Debremarkos University Civil Assocation

Debremarkos University Civil Assocation Work in your part time

visit our official telegram channel
https://t.me/engineer03

 #የደብረማርቆስ  #ዩኒቨርሲቲ  #መሃንዲስ  #በትግል  #ላይ!   Yonas Limenh
19/10/2025

#የደብረማርቆስ #ዩኒቨርሲቲ #መሃንዲስ #በትግል #ላይ!
Yonas Limenh

 #ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?*********ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የ...
13/06/2025

#ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?
*********
ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-
>አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡
>ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡
> ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡

የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ ተግባራዊ መሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች

*******
✍️በአገር ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋለውን የተወሳሰበ ችግር ይህ የአሰራር ስርአት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት እንደሚፈታ ይታመናል፤
✍️በዘርፉ የግብይት ስርአቱን ቀላል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባሻገር በአገር ኢኮኖሚ እድገቱ ላይ የራሱን አውንታዊ ሚና መጫወት ይችላል፤
✍️በዘርፉ በመረጃ አያያዝ ጉድለት የነበረውን ችግር ተጠቅመው ጥቂቶች አላግባብ የሚበለፅጉበትንና ህጋዊ ባለይዞታዎችን ለተለያዩ ጉዳቶች ይዳርግ የነበረውን የአሰራር ችግር ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታመናል፣
✍️ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ በዘመናዊ መንገድ የሚደራጀው የከተማ መሬት ይዞታ መረጃ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ አሰራሮችንና ህጎችን ለማመንጨት የተሻለ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፤
✍️ የከተማ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩትን መሬት ቆጥረው እንዲያውቁ፣ የትኛውን መሬት ለየትኛው አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸው አቅደው እንዲሰሩና በተገቢው መንገድ እንዲያስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርግላቸዋል፤
✍️ከተሞች ከመሬት ሃብታቸው መሰብሰብ የሚገባቸውን ግብር እና ኪራይ በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ ለለከተማው የመሰረተ-ልማት ግንባታ በማዋል ከተሞች በስርአቱ ያድጋሉ፣ የከተማው ነዋሪም የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል፤
✍️የካዳስተር ስርአቱ በሚፈጥረው የመረጃ ምልዑነት በከተማ መሬት ይዞታ የሚስተዋለውን በዜጎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር ይቀንሳል፣ በዚህ ምክንያት የሚያጠፋውን ገንዝብ፣ ጊዜ እና የፍትህ መጓደል ይቀንሳል፤
✍️ማንኛውም ዜጋ በከተማ መሬት ይዞታ ዘርፍ ማግኘት የሚፈልገውን መረጃ ብዙ ውጣውረድ ሳይገጥመው በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፤
✍️በከተሞች ህጋዊ ካዳስተርን መገንባት ከተቻለ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እምነት ስለሚያሳድሩ ሃብታቸውን ልማት ላይ ያውላሉ በዚህም ነዋሪው ተጠቃሚ ይሆናል፣ ከተሞች ያድጋሉ፣ ሳቢም ይሆናሉ፤
✍️በዘርፉ ሙያ ለተሰማራው አመራርም ሆነ ባለሙያ የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር ያደርጋል፣ አቅምም ይገነባል፣ በዚህም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
=====//=========

✅ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።https://t.me/engineer03
20/04/2025

✅ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።

https://t.me/engineer03

👉አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ :: ሚያዚያ 2017. ዓ.ም.full pdf on our telegram ➾➾➾➾https://t.me/engineer03
19/04/2025

👉አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ :: ሚያዚያ 2017. ዓ.ም.
full pdf on our telegram ➾➾➾➾
https://t.me/engineer03

22/12/2024
የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።  የአባ...
11/10/2024

የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።

የአባይ ሸለቆ መስራት አለብን!!!

#በነገራችን ላይ በ2008 ተመራቂ ተማሪዎች በነ ኢንጅነር ዋሲሁን እና ያረጋል ፕሮጀክት ተሰርቶበት ነበር

https://t.me/engineer03

💥የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/ ⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታልኬት/Eleva...
27/02/2024

💥የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/
⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/ Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።
➡ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/

➡ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።

➡ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

https://t.me/engineer03

✍️ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው  ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ:-🚧አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነ...
04/02/2024

✍️ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ:-

🚧አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው።

✍️The reasons a building collapses can be due to
✔️poor structural design,
✔️poor compliance with specifications
✔️poor quality control
✔️faulty construction methodology foundation failure
✔️extraordinary loads and corruption. Natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

✍️በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
☑️ poor structural design
☑️faulty construction
☑️poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

👉አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

#⃣ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1,በ Fatigue ና
2, Creep ነው

1,Fatigue
✔️ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
✔️አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

 #ማስታወቂያ   ➡️ከድርጅታችን ከኢትኬር ጋር እንዴት እንደሚሰሩ ያውቃሉ?👉 https://t.me/etcare_Ethiopian_Companyበየቀኑ ከፍ ያለ ብር  ይከፈልዎታል!!የ2ና የ3 ወር ...
21/09/2023

#ማስታወቂያ

➡️ከድርጅታችን ከኢትኬር ጋር እንዴት እንደሚሰሩ ያውቃሉ?
👉 https://t.me/etcare_Ethiopian_Company

በየቀኑ ከፍ ያለ ብር ይከፈልዎታል!!

የ2ና የ3 ወር ደሞዝዎትን እኛ ጋር አብረው ሲሰሩ የአንድ ቀን ገቢዎት እንደሆነ ያውቃሉ!

ይምጡ! ይደውሉ! በአሉበት ቦታ ሁነው ይስሩ!!

#የጊዜና የገንዘብ ነፃነት ሁሌም ያገኛሉ!!

Etcare |
I care! | You care! | We care!



☎️+251935785595

መልክት ለመላክ 👇

send your message through telegram:-



Join us on telegram :-
https://t.me/etcare_Ethiopian_Company


https://www.youtube.com/

🙏ሼር ይደረግ🙏

Dirección

Mexico City
00000

Notificaciones

Sé el primero en enterarse y déjanos enviarle un correo electrónico cuando Debremarkos University Civil Assocation publique noticias y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin, y puede darse de baja en cualquier momento.

Contacto La Empresa

Enviar un mensaje a Debremarkos University Civil Assocation:

Compartir