25/02/2026
ውድ ተማሪዎቼ፤
ዛሬ አንድ ቀላል ነገር ግን ወሳኝ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እፈልጋለሁ።
የወደፊት ህይወታችሁን በምናባችሁ በግልጽ አይታችሁት ታውቃላችሁ?
ሕልም አልማችሁ ወይም ተመኝታችሁ ታውቃላችሁ ወይ እያልኳችሁ አይደለም፤ በአእምሮአችሁ (በምናባችሁ) በግልጽ አይታችሁት ታውቃላችሁ ወይ እያልኳችሁ ነው።
አሁን ዓይናችሁን ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ጨፍኑ። ራሳችሁን ከአሥር ወይም አስራ አምስት ዓመታት በኋላ አስቡት።
የት ናችሁ?
ምን ዓይነት ሰው ሆናችኋል?
ለቤተሰባችሁ፣ ለማህበረሰባችሁ፣ ለአገራችሁ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አምጥታችኋል?
በዚህ ዓለም ያለ ታላቅ ነገር ሁሉ ሁለት ጊዜ ይፈጠራል። መጀመሪያ በአእምሮ ውስጥ፣ ከዚያም በእውነታ። ሕንፃ ከመቆሙ በፊት እቅድ ይሰራለታል። ድልድይ ከመገንባቱ በፊት በሐሳብ ይታሰባል። በተመሳሳይ መልኩ ሕይወታችሁ እውን ከመሆኑ በፊት በመጀመሪያ በምናባችሁ መገንባት አለበት።
መድረሻችሁን ካልወሰናችሁ፣ ሕይወት ራሷ ትወስንላችኋለች።
ስቴቨን ኮቪይ የሚባል አንድ ዝነኛ ፀሐፊ በፃፈው "The 7 Habits of Highly Effective People" በሚል ድንቅ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰ ድንቅ ሐሳብ አለ። “በአእምሮአችሁ ከመጨረሻው ጀምሩ።” ይላል። ይህ ማለት መራመድ/መሄድ ከመጀመራችሁ በፊት መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማወቅ አለባችሁ ማለት ነው።
መድረሻውን የማታውቁት አውቶቡስ ላይ መሳፈርን አስቡት። ለሰዓታት ልትጓዙ ትችላላችሁ፤ ግን የምትፈልጉበት ቦታ አትደርሱም። ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን በዚህ መልኩ ያሳልፋሉ—ጊዜ የላቸውም ወይም busy ናቸው ፣ ይደክማሉ፣ ይሮጣሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱበትን አቅጣጫ አያውቁም።
ውድ ተማሪዎቼ፣ ያለአቅጣጫ ጊዜያችሁን አታባክኑ።
ወደፊታችሁን በምናባችሁ ስታዩ ድንቅ የሆነ ነገር ይፈጠራል።
👉 ግቦቻችሁ ግልጽ ይሆናሉ።
👉 የእለት ተለት ተግባራችሁ ትርጉም ይኖረዋል።
👉 የምትከፍሉት መስዋትነት ዋጋ ያገኛል።
👉 ትጋታችሁ ይጨምራል።
ወደፊት ራሳችሁን ሐኪም፣ መሐንዲስ፣ መምህር፣ የንግድ ሰው፣ መሪ ወይም ተመራማሪ ሆናችሁ ስታዩ፣ የቤትም ሆነ የክፍል ሥራን እንደ ሸክም አታዩትም፤ እራሳችሁን ብቁ እንደምታደርጉበትና አእምሮአችሁ እንደምታሰለጥኑበት ታዩታላችሁ። ፈተናን እንደ ቅጣት ሳይሆን፤ ለወደፊቱ ህይወታችሁ እንደ መዘጋጃ ታዩታላችሁ።
እስቲ አስቡት! መሆን የምትፈልጉትን ሰው በምናባችሁ/በአእምሮአችሁ በግልፅ ካያችሁት ጊዜያችሁን በግድየለሽነት ታባክናላችሁ? ትኩረት የሚያሳጣችሁን ነገር ትከተላላችሁ? በቀላሉ ተስፋ ቆርጣችሁ ታቆማላችሁ? አታደርጉትም! ምክንያቱም ዛሬ የምትወስኑት እያንዳንዱ ውሳኔ ወደፊት መሆን ከምትፈልጉትና በምናባችሁ ካያችሁት ማንነትና ህይወት ጋር ታነፃፅሩታላችሁ።
አንዳንዶቻችሁ ከአስቸጋሪ አካባቢ መጥታችሁ ሊሆን ይችላል። አንዳንዶቻችሁ የገንዘብ ችግር ሊኖርባችሁ ይችላል። አንዳንዶቻችሁ ራሳችሁን ልትጠራጠሩ ወይም በራሳችሁ እምነት ልታጡ ትችላላችሁ። ግን አስታውሱ፤ አሁን ያለችሁበት ሁኔታ መጀመሪያችሁ እንጅ መጨረሻችሁ አይደለም።
📌 ግልጽ ራዕይ አሁን ካላችሁበት ማንኛውም ሁኔታ ይበልጣል።
ወደፊታችሁን በምናባችሁ ስታዩ፦
👉 በራስ መተማመን ስሜት ስትመረቁ ራሳችሁን እዩ።
👉 ወላጆቻችሁ በእናንተ ሲኮሩ ራሳችሁን እዩ።
👉 በምትሰማሩበት ዘርፍ ለሃገራችሁ እድገት አስተዋፅኦ ስታደርጉ ራሳችሁን እዩ።
👉 ችግሮችን ስትፈቱ፣ ለሌሎች እድል ስትፈጥሩ፣ የእናንተ ስኬት ሌሎችን ሲያነሳሳ ራሳችሁን እዩ።
የወደፊት ማንነታችሁ የአሁኑን ባህሪያችሁን እንዲመራ አድርጉ።
ነገር ግን አንድ አስፈላጊ የሆነ እውነታን ምንጊዜም አስታው