Dinu man

Dinu man Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dinu man, Business service, Harbu.

19/05/2022

እንኳን እርሳቸው እኔም ደንግጫለሁ‼
=========================
✍ ባለፈ ሰኞ ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የመጅሊሱ ስብሰባ ላይ 105 ሰዎች ታድመው ነበር። በዕለቱ ከታደሙት ሰዎች መካከል አንዱ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ሲሆን ኪታቦቹን ይዞ ወደ አዳራሹ ገና ሲገባ የመጅሊሱ ጊዚያዊ ጸሐፊ ጠበቃ ቃሲም ታጁዲን ይመለከቱትና በጣም ደንግጠው ወደ ዶ/ር ጀይላን ጋር በመሄድ «ከነ ኢልያስ ጋር አንድ ላይ ናችሁ እንዴ? በፊት አትስማሙ አልነበረም እንደ? እንዴት እነሱን ጠራችኋቸው?» ብለው ጠይቀው ነበር አሉ። (ሐሜት አይደለም! ከውስጥ ካገኘሁትን መረጃ ነው ያካፈልኳችሁ ብሏል ሚር ሸምሱ!)

እውነት ለመናገር ላለማካበድ እኔ ራሱ በቪድዮው ላይ ስመለከት ፊት ለፊቱ ያከማቻቸውን ኪታቦች ይዞ ያየሁት ጊዜ ትንሽ ደንግጫለሁ። ለዛ ውይይት የሐፈዘው ይበቃው ነበር እኮ!
አስቡት! በጠበቃ ቃሲም ታጁዲንና በነ "ሐጂ" ዑመር ቦታ ሆናችሁ! ሸይኹ ኪታብ ይዞ ሲገባ የሚሰማቸውን ስሜት!

ጭራሽ ደቂቃው በትንሹ 15 ደቂቃ ቢሰጠው ኖሮ፤ እነ ዑመር ኮምቦልቻ ራሱ እንደ "ሐጂ" ዑመር «ሰለፊይ ያልሆነ ሙስሊም አይደለም!» ብለው መስክረው ሊወጡ ይችላሉ¡
«አሽዓሪያ ማቱሪዲያ ወይስ ሰለፊያ?» በሚለው ነጥብ ላይ ዶ/ር አቡበከር ሱለይማንና ዑመር ኮምቦልቻ ላነሱት ሃሳብ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በዚህ መልኩ ነበር አጥጋቢ ምላሽ የሰጣቸው።

ስለ ኢስላም ሼር ሼር

እኔኮ በዕለቱ ከታች ያያዝኩትን ቃሲም ታጁዲን በድንጋጤ የተመታ መስሎ የታየበትን ፎቶ ስመለከት ገርሞኛል¡ ሸይኽ ኢልያስ ሲናገር በመሃል ለማደናቀፍ ሲሞክርና በሰዓት አልቋል ሰበብ ለማስቋረጥ ሲሞክር፤ እድል መስጠቱ ግድ ሆኖበት እንጂ ጭራሽ ባይናገር ደስ የሚለው ይመስላል¡

ያ ሁሉ ለአመታት ሲንከባለል የቆዬ ማምታቻና ብዥታ በ4 ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ አፈር ድሜ ነው የበላው። የእምቧይ ካብ በሉት! እውነት ሲመጣ ሐሰት ይንኮታኮታል የሚባለው እንደዚህ ነው። ጭራሽ ደግሞ የሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ደቂቃ ተጨምሮ፤ በዛው ላይ ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን (ዶ/ር) እና ዶ/ር ጀይላን ራሳቸው ቢጨምሩበት የሚፈጠረውን አስቡት!

ለማንኛውም አሁንም ቢሆን የእውነት ሐቅና ትክክለኛ አንድነት ከተፈለገ፣ ከእልህና የመሸናነፍ መንፈስ ተወጥቶ ለሃሳብ ልዕልናና ለእውነት እጅ መስጠት ከተገኘ፤ ይህ በሰከነ መልኩ ዕውቀት ተኮር ውይይት ቀጣይነት ቢኖረው እመኛለሁ። ከላይ ያሉት ከተስማሙ ከታች ያለውን አንድ ማድረግ ቀላል ነው።

ይህ የአላህም ትዕዛዝ ነው።

(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا)

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡»
[አ-ን'ኒሳእ: 59]

አላህ በትክክለኛወ የቁርኣንና የሐዲሥ መንገድ ላይ አንድ ያድርገን።
اللهم اجمع شملنا وألف بين قلوبنا ووحد صفوفنا.. نسألك يا رب أن تخرج الفتنة من بيننا وتسلم أهل

19/05/2022

Address

Harbu

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dinu man posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share