Jemal Hassen Ousman

Jemal Hassen Ousman all connect

03/06/2023
02/12/2020

ጀግኒት ታሪክ ሰራች!
ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች ።

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም ።

የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።

ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።

በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።

ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ፣ ወደ ኤርትራ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።

በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።

ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችው እንዲህ ታጫውተናለች ።

"... ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደ መፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ከሃዲው አዛዥ ተብዬ ፣ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድዬ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል..."

"... በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ ።"

ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።

ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !

ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄም ጀግና ማፍራት የማትሰለቸው ሃገራችን ከሰጠችን እንቁ ኢትዮጵያውያን አንዷ ናት፥ እንዳንች አይነት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌም በኢትዮጵያዊ ክብር ደምቆ ይኖራል ።

የከሃዲዎች መጨረሻ ሃገርን ለማዋረድ ባሴሩት ህልም ውስጥ ተጠልፎ መውደቅ ነው ።

አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ ብርሃኑ ወርቁ
#ከኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት

02/12/2020

👉 ይህ የኔም ጥያቄ ነው⁉️
አሁንም በጥርጣሬ እንድመለከታቸው ከአደረጉኝ 2 ነጥቦች ‼

1. የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻን አላመሰገኑም ???
2. ምክርቤቱ ትህነግ እና ኦነግ ሸኔን በሽብር እንዲፈረጅ የጠየቁትን ጥያቄ አልፈውታል ..ለምን ???

....ሌላውን በሂደት እናያለን‼️

30/11/2020

ሰበር ዜና

የበርካታ ኢስላማዊ ተቋማት መስራችና የቲሞች አባት የሆኑት የ 84 አመቱ ሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ ታሰሩ።‼

በቀጥታ ይድረስ ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ👉 የ84 አመቱ ታላቅና የሀገር ባለውለታ ሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ በግፍ መታሰራቸውን ስለማሳወቅ!

ህዳር 21/2013 ሰኞ

የኢትዮጲያ ቅዱስ ቁርኣን ማህበር መስራችና ፕሬዝደንት፣ የቲሞች አባት፣ በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች በርካታ መድረሳዎችንና መሳጂዶችን የገነቡት ሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ በእስር ላይ መሆናቸው ታወቀ።

ታላቁ ሰው ሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ ቅዳሜ እለት ህዳር 19/2013 በሰበታ ከተማ ፉሪ 04 ፍፁም በላይ ህንፃ ጀርባ የሚገኘውና ከ 40 አመት በላይ በሆነው በነጃሺ የአረብኛ ትምህርት ሁለገብ ማሰልጠኛ መስጂድና ማዕከል ግንባታ በተጀመረበት በሐጅ ሙሀመድ አወል ራጃ መስጂድ ቅጥር ጊቢ መጋዘን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማየት በሄዱበት መታሰራቸውን ለማወቅ ችለናል።

በአንቀጽ 19፣ ንኡስ አንቀጽ 3፣ የአገሪቷ ሕገ መንግስት፣ ዜጎች ሲታሰሩ በ48 ሰዓት ዉስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው በግልጽ ቢደነግግም ይህን ግልፅ መርህ በመጣስ ዛሬም ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

በአሁኑ ሰዓት በሰበታ ከተማ ፉሪ በሰበታ ከተማ መስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የክ/ከተማ ሦስት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በአንድ ክፍል ከ 150- 200 እስረኞች ተፋፍነው በሚታሰሩበት እጅግ አሰቃቂ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ይገኛሉ።

ይህን እስር ቤት ቦታው ድረስ በመሄድ እንዳጣራነውና የተለያዩ ታሳሪዎችን በማናገር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው "እስር ቤቱ ውስጥ በርካታ ንጽሀን ካለአንዳች ጥፋት እንዲታሰሩ በማድረግና እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ፖሊስና መርማሪ ትስስር በመፍጠር የሙስና ወንጀል የሚከናወንበት መሆኑን ተረድተናል።

እስር ቤቱ ውስጥ ዜጎች ፍርድ ቤት ሳያውቃቸውና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ገንዘብ እንዲያመጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ከ 4 ወር በላይ የሚታሰሩ ንጽሀን እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል። በእስር ቤቱ ቅጥርም ይሁን ቢሮዎች ውስጥ ታሳሪና ፖሊስ ምንም አይነት የኮቪድ ጥንቃቄ ፈፅሞ የማይደረግና በተለይም ማስክ እንኳን ስለማይለበስ በእድሜ የገፉ ሰዎች በበሽታው የመጠቃት እድላቸው ሰፊ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።

አንዳንድ የፖሊስ አበላትን በቦታው ሄደን እንዳናገርናቸው የግለሰቦች መፈንጫና ሙስና እጅግ የተበራከተበት ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን አስረድተውናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮምሽን ይህን እስር ቤት ያውቀው ይሆን?

እንደሚታወሰው ዶ/ር አብይ አህመድ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ቅዱስ ቁርዓን ማህበር በተዘጋጀው የኡድሁያ ፕሮግራም ላይ በዑመር ኢብኑ አል-ኸጠብ የቁርዓን ት/ቤት ተገኝተው ከወላጅ አልባ ህፃናት ጋር በዓል ሲያከብሩ ከሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ ጋር ተገናኘተው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ምሥጋና አቅረበውላቸው ነበር።

ሀጅ ሙሐመድ አወል ራጃ በሀገራችን 157 መድረሳዎች፣ 57 መስጂዶች እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በመላው ሀገሪቱ የገነቡ ታላቅ ባለውለታ መሆናቸው ይታወቃል። ሀጂ በእድሜ የገፉ በመሆናችው(84/5 አመታቸው ነው) ከ 150 በላይ እስረኛ ባለበት ጠባብ ክፍል ላይ መታሰራቸው ሕይወታቸውን አደጋ ውስጥ የሚጥል በመሆኑ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና መንግስት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንፈልጋለን።

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ዶክተር ዐቢይ አህመድ እኚህ ታላቅ የሀገር ታላቅ ባለውለታ፤ የሀገር ሽማግሌ፣ የሀይማኖት መምህር፣ የወላጅ አልባ ሕፃናት መከታ... ካለምክንያትና ግለሰቦች ሙስና ለመስራት ሲሉ ብቻ በአሰቃቂ እስር ቤት ታስረው ይገኛሉና፤ አፋጣኝ የሆን ማጣራትን በማድረግ አባታችንን ከእስር ከማስፈታት ጀምሮ፥ እንዲህ አይነት ወንጀል የፈጸሙ በሕግ ሽፋን የሚንቀሳቀሱ አካላት ሕዝበ ሙሥሊሙና መንግሥት መካረር ውስጥ እንዲገባ እየሰሩ በመሆናቸው ለፍርድ እንዲያቀርቧ ስንጠይቅ እንደሚያከነውኑት በማመን ነው።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት የተከበሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ- እርስዎ በሚያስተዳድሩት በሰበታ ከተማ የፉሪ የክ/ከተማ ሦስት ፖሊስ ጣቢያ በተቋም መመሪያና ሕግ የሚተዳደር ሳይሆን ግለሰቦች የፈለጉትን በማሰርና በመደብደብ ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ ሙስና የሚሰሩበት በመሆኑ ይህ ጉዳይ ከሕዝብ ጋር ለበርካታ ጊዜያት መሻከርን የፈጠረ በመሆኑ በፖሊስ አበላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እብዲወስዱ ስንል አበክረን እንጠይቃለን።

ከዚሁ እስር በስተጀርባ ዜጎችን በማሰቃየት የሙስና ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትን እንደአስፈላጊነቱ የምንገልጽ ይሆናል።

ግልባጭ
ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤ
ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ለኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
ለኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ

Address

Jeddah

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jemal Hassen Ousman posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share