TG Love

Call Directions

TG Love How to describre

05/07/2026
26/04/2026

🌀✅ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን ? ✅🌀

🌀ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️🔸️

🌀 ✅ለትዳርህ በቁ ነህን?✅🌀

🌀ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ
ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም
እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።
✅የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት።
✅ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

🌀ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው። ይህን ማስተዋል
ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

✅ወዳጆቼ

እንግዲህ ፈጣሪ የራሳችሁ በሆነ ሰው ባርኮ የስጣችሁ፡፡
በተረፈ ፈጣሪ ላገባነውም ላላገባነውም ማስተዋል ይስጠን እላለሁ

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

✅በትዳር ዓለም ውስጥ ላላችሁም ሆነ ላልሆናችሁ(ወደፊት ትዳር ለምትመሠርቱ) ሁሉ ትዳራችሁ የአምላክ፦ፀጋ፣በረከት ሰላምና ፍቅር የበዛበት ያድርግላችሁ!(አሜን)
ሼርርርር

26/04/2026

🌀✅ በጨጓራ ህመም የምትሰቃዩ እህቶቼ እና ወንድሞቼ ካነበብኩት ምክር ይዤ መጣሁ!!!

✳ መንስኤ!!

1. ባክቴሪያ
2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መውሰድ
3. ለረዥም ጊዜ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች
4. ከልክ ያለፈ መጨናነቅ
5. የመመገቢያ ሠአትን ጠብቆ አለመመገብ

✳ የጨጓራ ህመምን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?

1. ዝንጅብል!
አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡

2. እርጎ!
በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡

3. ድንች!
ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት።

4. ቆስጣ እና ካሮት!
የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት።

5. ውሃ!
በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት።

6. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…

7. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ።

8. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት።

9. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ።

10. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ።

11. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ።

12. ሥጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም።

13. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም።

14. ቡናና ሻይ መቀነስ።

15. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም።

16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ።

17. ቅመማ ቅመም መቀነስ ናቸው።

መልካም ጤንነት!!

ምርጥ መጣጥፎች
#ሼርርርር ያድርጉት

26/04/2026

✅🌀 ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮሀል፡፡
በዛው ልክ በውሀ የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም
ሲንከባለልም በእርጋታ ነው የሰው ልጅም እንደዛ ነው፡፡ ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው #ከመጮህ እና #ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር የለም፡፡

👉 በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ።

👉 በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው፡፡ አንዱ ፌርማታ ላይ #ይወርዳል ከዚያ በኋላ አታገኘውም፡፡ አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል፡፡

👉 ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ባለጌም የመከሩት ዕለት ይብሰዋል"
እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም ፣መልስ ለሁሉም አይመለስም፤ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም፡፡ ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ለይ፡፡ ዕንቁላሎችህንም የምታስታቅፋቸውን ዶሮዎች ምረጥ፡፡

❇✴ የሶቅራጠስ አባባሎች ✴❇

✅ ያልተፈተነ ሕይወት መኖር እርባና ቢስ ነው ።

✅ ልታስፈፅም የማትችለውን ትዕዛዝ አትዘዝ ።

✅ ራሱን በቅድሚያ ማንቀሳቀስ የቻለን ፣ ዓለምን እንዲያንቀሳቅስ ፍቀድለት ።

✅ እውነተኛ ጥበብ አለማወቅን ማወቅ ነው ።

✅ ብቸኛው ጥሩ ነገር ማወቅ ሲሆን ፣ ብቸኛው መጥፎ ነገር ደሞ መሀይምነት ነው ።

✅ ሐሰተኛ ቃላት በራሳቸው ብቻ ኃጢያት ሳይሆኑ ነፍስንም በሀጢያት ይመርዛሉ።

✅ በቅንነት ስህተትህን የሚገልፁልህን እንጂ ቃልህንና ተግባርህን በሙሉ የሚያወድሱት ታማኝ አይምሰሉህ ።

✅ አንዳንዶች ለመኖር ሲበሉ ሌሎች ደሞ ለመብላት የሚኖሩ አሉ ።

✅ አላዋቂ መሆኔን በማወቄ ብልህ ነኝ።

✅ መልካም ሰውን በህይወትህ እያለም ሆነ ከሞተ በኋላ የሚጎዳው ነገር የለም።

✅ ባለው ያልረካ የሚመኘውንም ቢያገኝም አይረካ ።

✅ ለራስህ ማሰብ ስትጀምር ራስህን ታገኘዋለህ።

✅ እውነተኛ ጥበብን የምናገኘው ስለሕይወት ፣ ስለአለምና ስለራሳችን ብዙም እንደማናውቅ ስንገነዘብ ነው።

✅ በዚች ምድር ሁሉም ነገር ያልፋልና ስታገኝም ከልክ በላይ አትፈንጥዝ ፣ ስታጣም አብዝተህ አትከፋ! ።

✅ ወደ ክብር የሚወስደው አቋራጩ መንገድ የምትመኘውን ለመሆን መጣር ነው!።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

26/04/2026

🌀🌀 ስማኝማ❗🌀🌀

🔸️ለፍቅር የቀረብካት ሴት ትውደድህ ትጥላህ ለምን እንደቀረበችህ ግራ
ገብቶሀል ? ይሄን ለማወቅ መከራህን አትይ ! ላንተ ያላትን ስሜት ለማወቅ
አትከታተላት ጎደኞቿንም አትጠይቅ! የፌስ ቡክ አካውንቷንም ለመበርበር
አትድከም እንደዛ ካደረክ ልብህን የሚሰብር ብዙ ነገር ሊያጋጥምህ ይችላል ።
፣
ያንን መቀበል የሚያስችል ሞራል ከሌለህ ደግሞ ልብህ የጥላቻን አረም
ያበቅላል ! ምን በወጣህ ወዳጄ ልብህን በጥላቻ ትመርዛለህ ! ባይሆን
እንዲህ አድርግ ! ሳትሰስት ልብህን ስጣት አፍቅራት አክብራት ሁሌም ቢሆን
በችግሯ ጊዜ ከማንም ቀድመህ አጠገቧ ተገኝ ። ባገኘሀት ቁጥር ለሷ ያለህን
ፍቅር እና አክብሮት ግለጽላት ።
፣
ምን ያህል እንደምታምናት እና የህይወትህ አንድ አካል እንደሆነች በተግባር
አሳያት ። በጭራሽ የት ወጣሽ ? የት ገባሽ ? በማለት ሰላሟን አትንሳት ነጻነት
እንዲሰማት አድርግ ። ወዳጄ ያኔ የምትወድህ ከሆነ ካንተ ሌላ ንጉስ እንደሌለ
አምና በህይወቷ ላይ አንግሳህ ትኖራለች ።
፣
የማትወድህ ከሆነ እና የተጠጋችህ ለሌላ አላማ ከሆነ ግን የሰጠሀትን ፍቅርና
አክብሮት መሸከም የሚችል ጫንቃ ስለማይኖራት ከአጠገብህ ትርቃለች !
ልክ አንተ ንጹህ ሳትሆን ቤተ ክርስቲያን መግባት እንደምትፈራው እሷም ንጹህ
ልብ ሳይኖራት አንተ ፊት የመቆም ድፍረት አይኖራትም ።
፣
ወዳጄ
ነገር_የለም !
ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች

ewnet new ende
25/04/2026

ewnet new ende

ሰበር‼️ ''የቴዲ አፍሮ ምክትል ማኔጀር የሆነችው ማህሌት ሰለሞን መታሰሯ ተሰማ''

በአንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የቅርብ ሰዎች እና የስራ ቡድን ላይ ያነጣጠረው የእስር እርምጃ ይበልጥ አሳሳቢ ወደሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል። የድምጻዊው የቅርብ ወዳጅ የሱፍ ያሲን በፖሊስ መወሰዱን ቀደም ሲል የዘገብን ሲሆን፣ አሁን የቴዲ አፍሮ ምክትል ማኔጀር እና ይፋዊ ቃል አቀባይ የሆነችው ማህሌት ሰለሞን በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሏ በቤተሰብ ምንጮች ተረጋግጧል።

ማህሌት ሰለሞን አረፈችበት አትላስ አካባቢ ከሚገኝ ሆቴል ውስጥ፣ ስድስት በሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት መወሰዷን የዓይን እማኞች እና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት ደግሞ ኦስትሪያዊት የሆነችው ማህሌት፣ በአርቲስቱ የስራ ማኔጅመንት ውስጥ ትልቅ ሚና ያላት ቁልፍ የቡድኑ አባል ነች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም የቴዲ አፍሮን አዲስ እና ሲጠበቅ የነበረው የሙዚቃ አልበም መውጣትን ተከትሎ፣ ድምጻዊውን በመወከል የተለያዩ ይፋዊ መግለጫዎችን እና የስራ እንቅስቃሴዎችን ስታስተባብር ቆይታለች።

ምንም እንኳን የፌዴራል ፖሊስ በእስሮቹ ዙሪያ ይህ ዜና እስከተሰራጨበት ጊዜ ድረስ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ ባይኖርም ይህ ተከታታይነት ያለው የእስር እርምጃ፣ ተራ የህግ ማስከበር ሂደት ሳይሆን በድምጻዊው ዙሪያ ያሉትን የቅርብ ሰዎች፣ ስራ አስኪያጆች እና ወዳጆች ነጥሎ በማጥቃት በቴዲ አፍሮ ላይ ከባድ የስነ-ልቦና ጫና እና የስራ መስተጓጎል ለመፍጠር የታለመ የተቀናጀ ኦፕሬሽን መሆኑን የፖለቲካ እና የደህንነት ተንታኞች ይገልጻሉ። በተለይም አርቲስቱ አዲስ አልበም ይዞ ወደ ህዝብ ለመውጣት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወሳኝ ወቅት ላይ፣ ቃል አቀባዩን እና ማናጀሩን ማሰር ሆን ተብሎ የጥበብ ስራውን ለማክሸፍ የተደረገ እንቅስቃሴ ተደርጎ ይወሰዳል።

ከዚህም ባሻገር የውጭ ሀገር (የኦስትሪያ) ፓስፖርት ያላትን ግለሰብ በዚህ መልክ በኃይል መውሰድ የዲፕሎማሲያዊ ህጎችን የሚጻረር እና ጉዳዩን ከሀገር ውስጥ የጥበብ ማፈን አልፎ ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ገጽታ ሊሰጠው የሚችል አደገኛ እርምጃ ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

አንድ ስማቸው እንዲጠቅስ ያልፈለጉ የቤተሰብ ምንጭ ለበሰጡት አስተያየት "ፌደራል ፖሊስ የማህሌት ሰለሞንን የት መገኘትም ሆነ የታሰረችበትን ምክንያት እስካሁን በይፋ የገለጸው ነገር የለም። አንድን አርቲስት በቀጥታ ከመንካት ይልቅ በዙሪያው ያሉትን የስራ አጋሮች በማሰር እና በማስፈራራት ለማዳከም የሚደረገው ይህ አይነት እንቅስቃሴ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እና የህግ የበላይነት ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ክስተት ሆኗል" ብለዋል።

Via:- ዘ-ሐበሻ

ትችላለህ kalu putik
25/04/2026

ትችላለህ kalu putik

Address

Mekelle

Telephone

+251938796311

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TG Love posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share