Mebratu

Mebratu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mebratu, Business service, Mekelle.

06/03/2024

የኤርትራ ጦር በሐይል ከያዘው የኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣ፥ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ሀላፊነቱ ሊወጣ ይገባል ሲል የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ጥሪ አቀረበ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ የያዘው የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት እንደሌለ ገልጿል።
በትግራዩ ጦርነት ከፌደራል መንግስት ጋር ተባብረው በትግራይ ሲዋጉ የነበሩ የኤርትራ ሐይሎች፥ ጦርነቱ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከተቋጨ በኋላም ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አለመውጣታቸው በክልሉ አስተዳደር ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ ጨምሮ በተለያዩ አካላት ሲገለፅ ቆይቷል።
በቅርቡ ለዚህ ተደጋጋሚ ክስ ምላሽ የሰጠው በእንግሊዝ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ፥ የኤርትራ ጦር በትግራይ ግዛት ውስጥ እንደሌለ ገልጿል። ባድመን ጨምሮ ሌሎች አሁን ላይ በኤርትራ ጦር የተያዙ አካባቢዎች ህወሓት በሕገወጥ መንገድ ለሁለት አስርት ዓመታት ይዟቸው የቆዩ የኤርትራ ሉአላዊ ግዛቶች ናቸው ሲል ገልጿል።
የኤርትራ ጦር በምስራቅዊ እና ሰሜን ምዕራብ የትግራይ ዞኖች ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች መኖራቸው በተደጋጋሚ የሚገልፀው የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር፥ እነዚህ በኢትዮጵያ ሉኣላዊ ግዛት ያሉ የውጭ ሐይሎች በሐይል ከያዙት ግዛት የማስወጣት እና የተፈናቀሉ ዜጎች የመመለስ ሐላፊነት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሰት ሃላፊነት መሆኑ ይገልፃል። የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም በተለይ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት የኤርትራው ኤምባሲ መግለጫ፥ የኤርትራ ጦር የተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በሐይል ተቆጣጥሮ እንዳለ አመላካች ብለውታል።
የኮምኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ሐላፊው አቶ ረዳኢ ሓለፎም፥ ከአልጀርስ ውል አፈፃፀም ጋር የተያያዘ ጉዳይም፥ በሐይል የተወረረው መሬት ከተመለሰ በኃላ በሕጋዊ እና ዓለምአቀፋዊ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ብለውታል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ረዳኢ በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት "ማለት ያለበት ማለት አለበት። ሐላፊነቱ መወጣት አለበት" ብለዋል።

በትግራይ የኤርትራ ጦር ብቻ ሳይሆን የአማራ ክልል ታጣቂዎች ጭምር መኖራቸው ጨምረው የገለፁት ሐላፊው ይህ የፕሪቶርያው የሰላም ውል የሚፃረረ፣ በትግራይ ያለው አሳሳቢ የተፈናቃዮች ችግር እንዳይፈታ እንቅፋት የሆነ ብለውታል ሲል ሚልዮን ሃይለስላሴ ከመቐለ ዘግቧል።

03/01/2023

Happy New year diaspora tigray

ምህረታቸዉና በረከታቸው  ይስጥልን አሜን
10/11/2019

ምህረታቸዉና በረከታቸው ይስጥልን አሜን

08/11/2019

Address

Mekelle
MEBRENI

Telephone

002519738419

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mebratu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share