮች ያላቸውን ሀይል ለማወቅ Terminator ማየት በቂ ነው። በእርግጥ Terminator Science Fiction የሆነ ፊልም ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት በጣም ብዙ ነገር ማድረግ የሚችሉ ሮቦቶች እየተሰሩ ነው። ማን ያውቃል በቀጣይ እራሱን Terminatorን ቢሰሩትስ።

◽️ ሮቦቶች አይርባቸውም ፣ አይጠማቸውም ፣ አይደክማቸውም በፍጥነት በጥንካሬ እና በብዙ ነገር ከሰዎች ይበልጣሉ ነገርግን የሰው ልጅ ያለው ፈቃድ የሚባል ነገር የላቸውም ስለዚህ እንዲጨፈጭፉ ከታዘዙ ያለምንም ርህራሄ ያደርጉታል። ሰው ሰራሽ ወታደሮች የሰሯቸውን ሰዎች የማጥፋት አቅም አላቸው።

3. DNA Editing

◽️ ሳይንቲስቶች የሰው ልጆችን ዘረመል ወይም DNA ካገኙ ጀምሮ የተለያዩ ምርምሮች እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገርግን ይህ ዘረመል በሰው ልጆች ለይ ብቻ የሚገኝ አይደለም በሁሉም ህይወት ያላቸው ነገሮች ለይ አለ። እናም ይህንን DNA በማስተካከል ድክመት የሌለው ፍጥረት ለመስራት እየተሞከረ ይገኛል።

◽️ ሳይንቲስቶች የሰዎችን ዘረመል ማረም ወይም ማስተካከል ይቻላል ብለው ያምናሉ። በአሁኑ ሰአት አለምን ያስጨነቀው ኮሮና እራሱ በጂኔቲክ ኤዲቲንግ የተፈበረከ ባዮሎጂካል መሳሪያ እንደሆነ ጥርጣሬያቸውን የሚሰጡ አሉ።

2. Micro Chips

◽️ በአሁን ጊዜ የተለያዩ መረጃዎቻችንን ወይም ሰነዶቻችንን የምንይዘው በወረቀች ወይም በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ነው። ነገር ግን አሁን እየተመረተ ያለ ቴክኖሎጂ መታወቂያችንን ፣ የልደት ሰርተፊኬታችንን ፣ የባንክ ቡካችንን ወዘተ መረጃዎቻችንን በአንዲት ቺፕ ለይ በመጫን ይህቺን መሳሪያ በሰውነታችን ውስጥ ትቀበራለች።

◽️ ነገር ግን ይህች በሰውነታችን ውስጥ የምትቀበር መሳሪያ የኛን መረጃዎች ከመያዝ ባለፈ የእኛን እንቅስቃሴዎች እና አኳኋን ከመከታተል እስከ መቆጣጠር ድረስ አገልግሎት ለይ ልትውል ትችላለች።

1. Nuclear Bombs

◽️ የኒኩሌር ቦምቦች የሚያደርሱትን ጥፋት ለመረዳት የጃፓኖቹን ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ማየት በቂ ነው። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት አያርገውና በአሁኑ ሰአት የኒኩሌሬ ጦርነት ቢነሳ አለማችን ትጠፋለች። በሀያላን ሀገራት ዘንድ ብቻ የሚገኘው ይህ መሳሪያ ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ለይ ሲጣል ከነበረው በላይ ዘምኖና ተሻሽሎ ተሰርቷል።

◽️ አሁን ያለው የኒኩሌር ቦምብ ቢፈነዳ በትንሹ የጨረራ ራዲየስ 7.49 ኪ.ሜ ወይም 176 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል ፣ የአየር ፍንዳታ ራዲየስ 12.51 ኪ.ሜ ወይም 491 ስኩዌር ኪ.ሜ ይሸፍናል ፣ የሙቀት ጨረር ራዲየስ 77.06 ኪ.ሜ ወይም 18626 ካሬ ኪ.ሜ ይሸፍናል ፡፡ አሜሪካ በ2ኛው የአለም ጦርነት ጃፓን ለይ ከጣለችው ቦምብ በ3,333 እጥፍ ያህል የበለጠ ኃይል አለው፡፡

ደግ እና መልካሙ ቀን ይመጣል። ለሚያልፍ አጭር ጊዜያት የማያልፉ ምግባራትን ፣ ጥላቻን፣ መጠፋፋትን፣ መጠላለፍን። በቀናነት እና መጥፎን በጥሩ በመተርጎም ።

አባት እናቶች ባሳዩን መንገድ መሻገርን በጥበብ፣ በመተሳሰብ፣ ጎን ለጎን በመሆን፣ ቢሆን ባይ ነኝ።

@ ቤናአብ አበበ።

ሄኖክ ዲጂታል ፎቶ ስቱዲዮ
07/08/2015

ሄኖክ ዲጂታል ፎቶ ስቱዲዮ

the history of mother tongue
03/06/2015

the history of mother tongue

PC
20/05/2015

PC

28/10/2014
23/10/2014
be careful in your move???
23/10/2014

be careful in your move???

amaizing littel baby... like it@all.. and share if u are amaized....
23/10/2014

amaizing littel baby... like it@all.. and share if u are amaized....

23/10/2014

Address

SOUTH WOLLO
Dessi
1033

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Smart-Link Internet Cafe and Print Advert posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share