Gondar Commission Agent

Gondar Commission Agent Online house and car selling, buying & renting solution @ Gondar, Ethiopia

ማንኛውም ቤት፣ቤት መስሪያ ቦታ፣ሕንፃ፣ኮንዶሚንየም፣መጋዘን፣መኪና ... መግዛት/መሸጥ እና ማከራየት/መከራየት ሲፈልጉ ይደውሉልን እንዲሁም ካለ ያስመዝግቡ ... መረጃ ገንዘብ ነውና መረጃ ይስጡ/ይውሰዱ ከእኛ ጋር በመስራት 2% ያግኙ እናመሰግናለን::

~~~ቅንነት የክፉ ቀን ስንቅ~~~እንዲህ እንደዋዛ ቀን ሳይጥላት በፊት ህንድ ውስጥ በምትገኝ ኪራላ በምትባል ከተማ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሂሳብ መምህርት ነበረች።አንድ ቀን የቀድሞ ተማ...
21/07/2025

~~~ቅንነት የክፉ ቀን ስንቅ~~~
እንዲህ እንደዋዛ ቀን ሳይጥላት በፊት ህንድ ውስጥ በምትገኝ ኪራላ በምትባል ከተማ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሂሳብ መምህርት ነበረች።አንድ ቀን የቀድሞ ተማሪዋ ባቡር ልትሳፈር ተሰልፋ ዘወር ስትል ከአመታት በፊት የሆነ ቦታ የምታውቀው ፊት ጋር ተገጣጠመች።

ይሄንን ኑሮ ያጎሳቆለውን የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር የተፈራረቁበትን ፊት የት እንደምታውቀው ለማስታወስ ብዙ ጥረት ካደረገች በኋላ የቀድሞ ሂሳብ መምህሯ መሆኗን አስታወሰች።

ተማሪዋም ከሰልፉ መሀል ፈጠን ብላ በመውጣት ይቅርታ "አድርጊልኝ እና አንቺ ሂሳብ አስተማሪ አልነበርሽምን?" አለቻት መምህርትም መለሰች አዎ ከአመታት በፊት የሂሳብ አስተማሪ ነበርኩ ነገር ግን ጡረታ ስወጣ ደሞዜ ለኑሮ በቂ አልነበረም ድህነት እና እርጅና ሲጫኑኝም ልጆቼ ጥለውኝ ሄዱ።አሁን ጭራሹን ደብዛቸው ጠፍቱዋል የት እንደደረሱም አላውቅም እኔም ይሄው ከባቡር ጣብያ ደጃፍ ምጽዋት እየለመንኩ የእለት ኑሮዬን እገፋለሁ ብላ መለሰች።
ተማሪዋም ልጅ እያለች የአስተማሪዋን ቅንነት እና ለተማሪዎቹዋ የነበራትን ፍቅር ባሰበች ግዜ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።በአንድ እጁዋ እንባዋን እየጠረገች በአንድ እጅዋ መምህሩዋን ይዛ ወደቤቱዋ ተመለች።የመምህሩዋን ገላ አጥባ ልብሱዋን ቀይራ የእለት ጉርስም ሰጠቻት።ከዛም በሁዋላ ድሮ አብረዋት የተማሩትን ተማሪዎች በማስተባበር የመኖሪያዋን እና ለኑሮ የሚያስፈልጋትን ሁሉ አመቻቹላት።
የራሱዋ ልጆች ቢሸሹዋትም ያስተማረቻቸው ልጆች ደረሱላት።ቅንነት እና በየተሰማሩበት መልካምን ሰርቶ ማለፍ የክፉ ቀን ስንቅ ይሆናል።

ሞኝ ሰው ይበቀላል፣ አዋቂ ሰው ይቅር ይላል፣ጥበበኛ ሰው ነገሩን ይተዋል።  | ከዕለታት አንድ ቀን ኔልሰን ማንዴላ ከሚኒስትሮቻቸው ጋር ሆነው በእግራቸው እየተጓዙ ከተማውን ይጎበኙ ነበር፣ ከ...
09/07/2025

ሞኝ ሰው ይበቀላል፣ አዋቂ ሰው ይቅር ይላል፣ጥበበኛ ሰው ነገሩን ይተዋል።

| ከዕለታት አንድ ቀን ኔልሰን ማንዴላ ከሚኒስትሮቻቸው ጋር ሆነው በእግራቸው እየተጓዙ ከተማውን ይጎበኙ ነበር፣ ከተማዋን ሲቃኙ ይቆዩና አንድ ምግብ ቤት አካባቢ ሲደርሱ፣ «እስቲ እዚህ ቤት ገብተን ምግብ እንብላ›› ይሉና ወደ ምግብ ቤቱ ይገባሉ፤ ምግብ ቤት ውስጥ አንድ ጥግ ይዞ ምግብ የሚመገብ በቀለሙ ነጭ የሆነ ሰው ነበር፣ ሰውዬው ፕሬዝዳንቱን ሲያይ ከመደንገጡ ብዛት እጁ መንቀጥቀጥ ጀመረ፣ ምግቡን መመገብ አልቻለም፤ ሁለቱም እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ፤ላብ በላብ ሆነ።

ይህንን ያዩት ማንዴላ ከጠባቂዎቻቸው አንዱን ጠርተው «እዚያ ጥግ ያለውን ሰው ጥራው አሉት!››

ሰውዬውም የባሰ እየተርበተበተ ወደ ማንዴላ መጣ፣ ከተቀመጡበት ተነስተው ጨብጠው እንዲቀመጥ ወንበር አመላከቱት።በደመ ነብስ ተቀመጠ፤ምግብ እንዲያዝ አድርገው ምሳ አብረው በልተውና አጫውተውት በከብር ይሸኙታል።

አብረዋቸው ከነበሩ ሚኒስትሮች አንዱ ወደ ኔልሰን ማንዴላ ጠጋ ብሎ ክቡር ፕሬዚደንት የቅድሙን ሰውዬ ያውቁታል? ያመዋል መሰለኝ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር! ሲላቸው፣

እዎ አውቀዋለሁ እኔን ሲያይ ደንግጦ ነው እንደዚያ የሆነው፤ ያኔ እስር ቤት በነበርኩበት አስከፊ ጊዜ ጠባቂዬ ነበር፤ አንድ ቀን ውሃ እንዲሰጠኝ ጠይቄው እሱ ግን ጭንቅላቴ ላይ ሽንቱን ሸንቶብኝ ነበር ያንን አስታውሶ ነው መሰለኝ፣ ዛሬ በተራው ይበቀለኛል ብሎ ፈርቶ ነው» አሉት!!

ሚኒስትሩም ፈጠን ብለው ለምን አናስረውም?›› ሲላቸው፣ ኔልሰን ማንዴላ ቀና ብለው ሚኒስትሩን እያዩ ትንሽ እንደመቆጣት ብለው፣ «እኔ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አልመለስም እሱን ተበቀልኩ ማለት ደግሞ ጉዞዬ ወደ ኋላ ተመለሰ ማለት ነው›› አሉት።

📌ሞኝ ሰው ይበቀላል፣አዋቂ ሰው ይቅር ይላል፣ጥበበኛ ሰው ነገሩን ይተዋል።"

#ኢትዮጵያዊነት #

ትንሽ ስለ ንቦችንቦች 3 ዓይነት ናቸው። እነሱም፦♦️ ንግስት  ንብ (Queen Bee)♦️ ድንጉላ ንብ (Drone Bee)♦️ ሰራተኛ ንብ (Worker Bee) ናቸው።👉 ንግስት ንብ እና ሰራተ...
25/05/2025

ትንሽ ስለ ንቦች

ንቦች 3 ዓይነት ናቸው። እነሱም፦
♦️ ንግስት ንብ (Queen Bee)
♦️ ድንጉላ ንብ (Drone Bee)
♦️ ሰራተኛ ንብ (Worker Bee) ናቸው።

👉 ንግስት ንብ እና ሰራተኛ ንብ ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ ድንጉላ ንብ ደግሞ ወንድ ነው።

♦️ ንግስት ንብ
👉 የመንጋው አለቃ ናት
👉 በመጠኗ ከሁሉም ትበልጣለች
👉 ስራዋ እንቁላል መጣል ሲሆን በቀን እስከ 2000 እንቁላል ትጥላለች
👉 ዕድሜዋ ከ5-7 ዓመት ነው
👉 ንግስት ንብ ስትሞት ወይም ስትታመም ሰራተኛ ንቦች በ14 ቀናት ውስጥ ከእንቁላሎቹ የተወሰኑትን በመምረጥ የተለየ ምግብ ይመግቧቸውና የንግስና ተፈጥሮ ያላት ስትወለድ ንግስት ያደርጓታል። ተመሳሳይ ወቅት ሌላ ንግስት ከተፈለፈለች ደግሞ ሁለቱ ንግስቶች እስከ ሞት ይፋለሙና ያሸነፈችው ትነግሳለች።

♦️ ድንጉላ ንብ
👉 በመጠኑ ከንግስት ንብ ያንሳል
👉 ትልልቅ ዓይኖች ያሉት ሲሆን ይህም ንግስቷን ለመለየት ነው።
👉 አይናደፍም
👉 ስራው ከንግስት ንብ ጋር ግንኙነት ማድረግ ብቻ ነው
👉 ግንኙነት የሚያደርገውም አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ግንኙነት ካደረገ በኋላ መራቢያ አካሉ ከአንጀቱ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ከንግስቷ ለመላቀቅ ሲሞክር አንጀቱ ተበጥሶ ይሞታል።
👉 በክረምት ጊዜ በቂ ምግብ ስለማይኖር ከቀፎው ይባረራል። በበጋ ወቅት ደግሞ ምግብ ስለሚኖር ቁጥሩ ይጨምራል።
👉 ዕድሜው ከ1-2 ወር ነው

♦️ ሰራተኛ ንብ
👉 በመጠኗ ከሁሉም ታንሳለች
👉 ስራዋ ማር መስራት፣ ቤት ማፅዳት፣ የሚፈለፈል እንቁላሉን መመገብና ንግስቷን መንከባከብ ነው።
👉 በየቦታው አበባ ሲቀስሙ የምናያቸው ንቦች ሁሉ ሰራተኛ ንቦች ናቸው።
👉 ከወንዱ ድንጉላ ንብ ጋር ግንኙነት አታደርግም
👉 ጠላት ሲመጣ ትናደፋለች። በዚህም መንደፊያ አካሏ ከአንጀቷ ጋር የተጣበቀ በመሆኑ ከነደፈች በኋላ በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለች። የማር ንብ ካልሆነች ግን በአንድ ንድፊያ ላትሞት ትችላለች።
👉 ዕድሜዋ በክረምት ስራ ስለማይበዛ እስከ 9 ወራት ስትኖር በበጋ ደግሞ ስራ ስለሚበዛባት 2 ወር ሳይሞላት በድካም ትሞታለች።

«ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ። ❝ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ። ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ። የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።❞ ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል። በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት።»
(አን-ነህል 68-69)

ሰልማን

28/02/2025

432 Followers, 2925 Following, 0 Likes - Watch awesome short videos created by Biniyam Serebe

ስልክ ተደውሎልን ስልኩን አንስተን  በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello'  ማለት ምን ማለት ነው ግን 'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ የተወሰነ ሰው ስም እንደሆነ ሲያውቁ ብ...
20/02/2025

ስልክ ተደውሎልን ስልኩን አንስተን በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello' ማለት ምን ማለት ነው ግን

'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ የተወሰነ ሰው ስም እንደሆነ ሲያውቁ ብዙዎችን ሊያስገርም(ሊያስደንቅዎ) ይችላል። 'Hello' በእውነቱ የአሌክሳንደር ግርሃም ቤል እጮኛዋ Margaret Hello ስም ነበር። የስልክ ፈልሳፊው ቤል በፈጠራው

የመጀመሪያ ሙከራ ወቅት ''Hello' ን እንደ መጀመሪያው ቃል ተጠቅሟል። ይህ ቀላል ንግግር እስከ ዛሬ ድረስ ስልኩን ስናነሳ እንደ ሰላምታ ጸንቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስልክ ጥሪዎች መደበኛ መክፈቻ ሆነ።

Telegram: https://t.me/samiauto1

ሰውዬው አዲስ መንጃ ፈቃድ ላወጣችው ሚስቱ የደስ ደስ አውቶማቲክ መኪና ገዛላት። ሚስትዬዋ ጓደኞቿን ለማስቀናት  በጠዋት መኪናዋን ይዛ ወጣች። ማታ ላይ መኪናዋን ካቆመችበት አስነስታ ለመንዳት...
17/02/2025

ሰውዬው አዲስ መንጃ ፈቃድ ላወጣችው ሚስቱ የደስ ደስ አውቶማቲክ መኪና ገዛላት። ሚስትዬዋ ጓደኞቿን ለማስቀናት በጠዋት መኪናዋን ይዛ ወጣች።

ማታ ላይ መኪናዋን ካቆመችበት አስነስታ ለመንዳት ተቸገረች። በዚህ ተናደደችና ባሏ ጋ ደወለች።

"ሃሎ! መኪናዋ አልሄድ አለችኝ"

"ለምን ? አዲስ መኪና ነች እኮ!"

"አላውቅም! ሜካኒክ ላክልኝ"

"ቆይ ቆይ! ትክክለኛው ማርሽ ላይ ነው ያደረግሽው?"

"ያን ያህል ጀዝባ መሰልኩህ እንዴ? ማርሹን ቀን 'D' ላይ ማታ ደግሞ 'N' ላይ አድርጌ መጠቀም አለብኝ"

"ለምን?

"D ማለት Day ማለት ሲሆን N ማለት ደግሞ Night ማለት አይደል?"

እንዲህ ዓይነት ፈተና ነው የገጠመን። ምንም ሳያውቁ እናውቃለን በሚሉ ህይወት የተወሳሰበችባቸው ሰዎች ነውኮ....."በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ነገሮች ውስብስብ ብለዋል...ብቻ ሀገራችንን ሰላም ያርግልን" አለ አንድ ወዳጄ🥰🤗

እንቁራሪቷ ኩሬ ውስጥ ሆና 'እዚያ ማዶ ያለው ከተማ ይቃጠላል' እያለች ትጨነቃለች።እንደ አጋጣሚ አንድ ሰው በአጠገቧ ሲያልፍ 'ወዳጄ ለፖሊስ ልትደውልልኝ ትችላለህ?' ትለዋለች...ሰውየውም ገ...
22/01/2025

እንቁራሪቷ ኩሬ ውስጥ ሆና 'እዚያ ማዶ ያለው ከተማ ይቃጠላል' እያለች ትጨነቃለች።

እንደ አጋጣሚ አንድ ሰው በአጠገቧ ሲያልፍ 'ወዳጄ ለፖሊስ ልትደውልልኝ ትችላለህ?' ትለዋለች...ሰውየውም ገርሞት 'ምን ሆንሽ ብዬ ነው የምደውውልልሽ?' ይላታል።

'ኧረ ባክህ እዛ ማዶ ሰደድ እሳት ተነስቷል ብለህ ደውል' አለችው።

ሰውየውም 'እሳቱ ያለው እዛማዶ አንቺ ምን አስጨንቆሽ ነው ደውል የምትይኝ?' አላት።

'አየህ እሳቱን እዚያ እያለ ካላቆምነው እዚህ ይመጣል። ያንዱ መቃጠል የኹላችን መቃጠል ሆኖ ካልተሰማን በኋላ መከራው ለኹላችን ይተርፋል" ትለዋለች።

ሰውዬውም አንቺ ያለሽው ውሃ ውስጥ እንዴት እሳቱ ያገኝሻል? አላት።

"እነዚያ ሰዎች እኮ እሳቱ ከባሰባቸው ውሃ ለመቅዳት ይመጣሉ። ያንጊዜ እኔን አብረው ጨልፈው ሊወስዱኝ ይችላሉ።" ስትል ትመልስለታለች።

"ቀልደኛነሽ" ብሏት ትቷት ይሄዳል.....

ወደ ማዶ አሻግረህ የምታየው የሌሎች ችግር አንድ ቀን ወደ አንተ ቤት ይገባል ...የሰዎችን ችግር እያይህ አትለፍ። የሰዎችን ችግር ስትፈታ የራስህን ችግር እያራክ መሆኑን ዕወቅ ❤
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ
Via Haileyesus Desta

የባለጌ ነገር========ባልና ሚስት ለሽርሽር በወጡበት አንድ የእንስሳት ባለ እርባታ ይጎበኛሉ።ሚስት የእርባታውን ባለቤት ይህ ኮርማ በቀን ስንት ነው የሚሳረረው [የባለጌ ነገር የሚያደርገው...
21/01/2025

የባለጌ ነገር
========
ባልና ሚስት ለሽርሽር በወጡበት አንድ የእንስሳት ባለ እርባታ ይጎበኛሉ።ሚስት የእርባታውን ባለቤት ይህ ኮርማ በቀን ስንት ነው የሚሳረረው [የባለጌ ነገር የሚያደርገው] ብላ ትጠይቀዋለች።ማነጀሩም፦"በቀን 5 ወይም 6 ጊዜ!"ይላታል።ሚስቱ ወደ ባሏ የጎሪጥ እያየች "ሰማህልኝ አይደል!?" ትለዋለች።

ባል እዚያ በቆሙበት አስተዳዳሪውን፦"ከአንድ ላም ጋር ነው ወይስ ከተለያዩ ላሞች ጋር!?" ይለዋል።አስተዳዳሪው፤"...ከተለያዩ ላሞች ጋር ነው" መለሰ።

"ሰማሽልኝ አይደል!?"

3ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረ።...እሳት መንደድ ጀመረ!

ጦርነቱን ማን ለኮሰው!?..😀

26/10/2024

Gondar (Gonder) in Ethiopia 🇪🇹 is often referred to as 'The Camelot of Africa' and is home to several splendid castles. The place was the capital of the Kingdom in the 17th and 18th Centuries.

Address

College Mazoria
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Commission Agent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share