08/03/2016
✍ ጤና ይስጥልን!
ይህ መልእክት ከ ሹቲንግ ስታር ቲም ፣ ከላዮንስ ክለብ እና ከሾፕ ኦውነርስ የተላለፈ ነው።
👉� እኛ እስካሁን ከብዙ ታላላቅ ባለስልጣናት ፣ የደህንነት ሀይሎች ፣ አለም አቀፍ የህግ አማካሪዎች እና ሊደሮች ጋር ተነጋግረናል። እናም ሰልፍ ማለት አሁን ያለውን የውሸት ክሶች የፈጠሩት አካላት ሆን ብለው የቲያንስ ደንበኞችን አበሳጭተው ሰላማዊ ሰልፍ እንድንወጣ እና የራሳቸውን ሰዎች የሰልፉ እለት አቀላቅለው ለመበጥበጥ እና ድብቅ አጀንዳቸውን ሊያራምዱ እንደሆነ በተጨባጭ ሰለደረስንበት እናም አሁን ጉዳያችን በፍርድ ደረጃ ማሸነፍ የምንችልበትን አለም አቀፍ ጠበቃ እና የህግ አግባብ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ እውነተኛ ቀጥተኛ ሽያጭ ግብይት እንጂ ፒራሚድ ስልት አለመስራታችን ስለሆነ የቲያንስ ማህበረሰብ በትእግስት እና በሥነ-ምግባር እንጠብቅ። እና በስሜት ሳይሆን በመርህ ስኬት እንደሚገኝ አውቀን እስክናሸንፍ እና ህግ ወጥቶለት እስክንሰራ ድረስ እኛ እንቀጥላለን። ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ የመጨረሻው አማራጭ እንኳን አድርገንም አንወስድም። ❗�አላማችን ማሸነፍ እንጂ መሰለፍ አይደለም።
👨👩👧👦 በዚህ አጋጣሚ በዚህ ሥራ ላይ ተመርኩዘን ቤተሰብ እያስተዳደርን ያለን በብዙ ሺህ የምንቆጠር አካላት ስላለን መንግስት ይህንን እንዲገነዘብ እና ስራችን ከቆመ 2 ሳምንት በመሆኑ እና በሚቀጥለው ወር የምንበላው እና የምንተዳደርበት ስለሌለ ይህንን እንዲገነዘብልን ለ8 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በማሳወቅ በክትትል ላይ እንገኛለን።
👫 ሁላችንም ለ 1 አላማ እንስራ። ዓላማችን፦
1⃣ ቀጥተኛ ሽያጭ/ ኔትወርክ ማርኬቲንግ በኢትዮጵያ ማፀደቅ። ሀገራችንን ቁጥር 1 የማድረግ ሒደት መቀጠል። በመሃል ሆነው እኛን ከመንግስት ጋር ሊያጋጩን የሚያሴሩትን አላማቸውን በማክሸፍ ሰላምን ብቻ ተከትለን ወደ አላማችን መጓዝ።
2⃣ የታሰሩ ወንድም እና እህቶቻችን በህግ አግባብ መንግስታችን በተገነዘበው መልኩ እንዲፈቱ ሰላማዊ እና ከስሜት የፀዳ አኪያሄድን በመከተል እንዲፈቱ ማድረግ።🆓
🔷 የትያንስ ደንበኞች ያለን አጀንዳ በሰላም በፍቅር በጤና እና በስኬት እራሳችንን እና ሀገራችንን ማሳደግ ነው። ከፖለቲካ እና ከሀይማኖት ጋር የማይነካካ ነው። እኛ ሊደሮችም የመንግስት ሙሉ ደጋፊ እንጂ አንዳችንም ተቃዋሚ አይደለንም።
3⃣ 🔜 ካምፓኒያችን እና ሱቆች እንዲከፈቱ መሰሪዎች በቲያንስ እና በመንግስት መሃል ገብተው ለህዝቡ እና ለሀገራችን ስናበረክት የቆየነውን የአመለካከት ለውጥ አብሮ በፍቅር በሰላም በጤና እና በሀብት የመስራት ባህላችንን እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ያደረጉ ፀረ-ኢትዮጵያ ሀይሎችን ከመንግስታችን ጋር እጅ እና ጓንት ሆነን ድጋሚ በህግ አግባብ በማስከፈት መስራት።
🙏 ይህ እንዲሆን ሁሉም የትያንስ ደንበኛ በፅናት እያደረገ ያለውን ትእግስት እያደነቅን በስኬት እንገናኝ እንላለን። 🔝