Bahire Giorgis Technical Training Services

Bahire Giorgis Technical Training Services Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bahire Giorgis Technical Training Services, Business service, Motta.

Bahire Giorgis Short Term Technical Education and Training Service/ ባሕረ ጊዮርጊስ የአጫጭር ጊዜ የቴክኒክ ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት Email:...
13/05/2023

Bahire Giorgis Short Term Technical Education and Training Service/ ባሕረ ጊዮርጊስ የአጫጭር ጊዜ የቴክኒክ ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት

Email: [email protected]
Phone: 0934659160/0905516864

14/04/2023

Bahire Giorgis Short Term Technical Training Service/ባሕረ ጊዮርጊስ የአጫጭር ጊዜ የቴክኒክ ትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት

ከእኛ ዘንድ ሲመጡ መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና አገልግሎት፣ የሲኦሲ ልምምድ፣ ማንኛውንም የጽሑፍ ስራ አገልገሎት፣ የሪሰርች፣ የቢዝነስ ፕላን፣ የፕሮጀክት እና የመሳሰሉ ተዛማጅ ስራዎች ስራና ስልጠና፣ የፕሮግራሚንግ ስልጠና፣ የጥገና ስልጠና አገልግሎት፣ የኔትወርክ ዝርጋታ፣ የመብራት ዝርጋታ፣ የድህረ ገጽ ልማት ስልጠና፣ የአፕሊኬሽ ልማት ስልጠና፣ የኢንተለጀንት ሲስተም ስልጠና አገልግሎት እና ሌሎችንም የስልጠና አገልግሎት ያገኛሉ።

አድራሻ፦ ጉንደ ወይን
ኢሜል፦ tanatec017gmail.com
ስልክ፦ 0934659160

13/04/2023

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ በሳር ቀለም ጉዳይ ክርክር ውስጥ ገቡ።

አህያ ፡- «የሳር ቀለም ቢጫ ነው» አለ።
ተኩላ ፡- «በፍፁም ! አረንጓዴ ነው» አለ።

ክርክራቸው እየጦፈ መጣ። የሚያስማማ የጋራ ነጥብ ላይ መድረስ ባለመቻላቸው የጫካ ንጉስ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው ጉዳያቸው በሽምግልና መፈታት እንዳለበት ወሰኑ። ሁለቱም የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም ግራ ቀኙን በጥሞና ካዳመጠ በኋላ የፍርድ ውሳኔውን ለመስጠት ተደላደለ። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን አሾሉ። አንበሳው ታዳሚውን እና ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ። ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ እና አህያው ደግሞ በነፃ እንዲሰናበት ወሰነ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በማለት ስሞታ አቀረበ ፡-

«ክቡር አንበሳ ሆይ ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን ? »

አንበሳም «በርግጥ አረንጓዴ ነው» ብሎ መለሰ።

ተኩላውም «ታዲያ በምን ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል ዘብጥያ እንድወርድ የተወሰነው» በማለት ጠየቀ።

አንበሳውም «ትክክል ነህ ፤ በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም። ትልቁ ጥፋትህ በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳትና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል ትምህርት እንድትቀስም ብየ ነው የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ» በማለት ምላሽ ሰጠው።

መልካም ቀን

13/04/2023

የአሸናፊዎች እና የሰነፎች ልዩነት

👉 ሰነፎች ሁሌም ነገሮችን ለመለወጥ የሆነ ነገር መደረግ አለበት ይላሉ፤ አሸናፊ አይምሮ ያላቸው ደግሞ እኔ ይሄን ማድረግ አለብኝ ይላሉ።

👉 ሰነፎች ሁሌም አስተያየት ሰጪዎች ናቸው ተግባር ላይ የሉበትም፤ አሸናፊዎች ግን የሚያውቁትንና የሚያምኑበትን ተግባራዊ ሳያደርጉ አያርፉም።

👉 ሰነፎች የምክንያትና የሰበብ ሀብታሞች ናቸው፤ አሸናፊዎች ግን የመፍትሄና የለውጥ ባለፀጋ ናቸው።

👉 ሰነፎች ብዙ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ስለ ትናንት እና ስላለፈ ነገር አብዝቶ በማሰብ ነው፤ አሸናፊዎች ግን ከትናንት ተምረው ዛሬን ያጣጥማሉ ነገን አስቀድመው ያቅዳሉ።

እነዚህ ፀባዮች በተፈጥሮ የተሰጡን አይደሉም፤ በጊዜ ሂደት እያዳበርን የመጣናቸው ናቸው። ስለዚህ ምርጫችን አሸናፊ መሆን ከሆነ ከላይ ያሉትን አመለካከቶች ፀባያችን እንዲሆኑ ዋጋ መክፈል አለብን።

💚💛❤️

ተለግራም ቻነል ይቀላቀሉ👇👇👇

https://t.me/+UzjOmX4DzaBxsuG-

Adey - አደይ

#አደይ

10/04/2023

Bahire Giorgis Short Term Technical Education and Training Service Our Training Services
💻 Basic Computer Training
💻 Hardware Engineering
💻Software Engineering
💻 Website Development
💻Application Development
💻Software Development
💻Teaching Methodology
💻Research Methodology
💻Project Methodology
💻 AUTOCAD
💻WATER CAD
💻 CIVIL 3D
💻 GIS Software and Remote Sensing
💻 Accounting Software
💻 Statistical Analysis Software
💻 Entrepreneurship and Business Plan
💻COC Training

08/04/2023

👉አምስቱ የመልካም ዛፍ ፍሬዎች

የሰው ልጅ ትውልድን ሊለውጥ እና ሊቀይር የሚችለውን የእውቀቱን ብርሃን በአንድ አንድ አልባሌ ነገሮች ውስጥ ደብቆ እና ሸሽጎ ማስቀመጥ ነውር እና በመጽሐፍም የተከለከለ በመሆኑ እንዲሁም መድኃኒታችን በተራራ ላይ የተሠራ ቤት መሰወር አይቻለውም እንዳለ ከፍ ዝቅ፤ ደፋ ቀና፤ ወጣ ወረድ፤ መለስ ቀለስ፤ ደረስ መለስ፤ ሄድ መጣ፤ ብሎ ያገኘውን የእውቀት ጮራ ፈንጥቆ ለትውልድ ማብራት ተገቢ ነው።
በመሆኑም የመንፈሳዊና የሳይንሳዊ አስተምህሮ ምሁራን ባህልን፣ እውቀትን፣ ጥበብን.......ወዘተ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍና ተተኪ ትውልድ ለመፍጠር በየሙያ መስካቸው ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላሉ።
እኔም በበኩሌ ያለኝን ትንሽ የቴክኖሎጂ እውቀት ለትውልድ የማካፍልበት አንድ ትልቅ የሙያ ማሰልጠኛ ድርጅት መክፈት ህልሜ ስለነበር ባሕረ ጊዮርጊስ የአጫጭር ጊዜ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና አገልግሎት የሚል ድርጅት መስርቼ በድርጅቴ ውስጥ በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በ01 ቀበሌ ከ19/01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ
1. Basic Computer Training
2. Programming Language(C++, Java, Python)
3. Software/Application Development
4. Website Development
5. Teaching Methodology
6. Research Methodology እና የመሳሰሉ ተዛማጅ ስልጠናዎችን ስሰጥ ቆይቼ በአንዳንድ ችግር ምክንያት አቋርጬ የቆየሁ ቢሆንም ለችግሮች መፍትሔ በማበጀት አሁንም እንደገና ህልሜን ለማሳካት ተስፋ ባለመቁረጥ በውስጣቸው ሰፋ ያለ ሀሳቦችን የያዙ ከታች ከ1-5 የተዘረዘሩትን የስልጠና አገልግሎት ለመስጠት ደፋ ቀና እያልኩ እገኛለሁ።
እነርሱም፦
1. Hardware Engineering & Software Engineering
2. Intelligent System
3. Website Development
4. Software/Application Development
5. Short Term Technical and Nontechnical Education and Training Service ናቸው።
አምስቱ የመልካም ዛፍ ፍሬዎች ከላይ ከ1-5 የተዘረዘሩት ሲሆኑ እኒህን የስልጠና አገልግሎቶች መሰልጠን የምትፈልጉ በሙሉ በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በጉንደ ወይን ከተማ ከቢያድ ማድያ ፊትለፊት የምንገኝ ሲሆን በአካል መጥታችሁ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ስንል
በታላቅ አክብሮትና ትህትና እናሳስባለን።

Address

Motta

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahire Giorgis Technical Training Services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share