02/07/2023
የአማራ ክልል የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ
ማኅበራዊዜና
የአማራ ክልል የተሟላ የከተማ ካርታ የሌላቸውን ይዞታዎች ሕጋዊ ሊያደርግ ነው መባሉ ጉዳዬን ሲከታተሉ ለነበሩ መልካም ዜና ቢሆንም ከቦታ ስፋት አወሳሰን ጋር ግን አዲሱ መመሪያ
በምሪት ለተጠቃሚ የተላለፉ የመኖሪያ ወይም ደርጅት ይዞታዎች የቦታ መጠን የሚወሰነው በምሪት ካርኒው ወይም ካርታ ላይ በተገለጸው የቦታ መጠን መሠረት ሲሆን፣ ካርኒው ወይም ካርታው ላይ የቦታ መጠኑ ካልተገለጸ በብሎኩ ውስጥ ባሉት አዋሳኞች የቦታ ሽንሻኖ መጠን መሠረት የሚፀድቅላቸው ይሆናል ይሆናል መባሉ ከፍተኛ የህግ ክፍተት ያለበት ነው።በምሪት ካርኒው ወይም ካርታ ላይ በተገለጸው የቦታ መጠን በልኬት ካለው ጋር ልዪነት ካለው ይህ እንዴት ይፈታል? በተለይ በመብለጥ ሆኖ ራስን ችሎ የማይለማ ሲሆን አንዴት ይፈታል? የቦታ ቅርፅ እንዴት ይጠበቃል ? የመንገድ ተደራሽነት በግልፅ የማያስቀምጥ በመሆኑ ለሙስና በር የሚከፍት ነው።
ኤልያስ ተገኝ
October 30, 2022
የአማራ ክልል የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ፣ በክልሉ የተሟላ የከተማ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌላቸው ይዞታዎችን ሕጋዊ የሚያደርግበት አዲስ አሠራር ዘረጋ፡፡
በክልሉ ከተሞች በሥራ ላይ የነበሩት የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሰነድ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 2/2005፣ 8/2007፣ እንዲሁም መመርያ 2/2011 በባህላዊ ግዥና በስጦታ የከተማ ቦታ የሚተላለፍበት መንገድ ለሕገወጥ አሠራር በር መክፈቱ አንዱ በምክንያትነት የተጠቀሰ ጉዳይ ሲሆን፣ ያንን ለማስተካከል የክልሉ የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ የተሻሻለ የአፈጻጸም መመርያ ማዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
የተሻሻለው መመርያ በከተማ አስተዳደሮች (ሪጂዮፖሊታን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ፈርጅ አንድ የከተማ አስተዳደር፣ ፈርጅ ሁለት የከተማ አስተዳደር) እንዲሁም በማዘጋጃ ቤት ከተሞች ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡
የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው፣ በአማራ ክልል በሥራ ላይ የነበረው የሰነድ አልባና ያልተሟላ ሰነድ አጣርቶ ማስተናገድ አገልግሎት በመቆሙ፣ ሕጋዊ የሆነ ከፊል የሰነድ ማስረጃ ያላቸው ባለ ይዞታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሳይስተናገዱ ቆይተዋል፡፡ ነዋሪዎች የከተማ ቦታ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጣቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እነዚህ ተገልጋዮች ባለመስተናገዳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፈጠሩ መመርያውን ማሻሻል አስ
በተሻሻለው መመርያ መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ይዞታ ስለመሆኑ የሚያስረዳ አግባብ ካለው አካል የተሰጠ የምሪት ካርኒ ወይም የግንባታ ፕላን፣ በሕጋዊ መንገድ (በምሪት) የተላለፈ ስለመሆኑ የተረጋገጠ የከተማ ቦታ የግብር ካርኒ ማቅረብ ከተቻለ ካርታ ማግኘት ይችላል፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የተሰጠ ካርታ ያለው ሆኖ በማዘጋጃ ቤት በኩል በደብዳቤ ተጠይቆ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ያልተወረሰ ስለመሆኑ፣ ከዞን መምርያ ማስረጃ ሲቀርብ እንዲሁ ካርታ የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በደርግ ዘመነ መንግሥት በምሪት የተገኘ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም የቤት ባለቤትነት ደብተር ካለው፣ ከላይ ከተጠቀሱት የሰነድ ማስረጃዎች አንዱን የሚያቀርብ፣ ይገባኛል ክርክር የሌለበትና ለዚህም ከከተማ ማዘጋጃ ቤት ወይም አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ማስረጃ የሚያቀርብ ባለይዞታ ሆኖ ለሦስተኛ ወገን የተላለፈና የባህላዊ ግዥ ወይም ስጦታ ውል ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ቤት የተሠራበት ይዞታ፣ ካርታ ለመስጠት ሊሟሉ የሚገባቸው አስፈላጊ ሰነዶች መሆናቸውን መመርያው ያትታል፡፡
በምሪት ለተጠቃሚ የተላለፉ የመኖሪያ ወይም ደርጅት ይዞታዎች የቦታ መጠን የሚወሰነው በምሪት ካርኒው ወይም ካርታ ላይ በተገለጸው የቦታ መጠን መሠረት ሲሆን፣ ካርኒው ወይም ካርታው ላይ የቦታ መጠኑ ካልተገለጸ በብሎኩ ውስጥ ባሉት አዋሳኞች የቦታ ሽንሻኖ መጠን መሠረት የሚፀድላቸው ይሆናል ተብሏል፡፡
መመርያው እንዳስቀመጠው በባህላዊ ስጦታ ወይም ሽያጭ ወደ ሦስተኛ ወገን የተላለፈ ይዞታ፣ ስጦታው ወይም ሽያጩ በተላለፈበት ወቅት በነበረው የሊዝ መነሻ ዋጋ መሠረት ወደ ሊዝ ሥርዓት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የይዞታ ማረጋጋጫ ካርታ ወደ ሊዝ ሥርዓት በገቡ ከተሞች ወደ ሦስተኛ ወገን ከተላለፉ ይዞታዎች በስተቀር በነባር ይዞታ ሥሪት የሚስተናገድ ሲሆን፣ ወደ ሊዝ ሥርዓት ባልገቡ ከተሞች ደግሞ ሁሉም ይዞታዎች በነባር ሥሪት አግባብ ተዘጋጅተው የሚሰጡ መሆኑን መመርያው ያስረዳል፡፡
በከተማ ፕላን ምደባ መሠረት ለጋራ አገልግሎት (ለስታዲየም፣ ለስፖርት ማዘውተሪያ፣ ለአረንጓዴ ቦታ፣ ለደን፣ ለገበያ፣ ለመንገድ፣ ለአምልኮ፣ ለማኅበራዊ አገልግሎት) በተመደበ ቦታ ላይ ተነሺ የሆኑ ሕጋዊ የይዞታ ባለቤቶች ከቦታ ተነሺ በሚሆኑበት ጊዜ፣ በካሳ ሕግ መሠረት መብታቸው የሚከበርላቸው ይሆናል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከተማው የከተማነት ዕውቅና ካገኘ በኋላ የተያዙና በተሻሻለው መመርያ መሥፈርቱን አሟልተው የቀረቡ ይዞታዎች እየተጣሩ እንዲፀድቁ የሚደረግ ሲሆን፣ ይዞታውን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ውዝፍ የከተማ ቦታ ኪራይ ክፍያ እንዲከፍሉ ተደርጎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኙ እንደሚደረግ በመመርያው ተመላክቷል፡፡
መመርያ መሬት አማራ
Previous article
ወደ ጥቅምት 15 የተቀየረው የመከላከያ ሠራዊት ቀን
Next article
ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ስምምነት ፈጸመች
- Advertisement -
Anbesa Insurance
Previous
Next
በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን
ከ ተመሳሳይ አምዶች
ማኅበራዊ
የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከግሎቹ እኩል ለማድረግ መታቀዱ ተገለጸ
ሔለን ተስፋዬ - July 2, 2023
የመምህራንን ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ በቀጣይ ይሠራል ተብሏል የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት በማሻሻል ከግል ትምህርት ቤቶች እኩል ለማድረግ፣ 50 ሺሕ ትምህርት ቤቶችን በሕዝባዊ ተሳትፎ እንደሚያሳድስ...
ዜና
ባለሥልጣናት በስማቸው የተመዘገበ የግል ድርጅትና የአክሲዮን ድርሻ እንዲያቋርጡ ወይም እንዲያስተላልፉ ሊገደዱ ነው
ኢዮብ ትኩዬ - July 2, 2023
የመንግሥት ባለሥልጣናት በግል ጥቅማቸውና በኃላፊነታቸው መካከል ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን መከላከልና ማስወገድ እንዲችሉ፣ በስማቸውና በቅርብ ቤተሰብ ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ኩባንያዎችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን እንዲያቋርጡ...
ዜና
ኢሠማኮ የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለፓርላማ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ
ሔለን ተስፋዬ - July 2, 2023
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለዓመታት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡ በአሠሪና...
ቢዝነስ
የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎችና ማደያዎች ግብይት ከሐምሌ አንድ ጀምሮ በዲጂታል ሊሆን ነው
ዳዊት ታዬ - July 2, 2023
የኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይት ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ ይቀይራል የተባለውና የነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ብቻ እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ የነዳጅ አቅርቦት አስተዳደር ሥርዓት፣ ከሐምሌ 1 ቀን...
ቢዝነስ
ከአዋጅ ውጪ መወረሱ ተረጋግጦ ለባለቤቶቹ እንዲመለስ ውሳኔ የተሰጠበት ይዞታ በድጋሚ ተወረሰ
ዳዊት ታዬ - July 2, 2023
ከአዋጅ ውጪ መወረሱ በመንግሥት እንዲሁም በፍርድ ቤት በተደረገ ክርክር ተረጋግጦ ለባለቤቶቹ እንዲመለስ ውሳኔና ትዕዛዝ የተሰጠበት ይዞታ፣ ለሕዝብ ጥቅም በሚል ምክንያት በድጋሚ ተወረሰ። የድሬዳዋ ዘርፍና ንግና...
ቢዝነስ
የኢትዮጵያና የጂቡቲ ጠረፍ ነጋዴዎች በወር ከአንድ ሺሕ ዶላር በላይ መገበያየት እንዳይችሉ ሊደረግ ነው
ሳሙኤል ቦጋለ - July 2, 2023
የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ጠረፍ ነጋዴዎች የወር መገበያያ ጣሪያ ሃያ ሺሕ ብር ሊሆን ነው የጂቡቲና የኢትዮጵያ ጠረፍ ነጋዴዎች በአንድ ወር መገበያየት የሚችሉት የምርት መጠን አንድ ሺሕ...
Zemen Bank AdvertisementZemen Bank Advertisement
Previous
Next
አዳዲስ ጽሁፎች
እኔ የምለዉ
ዜጎችን ማጎሳቆል እስከ መቼ ይቀጥላል?
አንባቢ - July 2, 2023
በቤኪ ዘሌ አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመራው መንግሥት አገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ ያቃተው ከመሆን ባለፈ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈንና በመርገጥ...
እኔ የምለዉ
ግለ ግምገማ አገር እንድትለማ
አንባቢ - July 2, 2023
በገብሬ ይንቲሶ ደኮ (ፕሮፌሰር) ኢትዮጵያ በግጭትና በኑሮ ውድነት የተነሳ ፈታኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች። ሰዋዊ ባህሪያት ክፉኛ ተሸርሽረው ለማሳብ የሚዘገንን የጭካኔና የግፍ ጥግ ማየትና መስማት እየተላመድን...
ተሟገት
የኢትዮ ቴሌኮም የፓርላማ ሪፖርት ጥያቄና ማብራሪያ በሰብዓዊ መብቶችና በሕግ የበላይነት ዓይን
አንባቢ - July 2, 2023
በገነት ዓለሙ ከአምባገነንነት ወጥቶ ወደ ዴሞክራሲ ለመግባት፣ በመንበረ መንግሥቱ አውታራት ላይ የደረሱ ብልሽቶችን ለማስወገድ፣ በአስተሳሰብና በማኅበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ የተፈጠሩ አደጋዎችን ለማስወገድ የተጀመረው ለውጥ አንዱ ምልክት...
ማኅበራዊ
የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከግሎቹ እኩል ለማድረግ መታቀዱ ተገለጸ
ሔለን ተስፋዬ - July 2, 2023
የመምህራንን ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ በቀጣይ ይሠራል ተብሏል የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት በማሻሻል ከግል ትምህርት ቤቶች እኩል ለማድረግ፣ 50 ሺሕ ትምህርት ቤቶችን በሕዝባዊ ተሳትፎ እንደሚያሳድስ...
ቆይታ
‹‹በትግራይ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶች እስኪጠገኑ እንጠብቅ ብንል ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ሊያስፈልግ ይችላል›› ኪሮስ ጉእሽ (ዶ/ር)፣ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
ዮናስ አማረ - July 2, 2023
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በኮሮናና በጦርነት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት ምዝገባ እንደሚጀምር ያስታወቀው ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ነበር፡፡ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም....
አስተያየት
የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ! ክልልነቱንስ ያገኙታል አደራውን ግን ለማን ይሰጡታል?
አንባቢ - July 2, 2023
በያሬድ ነጋሽ መግለጫ በምርጫ አስፈጻሚነት ሥራ ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ግለሰብ ቦርዱ በኃላፊነት ከሰጠው ተግባር ውጪ ስለምርጫው ሒደትና ውጤት፣ በተለይም ምርጫ ቦ
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ።
የደሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የተሟላ የከተማ ይዞታ ማረጋገጫ ወረቀት (ካርታ) የሌላቸውን ይዞታዎች ህጋዊነት ለመስጠት ተሻሽሎ በወጣው የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 4/2015 ላይ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና ሰጠ።
"ከተማችን ላይ የሚገኙ ካርታ የሌላቸው ይዞታወችን ወደ ህጋዊ ማእቀፍ ለማስገባት በቀጣይ ከምንሰራባቸው የትኩረት አቅጣጫወች አንዱ በመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ተሻሽሎ የወጣውን የአፈጻጸም መመሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና መስጠት አስፈልጓል" ሲሉ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘው እንደገለጹት ሰነድ አልባ የሆኑ የከተማችን ይዞታወች ወደ ህጋው ማእቀፍ ለማስገባት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላት መመሪያውን መሰረት በማድረግ ወደስራ እንዲገቡ እና የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሲሉ አሳስበዋል።
የተሟላ የከተማ ይዞታ ማረጋገጫ ወረቀት (ካርታ) የሌላቸውን ይዞታዎች ህጋዊነት ለመስጠት ተሻሽሎ የወጣውን የአፈፃፀም መመሪያ አቶ አዱኛ ካሴ በአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ መሬት ልማት ማኔጅመንት ዳይሮክትሬት የመሬት ይዞታ አስተዳደር ቡድን መሪ አቅርበዉ በመመሪያው ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት አቶ ሞላ ሁሴን የደሴ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ እንደገለጹት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያለው ባለድርሻ አካላት በተለይ አመራራችን ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ በማስተግበር በኩል በቁርጠኛነት ወደስራ እንዲገባ እና የተጣለበትን ሀላፊነት ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።