12/05/2026
#ትራምፕ ኤርትራ ለኢትዮጵያ የባህር በር እንድትሰጥ ,ሀገራቱን ለማስማማት እየጣሩ መሆኑ ተነገረ!!!
@ትራምፕ በኢትዮጵያ በኤርትራ ና በግብፅ ዙሪያምን አዲስ ስምንነት ለመፍጠር የእየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለፀ።የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ ላይ የጀመረው አዲስ የዲፕሎማሲ አካሄድ የቀጠናውን ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ እያነቃነቀው ይገኛል።
@ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ በኤርትራ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት መወሰኗ፣ ዋሽንግተን ለአስመራ ያላትን አመለካከት በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ያሳያል። የትራምፕ ዋነኛ ግብ የቀይ ባህርን ስልታዊ ጠቀሜታ እና የቀጠናውን የአሜሪካ ጥቅም ማስከበር ነው።
በዚህም የአሜሪካና ኤርትራን ግንኙነት ማሻሻል, ከኢትዮጵያ ጋር ከሚደረገው አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው።
@ትራምፕ በአንድ በኩል ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በማደስ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር መፈለጉ አሜሪካ በቀጠናው ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምታደርገው ጥረት አካል ነው። በአጠቃላይ፣ የትራምፕ "ጥቅምን መሰረት ያደረገ ዲፕሎማሲ" በቀድሞ የዲፕሎማሲ መሰናክሎች ሳይገደብ በአፍሪካ ቀንድ ላይ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ እየከፈተ መሆኑን ያሳያል።
👉የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነት
" ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታትና ሁኔታዎችን በማርገብ ረገድ የምትጫወተው ቁልፍ ሚና የሚደነቅ ነው " - የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
@የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን (ዶ/ር) ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት የደህንነት አጋርነት እና የንግድ ዕድሎችን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይና በተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
@የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታትና ሁኔታዎችን በማርገብ ረገድ የምትጫወተውን ቁልፍ ሚና እንዳደነቁ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
@በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በትብብር መስኮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ውይይት ማዕቀፍ (BSD) በዋሽንግተን ዲ.ሲ ተፈርሟል።
@ስምምነቱን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የአሜሪካ የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር አሊሰን ሁከር የፈረሙት ሲሆን፤ ማዕቀፉ በዋናነት ፦
- በኢኮኖሚ ብልጽግና፣
- በንግድና ኢንቨስትመንት፣
- በመከላከያና ደህነት፣
- በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ በትኩረት ለመስራት ያለመ ነው።
@አሜራካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ አየሰራች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማስማማት እየጣረች ትገኛለች።
👉አሜሪካ ከኢትዮጵያ ምንድነው የምትፈልገው ?
አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትፈልገው ዋንኛው ነገር ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ለግብፅ ዋስትና እንድትሰጥ ነው , ይሄ የዋስትና ጥያቄ ግብፅ ለዓመታት ከኢትዮጵያ ስትጠይቀው የነበረና በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያ በማስገደድ አስገዳጅ ስምምነቶችን እንድትፈርም ለማረግ ስትጥር የነበረች ሲሆን ኢትዮጵያ ይሄን የግብፅን ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅሜን ይጎዳል በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ ስታደርግ እንደነበር የሚታወስ ነው።
Esat tv