Sokka Kassa

Sokka Kassa Maganu Jawaho እግዝአብሔር ትልቅ ነው
Su'misino Maganoho ስሙም እግዚአብሔር ነው

''         🔥 የድል ትንቢት፡ 3-1 🔥ሊቨርፑልን በኤምሬትስ ምድር መድረሻ አሳጥተን፣ በሳካና በሀቨርትዝ ጥበብ አንገታቸውን አስደፍተን እንሸኛቸዋለን። የዛሬው ውጤት 3 ለ 1 ሆኖ ሲጠና...
08/01/2026

'' 🔥 የድል ትንቢት፡ 3-1 🔥
ሊቨርፑልን በኤምሬትስ ምድር መድረሻ አሳጥተን፣ በሳካና በሀቨርትዝ ጥበብ አንገታቸውን አስደፍተን እንሸኛቸዋለን። የዛሬው ውጤት 3 ለ 1 ሆኖ ሲጠናቀቅ፣ የተቃቃሚዎቻችን ጩኸትና የፀጉር መንቀል ድምፅ እስከ አንፊልድ ድረስ ይሰማል! 🏟️💨

ለአርሰናል ጠላቶች አንድ መልዕክት አለን፦ "ዛሬ በቲቪ ሳይሆን በፌስታል ታዩታላችሁ!" ምክንያቱም የመድፈኞቹ ጥይት አነጣጥሮ ማረፉ አይቀሬ ነው። እኛ በደስታ ስንጨፍር፣ እናንተ በቁጭት ጥርሳችሁን ስታፋጩ ማየት ለኛ ትልቅ ግብዣችን ነው። 🥂🔴

ያለጥርጥር ... ለንደን ቀይ ናት!
Sokka Kassa Bayu Belguda Belay H Batre Birhanu Mathewos Richa Minase Wako Gudeta Beko Ermias Beki Mostye Ye Tëßfayë Lij Tamirat Daniel Mili Kebede

ፎቶዎቼን በቢሮያችሁ ውስጥ ማየት አልፈልግም። ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ አይደለሁም። እኔ የአገሪቱ አገልጋይ ነኝ።በምትኩ የልጆቻችሁን ፎቶ አንጠልጥላችሁ አንድ ውሳኔ ለማሳለፍ ስትሉ ተመልከቷ...
18/03/2025

ፎቶዎቼን በቢሮያችሁ ውስጥ ማየት አልፈልግም። ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ አይደለሁም። እኔ የአገሪቱ አገልጋይ ነኝ።

በምትኩ የልጆቻችሁን ፎቶ አንጠልጥላችሁ አንድ ውሳኔ ለማሳለፍ ስትሉ ተመልከቷቸው፣ የሌብነት መንፈስ በመጣህ ቁጥር የቤተሰብህን ፎቶ በደንብ ተመልክተህ ሀገር ያጠፋ የሌባ ቤተሰብ መሆን ይገባቸዋል ወይ ብለህ እራስህን ጠይቅ።

የሴኔጋል ፕሬዝዳንት Bassirou Diomaye Faye

ቅዳሜ በታምራት ያሳመርክልን   🙏ከኦሎምፒክ አፍርሰው አሸብርን   ❌   ❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤Sokka Kassa
10/08/2024

ቅዳሜ በታምራት ያሳመርክልን 🙏
ከኦሎምፒክ አፍርሰው አሸብርን ❌
❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤
Sokka Kassa

የአምስት አመቱ እንግሊዛዊ Brecon Vaughan ሲወለድ ጀምሮ ባጋጠመው የአካል ጉዳት ምክንያት እንደ እድሜ እኩዮቹ መጫወት ፡ እንደልጅ መቦረቅ. . መዝለልና መሮጥ የማይችል. . እግሮቹ ...
20/07/2024

የአምስት አመቱ እንግሊዛዊ Brecon Vaughan ሲወለድ ጀምሮ ባጋጠመው የአካል ጉዳት ምክንያት እንደ እድሜ እኩዮቹ መጫወት ፡ እንደልጅ መቦረቅ. . መዝለልና መሮጥ የማይችል. . እግሮቹ የዛሉበት ታዳጊ ነው ።

የታዳጊው Brecon ቤተሰቦች ይህን የልጃቸውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ህክምናዎችን ሞክረው በመጨረሻ ግን አሜሪካን ውስጥ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ልጃቸው ቆሞ እንዲሄድ ማድረግ እንደሚችል አወቁ ።

ለዚህ ህክምና ፡ 60 ሺህ ፓውንድ ያስፈልጋቸዋል ።
እና ታዳጊውን በእግሩ ቆሞ እንዲሄድ ገንዘብ ማሰባሰብ ተጀመረ :: ብዙ ደጋግ ልብ ያላቸው ሰወች ይህንን ዘመቻ ተቀላቅለው የቻሉትን ያህል ገንዘብ አዋጥተው አርባ ሺህ ፓውንድ የሚሆን ተገኘ ። ግን አሁንም የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመሙላት ሀያ ሺህ ፓውንድ ይቀራል ።.....
ይህንን እዚህ ላይ አቁመን ስለዳን ብላክ እናውራ...

ዳን ብላክ ይባላል የ27 አመት ወጣት ነው ። ዳን እስከ 22 አመቱ ድረስ ሙሉ ጤነኛ የነበረ ሰው ነበር ። ሆኖም በአንድ መጥፎ ቀን ብስክሌቱን እየጋለበ በሚሄድበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ አደጋ አጋጠመው ። እግሮቹ ሙሉ ለሙሉ መሄድ አቁመው ዊልቸር መጠቀም ጀመረ ።....
ባልታሰበ አደጋ ዊልቸር ላይ የተቀመጠው ዳን ፡ በህክምና ዳግም ሊራመድ እንደሚችል ስለተነገረው ለዚህ የሚሆን ገንዘብ እያጠራቀመ ነው ። እናም ላለፉት አምስት አመታት ከሚያገኘው እየቆጠበ 22 ሺህ ፓውንድ ደርሶለታል ።.....
እንግዲህ ዳን በዚህ ሁኔታ እያለ ነበር ፡ ስለ አምስት አመቱ ታዳጊ የሰማው ።
ዳን ብላክ በዚህ አደጋ ምክንያት መራመድ አለመቻል ማለት ምን ማለት እንደሆነ አውቋል ።....
እና ይህን እንደሰማ ለራሱ ህክምና ካጠራቀመው ገንዘብ ላይ አንድ ሺህ ፓውንድ አንስቶ ለታዳጊው እንዲሰጡለት ላከ ።

ዳን ብላክ ይህንን ካደረገ በኋላ ግን ህሊናው እረፍት ነሳው ፡ እናም ለዚህ ከተወለደ ጀምሮ በእግሩ መራመድ ለተሳነው ታዳጊ የተሻለ ነገር እንደሚፈልግ ገልጾ የልጁን ወላጆች ካገኘ በኋላ .....
" የብስክሌት አደጋ አጋጥሞኝ ዊልቸር ላይ ከመቀመጤ በፊት በነበሩት 22 አመታት እንደፈለኩ እራመድ ነበር ፡ የህጻንነት ጊዜዬንም ተጫውቼና ቦርቄ ነው ያደኩት ። ሆኖም ይህ ታዳጊ ለሰከንድ እንኳን ተራምዶ አያውቅም ። ስለዚህ እንደገና ቆሜ ለመሄድ ፡ ላለፉት አምስት አመታት ሳጠራቅም የቆየሁትን 20 ሺህ ፓውንድ በሙሉ ለዚህ ታዳጊ መስጠት እፈልጋለሁ " በማለት ተናግሮ ለታዳጊው ቤተሰቦች ለራሱ ያጠራቀመውን ገንዘብ ሰጣቸው ።.......
ባልታሰበ ሁኔታ የጎደላቸውን ገንዘብ በሙሉ ያገኙት የባሮክ ቤተሰቦች ልጃቸውን ይዘው ለህክምና ወደ አሜሪካ ተጓዙ ።
ያ ..እንደሌሎች ልጆች በእግሬ መሄድ የማልችለው ለምንድነው ብሎ እናቱን የሚጠይቀው ታዳጊ በተደጋጋሚ በተደረገለት የቀዶ ጥገና ህክምና መራመድ ቻለ ። ይህ ብቻ አይደለም ፡ በትምህርት ቤቱ በሚደረገው የስፖርት ቀን በሩጫ ተወዳድሮ ማሸነፍ ችሏል ።.....
ይህ ዜና እንደተሰማም ፡ ራሱ ዊልቸር ላይ ተቀምጦ ፡ ከኔ ይልቅ ይህ ታዳጊ በእግሩ መሄድ አለበት የሚል የደግነት ጥግ ያሳየው የዳን ብላክ ነገር የሚዲያዎች ርእስ ሆነ ፨
በብሪታንያ ቀና እና ደጋግ ልብ ላላቸው መልካም ሰወች በየአመቱ በሚሰጠው ሽልማት ተሸለመ ።...
ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ይህ ከራሱ አስበልጦ መልካም ነገር ላደረገው ዳን ብላክ ዳግም ወደጤንነቱ እንዲመለስ ድጋፍ ተደርጎለት እሱም እንደታዳጊው ዳግም መራመድ ችሏል ።

ወዳጆቼ ከዚህ ፁሑፍ ምን ተረዳን? ምን እንማር ? ሀሳባችሁን አጋሩን 🙏🙏❤️

Photo የጉራጌ የልጃገረዶች ቀን  በዚህ ዘመን የምልም አይጠፋም እኮ 🙄🙄 እንግዲህ እርምህን አውጣ ጉራጌ እንዲህ ናቸው ።
28/01/2024

Photo የጉራጌ የልጃገረዶች ቀን

በዚህ ዘመን የምልም አይጠፋም እኮ 🙄🙄 እንግዲህ እርምህን አውጣ ጉራጌ እንዲህ ናቸው ።

 🇪🇹 እንደ ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች:-የተፈጥሮ ሣይንስ ፦➡ እንግሊዝኛ፣ ➡ ሒሳብ፣ ➡ ፊዚክስ፣ ➡ ኬሚስትሪ፣ ➡ ባዮሎጂ...
20/01/2024



🇪🇹 እንደ ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች:-

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ፊዚክስ፣
➡ ኬሚስትሪ፣
➡ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ታሪክ፣
➡ ጂኦግራፊ፣
➡ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

በዚህም #የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ምንጭ ፦

የራስን ማጥፊያ ማሽን ጥቅም ላይ ውሏል አሉን እኮ 🤔😮    (እግዚኦ ማረን)እነሆ የኔዘርላንድ ሳይንቲስቶች ለአለም ህዝብ ጌጥ ብለው ያለ ስቃይ የሚገድል ቴክኖሎጂ አበርክተዋል። በ3D Prin...
13/12/2023

የራስን ማጥፊያ ማሽን ጥቅም ላይ ውሏል አሉን እኮ 🤔😮 (እግዚኦ ማረን)

እነሆ የኔዘርላንድ ሳይንቲስቶች ለአለም ህዝብ ጌጥ ብለው ያለ ስቃይ የሚገድል ቴክኖሎጂ አበርክተዋል።

በ3D Printing እና AI መሳሪያ ሲሆን ይህ መሳሪያ ራሱን ለማጥፋት የሚፈልግ ሰው ያለምንም ስቃይ ከ1 ደቂቃ ባነሰ ሰከንዶች ፀጥ የሚያደርግ መሰሪያ በጣም ምቹና ተመራጭ መሳሪያ እንደሆነ ዩሮኒውስ ዘግቧል ።

ይህ #ሰርኮ የሚል ስያሜ የተሰጠው የራስን መግደያ መሳሪያ በአሁን ሰአት ራስን ማጥፋት በማይከለክሉ ሀገራት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ፣ ባለፈው አንድ አመት በጀርመን ብቻ (ብንሄድ ይሻላል) ብለው ተመዝግበው ከፍለው በዚህ መሳሪያ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ብዛት 1,300 መሆኑን ተጠልጿል።

ከሁሉ በፍት ፈጣሪን ካስቀደምክ ይሁን ካለው ከመሆን አንድስ እንኳ አይቀርም ።   የመሰናከል ብዛት ያጠነክራሀል እንጅ ፈጣር የከፈተልህን በር ልዘጋው እንደማይችል ባለፍንበት መንገድ አይተናል...
05/11/2023

ከሁሉ በፍት ፈጣሪን ካስቀደምክ ይሁን ካለው ከመሆን አንድስ እንኳ አይቀርም ።

የመሰናከል ብዛት ያጠነክራሀል እንጅ ፈጣር የከፈተልህን በር ልዘጋው እንደማይችል ባለፍንበት መንገድ አይተናል።

የዛሬ ሰላማችን ደስታችን የስኬታችን ምንጭ ሁሉ የሆነው
☝️እሱ የነገ መንገዳችን ፣ መከናወናችን ባለቤት ነው።

ያለ እሱ ፍቃድ አንድት የፀጉራችን ዘለላ ከላያችን አትወድቅም ። ብቻ እሱ ከፈቀደ ሸለቆም የመንፈጠሪያችን መነሻ ይሆናል። አሜን አሜን

  🙏
22/10/2023

🙏

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sokka Kassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share