11/07/2024
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዛሬ በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ከከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሩ ጋር ባደረገው ግምገማ የድርጅቱ ስራዎች በውጤታማነት መከናወናቸው ተነስቷል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት ዶ/ር በሪሶ አመሎ እንደገለፁት መላው የኢባትሎ አመራርና ሰራተኛ በ2016 በጀት ዓመት ለተመዘገበው ውጤት የላቀ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
ዶ/ር በሪሶ አክለውም መላው የድርጅታችን አመራርና ሰራተኛ ድርጅቱ ያቀዳቸውን ስራዎች በውጤታማነት ለማከናወን በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራቱ ውጤቱ መመዝገቡን አንስተው የድርጅቱን ዓለማቀፋዊ ተወዳደሪነት ለመጨመር እና በገቢ ወጪ የንግድ ስርዓቱ የሎጀስቲክስ ስራዎች ላይ ያለውን ፋይዳ በላቀ መሰረት ላይ ለመገንባት በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እና ዲጂታል ኢ ኤስ ኤልን መተግበር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
በድርጅቱ የስራ አመራር ጉባዔ ላይ የተሳተፉት ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለውጤታማነታችን የአመራሩ ጠንካራ ድጋፍና ያላሰለሰ ክትትል ለውጤታማነት አብቅቶናል ያሉ ሲሆን ዕቅዳችንን ለጥጠን በማቀድ ለስኬታማነቱ ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል፡፡