Dire Micro Finance Institution

Dire Micro Finance Institution በፍቅር እናገለግሎታለን!

 #ተምሳሌቶቹ   የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም              "ካልቆጠብኩ ቅር ቅር ይለኛል"                      ሰለሞን ተፈራየድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫ...
20/02/2026

#ተምሳሌቶቹ
የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም
"ካልቆጠብኩ ቅር ቅር ይለኛል"
ሰለሞን ተፈራ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ

አቶ ሰለሞን ተፈራ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ ሲሆኑ በንፅህና መስጫ አገልግሎት /በሻወር ቤትና መፀዳጃ ቤት/ አገልግሎት የተሰማሩ ምስጉን ደንበኛ ናቸው፡፡

ለሥራቸው መነሻ የሆናቸውና ምቹ መደላድል የፈጠረላቸው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ያመቻቸላቸው የፋይናንስ ድጋፍ ነው፡፡ ስራቸውን ሲጀምሩ በ4 ሻወር ቤትና በ2 መፀዳጃ ቤቶች ሲሆን አሁን ላይ የሻወር ቤታቸው ወደ 10፣የመፀዳጃ ቤቶቹ ደግሞ ወደ 5 በማሳደግ ለአሸዋና አካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ቁጠባ ለአቶ ሰለሞን የህይወቱ መሠረት ፣የህይወቱም መርህ ነው፡፡ ያለቁጠባ መኖር ለእሱ ከባዱ ነገር ነው፡፡ ቁጠባ ለእኔ ሱስ ነው ካልቆጠብኩ እራሱ ቅር ቅር ይለኛል ይላል ቁጠባን ባህል አድርጎ ያሰረፀው ዕንግዳችን፡፡ በመቆጠቡ በህይወቱ፣ በስራው ያገኘውን ጥቅም ያውቀዋልና ቁጠባን የህይወቱ አንድ አካል አድርጎ ይዞታል፡፡ ሌሎችም ይህን ባህል ቢያዳብሩ በእጅጉ እንደሚጠቀሙም ከልምዱ ያጋራል፡፡

በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከፍተኛ ዕገዛ እንደተደረገለትና በተቋሙ አገልግሎት ደስተኛ መሆኑን የሚገልፀው አቶ ሰለሞን ተፈራ ለተቋሙ ድጋፍና አለኝታነት ምስጋናውን በማቅረብ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ፈጥኖ ደራሽና የማኅበረሰቡ አለኝታ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው ሲልም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስን አበርክቶ በጉልህ ይጠቅሳል፡፡

በቀጣይም ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ያለውን ቤተሰባዊ እና የደንበኝነት ግንኙነት በማጠናከር ስራውን ለማስፋፋት ያልማል ምስጉን ደንበኛ አቶ ሰለሞን ተፈራ፡፡ እኛም ያሰብከው ይሳካ፣ ስራህ ፍሬያማህ ይሁንልህ እያልን እንደ መርሃችን አንተንም ሌሎች ደንበኞቻችንን በፍቅር ማገልገላችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን፡፡
በፍቅር እናገለግሎታለን!

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #መረጃ | ስለ-የፋይናንስ ዕውቀት   የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ምየፋይናንስ ዕውቀትየፋይናንስ ዕውቀት ማለት ገንዘብ ከየትና እንዴት  እንደሚመጣ፣ እንዴት እንደሚሰራ፣ እንዴት ማስተዳደር እ...
16/02/2026

#መረጃ | ስለ-የፋይናንስ ዕውቀት
የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም

የፋይናንስ ዕውቀት

የፋይናንስ ዕውቀት ማለት ገንዘብ ከየትና እንዴት እንደሚመጣ፣ እንዴት እንደሚሰራ፣ እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል፣ ምን ላይ መዋል እንዳለበት፣ እንዴት ኢንቨስት ማድረግ እንደሚቻል ማወቅ ማለት ነው፡፡

የፋይናንስ ዕውቀት አሁን ባለንበት የዓለም ዕድገት ደረጃ በጣም አስፈላጊ ዕውቀት ነው፡፡ምክንያቱም በተለያየ መንገድ ያገኘነውን ገንዘብ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት የተሻለ ኑሮ ላይ ወይም ዓላማችን ላይ መድረስ አንችልም፡፡ስለ ገንዘብ ማወቅ ማለት ስነ ኑሮአችን፣ስለስራችን፣ በአጠቃላይ ስለ ዓላማችን ማወቅ ማለት ነው፡፡የፋይናንስ ዕውቀት ስለ በጀት፣ቁጠባ፣ ብድርና ኢንቨስትመንት ልከኛ ውሳኔዎችን እንድንወስን ይረዳናል፡፡የዚህ ዕውቀት አለመኖር ሰዎች ለፍተውና ጥረው ግረው የሚያገኙት ገንዘብ ያሰቡትን ሳይፈፅሙና ደስተኛ ሳይሆኑ እንዲያልፉ ያደርጋቸዋል፡፡

የገንዘብ ማግኛ መንገዶች ምንድናቸው?

አራት ዋና ዋና የገንዘብ ማግኛ መንገዶች አሉ፡፡ እነዚህም ፡-1.ቅጥር (Employee) ፡ ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት መስራት፡፡ 2. የራስን ስራ በመሥራት (Self Employed): የራስን ስራ ፈጥሮ መሥራት (ለምሳሌ ፍሪላንስ) ፡፡ 3. የንግድ ሥራ ላይ በመሰማራት (Business Owner): ሰዎች ለእርስዎ የሚሰሩበት የንግድ ድርጅት መመስረት፡፡ 4. ኢንቨስተር ሆኖ ገንዘብን መሥራት (Investor): ገንዘብዎን ለእርስዎ እንዲሰራ በማድረግ ከኢንቨስትመንት ገቢ ማግኘት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 3ኛውና እና 4ኛው የፋይናንስ ነፃነት የሚያስገኙና አስተማማኝ ምንጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ቁጠባ ምንድነው ለምን እንቆጥባለን?

ቁጠባ ማለት ገንዘብ ወደፊት ጥቅም እንዲሰጥ ዛሬ ላይ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ ቁጠባ ከወጪያችን ላይ የሚተርፍ ሳይሆን ከገቢያችን ላይ ቅድሚያ በመስጠት የምናስቀምጠው የተወሰነ ክፍል ነው፡፡ ቁጠባ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ከብክነት የፀዳ ኑሮ መኖርም የቁጠባ አካል ነው፡፡ገንዘብ የምንቆጥብባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ ከእነዚህም መካከል፡- የተጠበቁና ያልተጠበቁ ፍላጎቶችን ለማሟላት፣ለኢንቨስትመንት መሠረት ለመጣል ወይም ካፒታል ለማሳደግ፣ንብረት ለማፍራት፣ አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭ እንዲኖር፣ ለድንገተኛ ክፍያዎች፣ ለትምህርት፣ለጤና እና ለጡረታ ጊዜ፣ ለልጆች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ቁጠባችንን የሚወስነው ገቢያችን ሳይሆን ወጪያችንን የመቆጣጠር ችሎታችን መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

የመረጃ ምንጫችን ክህሎት ዶትኮም ነው፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ተምሳሌቶቹ    የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም "ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እኔን ስኬታማ እንድሆን አድርጎኛል"                     ሰለሞን ደምሴየድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ...
11/02/2026

#ተምሳሌቶቹ
የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

"ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እኔን ስኬታማ እንድሆን አድርጎኛል"
ሰለሞን ደምሴ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ

ሰለሞን ደምሴ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ምስጉን ደንበኞች አንዱ ነው፡፡ በአልባሳትና በጫማ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራው ይህ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ በቁጠባ ባህሉና ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ባለው የታማኝ ደንበኛነት በጉልህ የሚጠቀስ ነው፡፡

ደንበኝነት ‘ሀ’ ብሎ ሲጀምር ከሚሰራው ላይ የነገ ተስፋን በመሰነቅ፣ነገ የሚያስበው የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት በመቆጠብ ነው፡፡ ይህም የቁጠባ ትጋቱና ከልምድ አድጎ ባህሉ ያደረገው የቁጠባ ብርታቱ በትልቁ ጠቅሞታል፡፡

በቁጠባ የጀመረው የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ወዳጅነቱ ወደ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚነት አደገና በቡድን ብድር ከእህት ወንድሙ ጋር በመሆን ከ10ሺ ብር የጀመረው የብድር አገልግሎት ተጠቃሚነቱ እስከ 200 ሺ ብር በማሳደግ ስራውን ማሳደግና ማስፋፋት ችሏል፡፡

ሰለሞንን ለየት የሚያደርገው ከእሱም ባለፈ የቤተሰብ አባላቱን የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግና ስራቸውን እንዲያሳድጉ ተምሳሌት መሆኑ ነው፡፡

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንደሚያስደስቱትና በስራውም ውጤታማ እንዲሆን እንዳደረጉት ዕንግዳችን ይናገራል፡፡

ሰው ባለው ነገር ሲያምንና በትንሹ ቁጠባ በመጀመር እያለ እያለ የቁጠባ ባህሉን ማሳደግ ከቻለ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ከህይወት ተሞክሮው ያካፍላል፡፡ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከምንም በላይ ስራው ነው የሚመሰክርለት የሚለው የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ ደንበኛው ሰለሞን ሰብስቤ በተለይም ተቋሙ ለወጣቶች በርካታ አማራጮች ያሉትና ሰፊ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ቁጠባን አንድ ብሎ በተቋሙ በመጀመር የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ ለራሳቸው የስራ ዕድል መፍጠር ብሎም ለሌሎችም መትረፍ እንደሚችሉ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ዜና| ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ  በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ  አዲስ ቅርንጫፋን በይፋ ከፈተ ።   ጥር  23 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በመዲናችን አዲስ አበባ ቦ...
31/01/2026

#ዜና| ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ አዲስ ቅርንጫፋን በይፋ ከፈተ ።

ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በመዲናችን አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ አዲስ ቅርንጫፋን በይፋ አስመርቆ ሥራ ጀመረ።

ተቋሙ አዲሱን ቅርንጫፍ መክፈቱ የፋይናንስ ተደራሽነትና አካታችነትን ለማስፋት የሚያግዝ እርምጃ መሆኑ በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ እንደገለፁት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለማኅበረሰብ የተመሰረተ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠትን ዋነኛ ተልዕኮው አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት የተቋሙ ጠቅላላ የብር መጠን ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን እና ከ111 ሺህ በላይ የብድርና ቁጠባ ደንበኞችን እያገለገለ መሆኑን ገልጸዋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በተለያዩ የክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተሾመ አዲሱ የቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የተቋሙ ቅርንጫፍ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ተቋሙ ከመደበኛ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪ ወለድ አልባ አገልግሎቶች፣ የማሽነሪ ሊዝ ብድር እና ከንጹህ ኃይል ጋር የተያያዙ አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን እያቀረበ ወደ ህብረተሰብ እየቀረበ መሆኑን አቶ ተሾመ ጨምረው ገልጸዋል ።

በምረቃት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት ተጋባዥ ዕንግዶች ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ መክፈቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የቅርንጫፉ መከፈቱ ተደራሽነቱን በይበልጥ በማስፋት ኅብረተሰቡን በቅርበት ለማገልገል አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግሥትና የተቋማት ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ዜና| ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ ፡፡   ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ምየቁጠባ መሠረት ማስፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መ...
24/01/2026

#ዜና|
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ ፡፡

ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የቁጠባ መሠረት ማስፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ በሐረር ከተማ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሚገኙ ቅርንጫፎች የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የኦፕሬሽን እና የፋይናንስ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ለ2,115 የብድር ደንበኞች ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ ለ2,084 የብድር ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም የዕቅዱን 99 በመቶ ማሳካት ተችሏል ፤ በግማሽ ዓመቱ 560,559,095 ብር ለማበደር ታቅዶ 511,881,132 ብር ማበደር የተቻለ ሲሆን የዕቅዱን 91 በመቶ ማሳካት መቻሉ በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡

በቁጠባ አሰባሰብ ረገድም በግማሽ ዓመቱ የዕቅዱን 119 በመቶ መፈጸም ተችሏል፤ ሴቶችን እና ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራ ስራ በግማሽ ዓመቱ ለ1,231 ሴቶች ብር 320,641,086 ለማበደር ታቅዶ ለ1,022 ሴቶች የዕቅዱን 83 በመቶ ፣ በብር ደግሞ 283,971,200 የዕቅዱን 89በመቶ ማሳካት ተችሏል፤ ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በአጠቃላይ ከሚሰጠው ብድር ውስጥ ለ821 ወጣቶች ብር 213,760,724 ለማበደር ታቅዶ ለ1,282 ወጣቶች የዕቅዱን 156 በመቶ ወጣቶች ፣ በብር ደግሞ 357,377,503 ብር በማሰራጨት የዕቅዱን 167 በመቶ ማበደር መቻሉ ተመላክቷል፡፡

የተጠቃለለ በብድር አመላለስ ረገድም የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ፣ የዘመን ብድር አመላለስ ላይም የታየው ለውጥ አበረታች መሆኑን በመጥቀስ የውዝፍ አመላለስ ላይ ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ ትኩረት በመሥጠት መስራት እንደሚጠበቅም በዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ተሾመ አበበ ተመላክቷል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የቁጠባ አሰባሰብ ላይ ዕመርታ እየታየ መሆኑን በመጥቀስ በይበልጥ የቁጠባ መሠረትን ማስፋት ላይ በቁርጠኝነት፣ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ መሥራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
የደንበኞች ዕርካታን በማሻሻልና በማሳደግ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች የደንበኛን ዕርካታን በሚጨምሩ አግባቦች መቃኘት እንዳለበትና የደንበኞች ዕርካታ የተቋማቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ የደንበኞች ዕርካታ ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ አፅንኦት ተሰጥቶ እንደሚሰራበት ገልፀዋል፡፡

በገጠር ወረዳዎች ላይ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የብድርና ቁጠባ ተደራሽነት ማስፋት፣የሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚነት በይበልጥ ማጎልበት በቀጣይ የተቋሙ ዋና የትኩረት መስኮች መሆናቸውም ተነስቷል፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
18/01/2026

እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

 #ተምሳሌቶቹ    ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም "ቀደም ብዬ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ አለመሆኔ በጣም ይቆጨኛል"                             አሸናፊ አበበየድሬ ማይክሮ ፋ...
17/01/2026

#ተምሳሌቶቹ
ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

"ቀደም ብዬ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ አለመሆኔ በጣም ይቆጨኛል"
አሸናፊ አበበ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ

አቶ አሸናፊ አበበ በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ ደንበኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ በፊት ላይ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች በመሰማራት ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ በሸቀጣሸቀጥ የንግድ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ በዚህ ሥራውም የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ተግቶ እየሰራ ያለ ወጣት ነው፡፡

ቀደም ብሎ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ አለመሆኑ በጣም እንደሚቆጨው የገለጸው አሸናፊ አበበ ይህም አገልግሎቱን በማለዳው አግኝቶ ብዙ ሥራዎችን መሥራት ያስችለው እንደነበር ይናገራል፡፡

ለለውጥ አይረፍድምና ሁሌም በጥረት ውስጥ ላለ ሰው ዛሬም ትልቅ ሀብት ነውና አሁን ላይ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ መሆን ከቻለበት ጊዜ ጀምሮ በቁጠባም በብድር አገልግሎትም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡ ይህም በሕይወቱ ላይ ብሎም በስራው ላይ ትልቅ ዕምርታ እንዲያሳይ አግዞታል፡፡

በቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚነት 4 ዓመት፣ በብድር አገልግሎት ተጠቃሚነት 2 ዓመት በደንበኝነት የቆየው አሸናፊ አበበ የፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ መላው ሰራተኞች ድጋፍና ክትትል ከፍተኛ መሆኑን ይገልጻል፡፡ የቅርንጫፉ ሰራተኞች ለቁጠባና የብድር አገልግሎት ድጋፍና ክትትል ከማድረግ ባለፈ የሥራ አማራጮችንም በማማከርም ትልቅ ዕገዛ አድርገውለታል፡፡ ከ150ሺ ብር ጀምሮ እስከ 400ሺ ብር ድረስ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ሲሆን ብድሩንም በአግባቡ በመክፈል በስራው ላይ ዕድገት ማሳየት ችሏል፡፡

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሚያሰራና ሰዎችን ለላቀ ስኬት የሚያንደረድር ተቋም ነው የሚለው አሸናፊ አበበ በቀጣይም ከተቋሙ ጋር በቅርበት በመስራት ውጤታማነቱን ለማስቀጠል ተግቶ እንደሚሰራ ይናገራል የምስጉን ደንበኛ ተሸላሚው የተምሳሌቶቹ ገጽ ዕንግዳችን፡፡

ሰዎች የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ በመሆን የቁጠባ ባህላቸውን በማዳበር ተግተው በመቆጠብ ከዚያም የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ጠንክረው ከሰሩ መለወጥ፣ማደግ እንደሚችሉ ከሕይወት ተሞክሮው በማካፈል መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ዜና| ስልጠና ተሰጠ   ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ በደንበኞች አገልግሎትና በተቋማዊ አሰራሮች ዙሪያ ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ...
10/01/2026

#ዜና| ስልጠና ተሰጠ
ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም

ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
በደንበኞች አገልግሎትና በተቋማዊ አሰራሮች ዙሪያ ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና የትኩረት ማዕከሉ አድርጎ ከሚሰራቸው አበይት ተግባራት መካከል የሰራተኞቹን አቅም የሚገነቡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ተከታታይና ወጥነት ባለው መልኩ መስጠት ነው፡፡

ይህን የአቅም ግንባታ ሥልጠናንም በማጠናከር ለተቋሙ ሰራተኞች በተቋሙ ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ ተሾመ አበበ በደንበኞች አገልግሎትና በተቋማዊ አሰራሮች ዙሪያ ለሰራተኞቹ ግንዛቤ የሚያስጨብጥና ለስራ እንቅስቃሴያቸው ግብዓት የሚሆን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የደንበኞች አገልግሎት ፅንሰሃሳብና ለደንበኞች የላቀ አገልግሎትን ከመስጠት አንጻር ሰራተኞቹ ምን ዓይነት ስብዕና መላበስ እንዳለባቸው በዝርዝር በስልጠናው ተዳሷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች በግለሰብ ደረጃ፣በተቋም ደረጃና በተለያየ አግባብ ለሚመጡ ደንበኞች አካውንት ለማስከፈት የሚጠበቁ ቅድመ-ሁኔታዎች እንዲሟሉ ከማድረግ አንጻር ከሰራተኞች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች ረገድና ከቼክ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ባሉ አሰራሮች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በ3ዙር ለ62 ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን በተመለከተ ያነጋገርናቸው ስልጠናውን የሰጡትና የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋናስራአስፈጻሚ አቶ ተሾመ አበበ ጥራት ያለውና የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለአንድ ተቋም የህልውናው መሠረት በመሆኑ ሰራተኞች ለደንበኞች ደረጃውን የጠበቀና ፈጣን፣ቀልጣፋና ደንበኛን የሚያረካ አገልግሎት መሥጠት ይችሉ ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መሠጠቱን ገልፀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም ስልጠናው ከተንቀሳቃሽ ቁጠባና ከቼክ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሰራተኞች የጠራ ግንዛቤ እንዲያገኙና የጠለቀ መረዳት እንዲኖራቸው የማድረግ ዓላማን ያነገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመለወጥና የዕለት ተዕለት የስራቸው አካል በማድረግ ጥራት፣ፍጥነትና ቅልጥፍና ያለው የላቀ የደንበኞች አገልግሎት በመስጠት ተቋሙ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የረካ ደንበኛ ለመፍጠር እያደረገው ላለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዘርፈ-ብዙ እንቅስቃሴዎችን ተቋማቸው እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተሾመ ይህን አገልግሎት በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ለመስጠት ደግሞ ተከታታይና ወጥነት ባለው መልኩ ሰራተኞችን ማብቃት የግድ የሚል ነገር በመሆኑ መሠል ስልጠናዎች በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ሰልጣኞችም ይህን ዓይነት ስልጠናዎች አቅማቸውን በመገንባትና በማብቃት ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆኑን በመግለፅ ስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 # እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ።             በፍቅር እናገለግሎታለን             ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ  ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም   Microfinance...
06/01/2026

# እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ።
በፍቅር እናገለግሎታለን
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ
ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተታግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ተምሳሌቶቹ   ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም                 "ያልቆጠብኩበት ጊዜ ይቆጨኛል"                             ቢልልኝ  አረቦየድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖ...
06/01/2026

#ተምሳሌቶቹ
ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

"ያልቆጠብኩበት ጊዜ ይቆጨኛል"
ቢልልኝ አረቦ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የማሽነሪ ሊዝ ደንበኛ
ወጣት ቢልልኝ የረጅም ጊዜ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ ነው፡፡ ቀደም ብሎ ከአራት ጓደኞቹ ጋር በጋራ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ ላይ ለብቻው የሚያስተዳድረው ትልቅ የወንዶችና የሴቶች ቤተውበት/ፀጉር ቤት/ ባለቤት ነው፡፡በቁጠባም በብድርም አገልግሎት ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ዕንግዳችን ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በቅርበት መሥራት በመቻሉና የተቋሙን አገልግሎቶች በሚገባ በመጠቀሙ ከእሱ የሥራ ታታሪነትና የሥራ ሥነምግባር ተደምሮ ከራሱ አልፎ ለሌሎች እንዲተርፍ ሆኗል፤ 30 ለሚጠጉ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የስራ ሃሳብ ኖሯቸው የፋይናንስ ችግር ለገጠማቸው ፍቱን መፍትሔ የሆነ ተቋም መሆኑን ወጣት ቢልልኝ ይናገራል፡፡ እሱም ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ባገኘው የፋይናንስ ድጋፍ የካበተ ሙያን ባዳበረበት የወንዶች የውበት /የፀጉር ማስዋብ ሥራ/ የእኔ የሚለው የራሱ ድርጅት ማቋቋም የቻለው፡፡ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ለስራው የሚሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት እና ድርጅቱ በሁለት እግሩ እንዲቆም በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ወጣት ቢልልኝ ይገልጻል፡፡

ለረዥም ጊዜ ቁጠባን እስከ አሁን ድረስ የቀጠለው ወጣት ቢልልኝ ጠንካራ የቁጠባን መሠረት መጣሉ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የብድር አገልግሎትን እንዲያገኝ ሁነኛ ሚና እንደተጫወተም ይጠቅሳል፡፡ የቁጠባ ባህሉን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለና እያጠናከረ ቢመጣም ያልቆጠብኩባቸው ጊዜያት ግን ይቆጩኛል ይላል፡፡
አሁን ስራውን በላቀ ደረጃ ለመሥራት እየተጋ ያለው የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛው ወጣት ቢልልኝ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ያለውን ደንበኝነት በማጠናከር ነገን ለሌላ ስኬት ነገን ከራስ ባለፈ ለብዙኃን ለመትረፍ ያልማል፡፡

ወጣቶች የዳበረ የሥራ ባህልንና ሥነምግባርን ስንቅ በማድረግ የፋይናንስ አቅርቦት ችግራቸውን ደግሞ ለወጣቶች ሁሌም በሩን ክፍት አድርጎ ቀልጣፋና ፈጣን የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በሚሰጠው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በመፍታት ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ከህይወት ተሞክሮው ያጋራል፡፡

ተግታችሁ ቆጥቡ! የምትሰሩትን ስራ ውጤታማነት በመመዘን የፋይናንስ ዕጥረት ሲገጥማችሁ ተበደሩ! ብድራችሁንም በአግባቡ ክፈሉ የማሳረጊያ መልዕክቱ ነው፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #ተምሳሌቶቹ   ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም      "ለስራችን ብርታት የሆነን ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው"                           ወ/ሮ ገነት ጥላሁንየድሬ ማይክሮ ፋይ...
01/01/2026

#ተምሳሌቶቹ
ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም

"ለስራችን ብርታት የሆነን ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው"
ወ/ሮ ገነት ጥላሁን
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ

በተምሳሌቶቹ አምዳችን የድሬ ማይክሮፋይናንስን በደንበኞቹና በዙሪያቸው ባሉ ቤተሰቦቻቸው ብሎም የስራ ዕድል በፈጠሩላቸው ሰዎች ዙሪያ ከየቅርንጫፎቻችን ያሉ ምስጉን ደንበኞችን አብነታዊ እንቅስቃሴ እያስቃኘናችሁ እንገኛለን፡፡ በዛሬው ጥንቅር የፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ የሆኑትን የወ/ሮ ገነት ጥላሁንን ተምሳሌታዊ ተሞክሮ እናካፍላችኃለን፡፡

ወ/ሮ ገነት የባህላዊ ቡና አቅርቦት የአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በዚህም ሥራ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ‹‹እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ›› በመሆን በጋራ በመስራት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠር የቻሉ ናቸው፡፡ከእነሱ ጋር በመሥራት የባህላዊ ቡና አቅርቦት አገልግሎቱን በደንብ በመቅሰም የራሳቸውን የጀመሩም አሉ፡፡

በሥራቸውም ትጋትን ሸማቸው በማድረግ፣ ስራቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግም በርካታ ደንበኞችን ማፍራት ችለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ብርታት ምንጭ ግን ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው ሲሉ ወ/ሮ ገነት ይናገራሉ፡፡

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ መሆናቸው በስራቸው ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ በመግለጽ ለተቋሙ ምስጋናቸውን ችረዋል፡፡ ከራሳቸውም አልፈው ለሌሎች ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻል ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ይገልጻሉ፡፡
ከባህላዊ ቡና አቅርቦት አገልግሎት በተጓዳኝ የወንዶች የውበት ሳሎን ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ገነት አሁን ላይ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ባገኙት ብድርም በመታገዝ ፎቅ ቤት እየሰሩ ነው፡፡

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በር ክፍት ነው ተቋሙ ያመቻቸውን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም መስራት፣ መለወጥ፣ ማደግ ይቻላልና እኛ ያገኘነው ዕድል እንዳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት ከእኛ ተሞክሮ ውሰዱ የሚለው ማሳረጊያ መልዕክታቸው ነው፡፡

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 #የሩጫ ውድድር  ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም"የሀገር ባለውለታ የሆኑትን ጀግኞች አባት እናቶቻችን አረጋውያንን ለመደገፍ እንሮጣለን"             የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ማኔጅመንት...
22/12/2025

#የሩጫ ውድድር
ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
"የሀገር ባለውለታ የሆኑትን ጀግኞች አባት እናቶቻችን አረጋውያንን ለመደገፍ እንሮጣለን"
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ማኔጅመንትና ሰራተኞች

"ኑ - አረጋውያንን ለመደገፍ እንሩጥ"
10ኛው የዳዊት ለአረጋውያን የሩጫ ውድድር እና የአብሮነት መድረክ!!
እኛ እናትና አባቶቻችን ለመደገፍ እንሮጣለን!
# አረጋውያንን ለመደገፍ ለ10ኛ ጊዜ ለተዘጋጀው የሩጫ ውድድር በመግዛት በዕለቱ እንገናኝ።
➤ቀን፦ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
➤ቦታ፦ ድሬዳዋ ምድር ባቡር

የአዋቂ ------ 300 ብር
የልጆች-----200 ብር

ዳዊት አረጋውያን መርጃ -- ዲፖ
ምድር ባቡር አደባባይ
➤ !!
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
09 13 35 32 91

Microfinance
ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት በሁሉም የሶሻል ሚዲያ አማራጮቻችን ይከተሉን፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/diremicrofinance/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/
ኢንስተታግራም፦ https://www.instagram.com/diremicrofinanceinstitution
በመወዳጅነትት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Dawit Aregawiyan Merja #ድሬዳዋ

Address

Diredawa
Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Micro Finance Institution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share