20/02/2021
"ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ"?
ሸዋረገድ ገድሌ የጀግንነት ተምሳሌት በ1935 የኢጣሊያን ወረራ ጊዜ መረጃ ስንቅ በማቀበል ተርፎም መሳሪያ በመያዝ ጠላትን በመጣበት በመመለስ ጀግንነትን ያሳየች ሴት ዕንቁአችን ናት።
በ1935 ጦርነት ጊዜ ወደ ጅማ ሂዳ ከገረ ሱዱኪ ጦር ጋር ተቀላቅላ ተዋግታለች ታላቆ አርበኛ ሸዋረገድ ገድሌ ያን ጊዜ በነበረው ውጊያ ጣሊያኖች ማረኮት በጣሊያኑ ፊት ስትቀርብ በንቀት ነበር ያያት ምክንያቱም ሴት መሆኖና አርበኛ መሆኖን ስላልተቀበለ ጣሊያኑ "ቆይ አንች ሴት ነሽ ጫካ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ?" አላት እንግዲህ ልብ በሉ የጣሊያን ጦር አሸንፎል የእሶ ጦር ከሆላ ተሸንፎል።
ምን ብትል ነፃ ትወጣለች? ምንም አያስቸግርም "አስገዲደውኝ ነው።" ማለት ትችል ነበር።
ኢትዮጲያዊነት ሚስጥሩ ስለገባት "የአንበሶች መኖሪያ ጫካ ውስጥ ስለሆነ" አለቻቸው አያችሁ አርበኞቻችን ስለሀገራቸው ተሰውተው ነው ያቆሞት እነ ባልቻ ሳፎ አጨብጫቢ ሸላሚ በሌለበት ብቻውን ሂዶ የጣሊያንን የጦር መሪውንና ጠባቂዎቹን እረሽኖ የተሰዋ አርበኛ ያሉበት ሀገር ነው ያለነው።
እምየ ሚኒልክ የጊወርጊስን ታቦት አውጥተው በማሪያም ምለው ህዝቡን ቀስቅሰው አድዋ ላይ የነፃነታችንን በር የከፈትንበት ጊዜ ነው።
ኢትዮጲያየ3000 ዓመት ታሪክ ያላት እያልን አንሸወድ የ6000 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ምንጭ መራራ እውነት ከሚለው መፅሀፍ ነው ያገኘሁት ኢትዮጲያ "ታሳልፋለች እንጅ አታልፍም"
ስለ አድዋ በእንግሊዘኛ ከተፃፈው መፅሀፍ ለአድዋ ድል ምክንያቱ አዋሉም የሚባል ለጣሊያኖች የተሳሳተ መረጃ የሚሰጥ ሰው ነው ይላል ግን ፍፁም ስህተት ነው። በጀግና ልጆቾ ነፃነት አግኝተናል። የመለኮታዊ ሀይል(spiritual power) እንዳለ ሁኖ የአርበኞቻችን ክብር መጠበቅ የእኛ ሀላፊነት ነው።
"ክብር ለአርበኞቻችን"
13/06/2013
ወገልጤና
አድስ በለጠ