Asnake Mesfin

Asnake Mesfin Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Asnake Mesfin, Business service, metahara, Metahara.

11/12/2024
የቡሄ (የደብረ ታቦር) ችቦ የሚበራው  መቼ ነው??መጽሐፈ ታሪክ ወግሥ ገጽ 307 (አዘጋጅ፦ መምህር አፈወርቅ ተክሌ  የቅኔና ሰባኪ ወንጌል 1997 ዓ.ም አዲስ አበባ)
18/08/2024

የቡሄ (የደብረ ታቦር) ችቦ የሚበራው መቼ ነው??

መጽሐፈ ታሪክ ወግሥ ገጽ 307 (አዘጋጅ፦ መምህር አፈወርቅ ተክሌ የቅኔና ሰባኪ ወንጌል 1997 ዓ.ም አዲስ አበባ)

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ
01/05/2024

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ

Watch, follow, and discover more trending content.

ከመምህር ይላቅ
01/04/2024

ከመምህር ይላቅ

 # # #ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል # # #       (   ሉቃስ 15 ፥2 )ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።  ፈሪሳውያንና ጻፎችም፡—...
23/03/2024

# # #ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል # # #
( ሉቃስ 15 ፥2 )

ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ፈሪሳውያንና ጻፎችም፡— ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል፡ ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ። ይህ ማለታቸው ንፅህናውን ለመግለጥ አይደለም ይልቁን አላዋቂ ቢሆነው ለማለት መሞከራቸው እንጂ

ማቴዎስ 9 ፥12-13 ኢየሱስም ሰምቶ፡— ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ብሎ መለሰላቸው ይገርማል እኛ ዛሬም ይሄኑኑ የጻፎችና የፈሪሳውያን መንገድ ይዘን ወንድሞቻንን መንክሳችን በእህቶቻችን መጠቋቆማችን እኛ ከእነሱ አንሻል ብዙ እንላለን ንፁሀ ባህሪ ክርስቶስ ግን እንዲ ነው ያለው

ማቴዎስ 9 ፥ 13 ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና እናንተ ጨካኞች ስትሆነ ልጆቻቹ ትራራላቹ ብሎም ለእንስሶቻቹ ሉቃስ 15 ፥4-7 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፡— የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ፡ ይላቸዋል።

እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። ይህስ ኃጢያተኞችን ይቀበላል እውነት ነው ኃጢያቶኞች የተባልን እኛን ቀረበን የእኛንም ስጋ ነሳ ተዋህደ ከእነርሱም ጋር ይበላል እዳሉ በላ ጠጣ ይማለት ስጋን መልበሱን ለማጠይቅ ነው እንጂማ በመለኮት መራብና መጠማት የለበት

ከኃጢያት ሞት ያዳነን ክርስቶስ ስሙ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ይመስገን

ወስብአት ለእግዚአብሔር

ገብረ ክርስቶስ(Asnake Mesfin)

ሼር ሼር ሼር

> > > ልብሳችሁን አጥባችሁ ንጹሕ አድርጉ < < <(ተአምረ ኢየሱስ 69 ተአምር)ተአምረ ኢየሱስ ከቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍት አንዱነው  በ69ነኛው ተዘጋጅቶ ስለ መቀመጥ በሚያስተምር አንቀ...
23/03/2024

> > > ልብሳችሁን አጥባችሁ ንጹሕ አድርጉ < < <

(ተአምረ ኢየሱስ 69 ተአምር)

ተአምረ ኢየሱስ ከቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍት አንዱነው በ69ነኛው ተዘጋጅቶ ስለ መቀመጥ በሚያስተምር አንቀጽ ላይ ርዕሳችንን እናገኛለን

``ዕወቁ ተጠንቀቁ የዚህ ዓለም ዘመኑ እንደሕልም ወይም እንደጥላ ያልፋልና። እኔ ወደሠርግ ቤት ከመምጣቴ በፊት ልብሳችሁን አጥባችሁ ንጹሕ አድርጉ ሙሽራው ከመድረሱ በፊት ነቅታችሁ ጠብቁ ድንገት በሌሊት ይመጣልና`` ይላል ወንጌልም እንዲ ይደግፈዋል ማቴዎስ 24 ፥42 ``ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።``ማቴዎስ 25 ፥1-13``ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ``

ልብሳችሁን አጥባችሁ ንጹሕ አድርጉ፦ ምን ማለት ነው ልብስ ገላን መሸፈኛ(አፍረተ ስጋን ይሸፍናል)፣ አንድም ክብር ነው ይሄን ካልን ታድያ ሰው በክብር ሲጠራ ወደ ተጠራበት ሲሄድ አዲስ ልብስ ወይም ያለውን አጥቦ ይለብሳል በዚህም የጠራውን ሰው ያከብራል ከዛም ባሻገር በጠሪው ፊት ክብርን ያገኛል።

እግዚአብሔር እስራኤል ከግብፅ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በተራራው በክብር ሊገለጥ ሙሴን ህዝቡ እንዲዘጋጁ ንገራቸው ብሎታል ዘጸአት 19 ፥10 ``እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፡— ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገም ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ይዘጋጁ።``

ይህ ማለቱ ለምድነው ቢሉ በቆሻሻ ያደፈውን ልብስ እንዳለብሱ በንጹሕ ልብስ እንዲገኙ ነው ምስጢሩ እድፍ በተባለች በኃጢያት የቆሸሽ እራሱን ያንጻ ስለ በደሉ ይጸጸት ማለት ነው ምክንያቱም ያለ ንስሀ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አይቻልምና መንግስተ ሰማያትን ለማግኘት በንስሀ መታጠብ ተገቢ ነውና

ራእይ 22፥14``ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።``ራእይ 7፥13-14``ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ፡— እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስመጡ?አለኝ። እኔም፡— ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ፡ አልሁት። አለኝም፡— እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።``

ልብሳችሁን አጥባችሁ ንጹሕ አድርጉ አለ በንስሀ ታጠቡ ንጽሀን ሁኑ ስለኃጥያያታቹ ተናዘዙ ትነጻላቹ ንጹሕ ትሆናላቹ ኢሳይያስ 46፥8 ``ይህን አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፥ ንስሐ ግቡ፥ ልባችሁንም መልሱ። `` በንስሀ ኃጥያታችን ይደመሰስልናል

ሐዋ 2 ፥38``ጴጥሮስም፡— ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።``

ሐዋ3 ፥19-20``እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።``

በንስሀ ታጥበን በንጹሕና የመንግስተ ሰማያት ዜጎች ያድርገን

ወስብአት ለእግዚአብሔር

✍️️ገብረ ክርስቶስ (Asnake Mesfin)✍️

ሼር ሼር ሼር

አለም አንተን ሳትንቅህ አንተ አስቀድመህ ናቃት(ቅዱስ አትናቴዎስ)  https://t.me/Asnakemesfin ሼር አትናቴዎስ በእስክንድርያ በ298 ዓ/ም ተወልዶ ወላጆቹ አረማውያን ስለነበሩ ...
23/03/2024

አለም አንተን ሳትንቅህ አንተ አስቀድመህ ናቃት
(ቅዱስ አትናቴዎስ)
https://t.me/Asnakemesfin ሼር

አትናቴዎስ በእስክንድርያ በ298 ዓ/ም ተወልዶ ወላጆቹ አረማውያን ስለነበሩ ክርስትና አልተነሳም ነበረ ሕፃን እያለ ለጫወታ ከቤት ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጫወታ ሲጫወቱ ተመለከተ።

ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት። አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ አለቸው እነሱም እሺ ብለውት ሕፃናቱ እጣ ሲጣጣሉ ለአንዱ ቄስ ለአንዱ ዲያቆን ሲደርስቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለደረሰው ሌሎቹ ሕፃናት ለእርሱ ይሰግዱለት ጀመር።

በአጋጣሚ ሕፃናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕፃኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት ከዚያም የአትናቴዎስ አባት ሲያርፍ ሊቀ ጳጳሱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ ሃይማኖትን አስተምሮት ከዚህ በኃላ ከዲቁና እስከ ሊቀ ጳጳስና የደረሰ ለክብር የበቃ አባት ነው።

የማይረሳውና የማይዘነጋው በኒቃያ ጉባኤ ላይ መናፍቁን አርዮስን ድል የነሳበት መልስ ያሳጣበት የጀብድ ስራው ሳናነሳው የምናልፈው አይደለም ይሄም ብቻ አይደለም በፓትርያርክነት በተሾመበት በዛው በግብፅ(በእስክንድርያ) ብዙ መከራ ተቀብሏል ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምንጠቀሰውን መልእክትና ትምህርት ከኒቃያ ጉባኤ ጀመሮ የጻፈው ነው

ከላይ በርዕሳችን የጠቀስነው ዐይለ ቃለ የተናገረው እርሱ ነው 1 ዮሐንስ 2፥15-16 '''ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ''' የሚለውን ቅዱስ ወንጌልን መሰረት አድርጎ አለምን የናቀ ሌሎችንም ያስተማረ ድንቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ዛሬም ድረስ ቤተክርስቲያን ትምህረቱንና ህይወቱን እያነሳች የምታስተምርበት የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ አትናቴዎስ ነው

በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።

አለም አንተን ሳትንቅ አንተ ናቃት ማለት ፦ አለም ጀርባዋን ሳሰጠ ትምህርትና የትዳር ህይወት ሳያሰለችህክ በፊት
አለም ማር እያላሰችህ ክብር በምትለው ነገር ሁሉ ባከበረችህ ጊዜ ሁሉም በተገዙል ጊዜ በአለም ፀሐይ የማይጠልቅባትና የማይጨልምባት በሚመስልበት ጊዜ አለም ልሹምህ ልሸልም ባለች ጊዜ አንተ ናቃት

አለም ሳትንቀን እኛ አስቀድመን እንናቃት እንደ ቅዱሳኑ ዕብራውያን 11፥38-40 '''ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።'''

1 ዮሐንስ 5 ፥4-5 ''' ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?'''

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ገብረ ክርስቶስ(አስናቀ መስፍን)

 # # #ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት # # #(ዮሐ8፥7)    ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴትን ወደ ጌታችን አምጥተዋት ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።...
23/03/2024

# # #ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት # # #
(ዮሐ8፥7)

ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴትን ወደ ጌታችን አምጥተዋት ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፡— ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት፡ አላቸው።
ዛሬም ልክ እንደ ጻፍትና ፈሪሳውያን ከሳሽ ሆነን ብዙዎችን እንወነጅላለን እንከሳለን ብሎም እንፈርዳለን

'''ማቴ 7፥3 በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፡— ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ፡ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።'''

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ጣሪያ ግድግዳ ይሰውረዋል ሰው አያየውም አይሰማውም ብለን የሰራነው ኃጢያት በእርሱ ዘንድ ግልፅ ነው በሕሊናችንም ይወቅሰናል
አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፡— ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች።

'''ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።''' መዝ13(14)፥3

ገመናችንን ሸፍኖልን እንጂ መቼ ከሰው ፊት ከአውደ ምህረቱ እንቆም ነበረ በቸርነቱ ነውራችንን ሰውሮልን ባይሆን ኖሮ

አሁን ግን እንዲህ ይለናል፦ እኔ አልፈርድብህም፤ሂድ ከአሁንም ጀምሮ ደግመህ ኃጢአት አትስራ
እኔ አልፈርድብሽም ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ገብረ ክርስቶስ(አስናቀ መስፍን)
ሼር ሼር ሼር

👉📖ያየውትን እዩ የሰማውትንም ስሙ📖 ይሄ ልባዊ ጥሪ ነው ይሄን ቻናል የከፈትኩት በዚህ ቅን ሐሳብ ነው። ⛪️የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በማኀበራዊ ገጽ ለምዕመናን ለማድረስ ነው። ማ.....

Address

Metahara
Metahara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asnake Mesfin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share