Highway Star

Call Directions

Highway Star brief any difficult reserves, question and also........................!!!!!!!//

የኮስሞስ ሳዱካ አባት በአራት አመቱ ነበር የሞተበት፡፡ ድሮውንም የተወላዳ ኑሮ ስላልነበራቸው የአባትየው መሞት ችግር ውስጥ ጣላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት በአራት አመቱ ከወንድሙ ጋር መንገድ ላይ...
22/05/2021

የኮስሞስ ሳዱካ አባት በአራት አመቱ ነበር የሞተበት፡፡ ድሮውንም የተወላዳ ኑሮ ስላልነበራቸው የአባትየው መሞት ችግር ውስጥ ጣላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት በአራት አመቱ ከወንድሙ ጋር መንገድ ላይ ምግብ እያዞሩ መሸጥ ጀመሩ፡፡ ናይጄሪያ ውስጥ ለመክሰስ የሚሸጠውን እና ከባቄላ የሚሰራውን አካራ እየዞረ ሲሸጥ ጎበዝ ሴልስ መሆኑ ያስታውቅ ነበር ይባልለታል፡፡

እድሜው ሰባት አመት ሲደርስ በኢግባ አዲቦ ሲስተም ለስራ ሃብታም አጎቱ ጋር ተላከ፡፡ በናይጄሪያ ኢግባ አዲቦ ሲስተም የሚባል ባህላዊ አሰራር አለ፡፡ አንድ ሰው ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ ወደ ከተማ ይሄዳል፡፡ ከዛ ቢዝነስ ተሳክቶለት ጥሩ ስራ መስራት ሲጀመር ወደ አደገበት ገጠር ተመልሶ ወጣት ልጆችን ወደ ከተማ ይዞ ይሄዳል፡፡ እነዚህ ልጆች ከሰውየው ጋር እየሰሩ ከሰባት እስከ ስምንት አመታት ይቀመጣሉ፡፡ ይሄ ቢዝነስ እንዴት እንደሚሰራ እንዲማሩ ይጠቅማቸዋል፡፡ በመቀጠልም ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስፈልገውን ገንዘብ ባለ ሃብቱ ይሰጣቸው እና የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ ይረዳቸዋል፡፡

በዚሁ ሲስተም መሰረት ኮስሞስ ወደ አጎቱ የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች የመሸጥ ቢዝነስ ተቀላቀለ፡፡ ምግቡን አጎቱ የሚያቀርበለት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ በሱቁ ውስጥ ፍራሽ አንጥፎ ሱቁን እየጠበቀ ያድራል፡፡ በዚህ ሲስተም ልጆቹ መጨረሻ ላይ ለቢዝነስ መጀመሪያ ከሚሰጣቸው ገንዘብ ሌላ በየወሩ ደሞዝ አይከፈላቸውም፡፡ አጎቱን ሰባት አመት ካገለገለ በሆዋላ ከአጎቱ ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባት ጀመሩ፡፡ በዚህ ምክንያት ላገለገለበት የናይጄሪያን 200 ናይራ ሰጥቶ ከስራ አሰናበተው፡፡ በጊዜው 200 ናይራ ማለት አንድ ዶላር ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ኮስሞስ ለአጎቱ “ሰባት አመት አገልግዬ የሚገባኝ ይሄ አይደለም፡፡ የዛሬ አምስት አመት እንገኛኝ፡፡ ያረከኝ ነገር ይፀፅትሃል” ብሎ ተናገረው፡፡

መጀመሪያ ከወንድሙ ጋር ሆነው የመለዋወጫ ሱቅ ከፈቱ፡፡ ከወንድሙ ጋር በብር አያያዝ መስማማት ስላልቻሉ ሱቁ ተዘጋ፡፡ በመቀጠል ከጓደኛው ጋር ሆነው ኮስዴቭ የተባለ የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች ሱቅ ከፈቱ፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ግን ከስረው ሱቁ ተዘጋ፡፡ በሶስተኛ ዙር ከሚስቱ ከቻሪቲ ጋር በመሆን ኮስቼር ሞተርስ የተባለ የመለዋወጫ እቃዎች ሱቅን በ300 ናይራ ከፈተ፡፡ “ነጋዴ ስትሆን እቃን እንዴት መሸጥ እንዳለብህ ብቻ ሳይሆን እቃን ከየት ገዝተህ ማምጣት እንዳለብህ ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ እኛ ስራውን ስንጀምር ብር ስላልነበረን በዱቤ እቃ የሚሰጡንን አካፋፋዮች ደጅ መጥናት ነበረብኝ፡፡ የቤት ኪራይን እና ሌላም ሌላም ወጪ በዱቤ ለማግኘት ወይም ዋጋ ለማስቀነስ መሟሟት ነበረብኝ” ብሏል፡፡

በ1982 አ.ም የናይጄሪያ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የመለዋወጫ አስመጪነት ፈቃድን ለአስር የግለሰብ ድርጅቶች ሰጠ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ኮስቼር ሞተርስ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ኮስሞስ ከጃፓን የመኪና እና የሞትር ሳይክል መለዋወጫዎችን እያስመጣ በናይጄሪያ ማከፋፈል ጀመረ፡፡

ዛሬ ኮስቼርስ ሞተርስ ቢዝነስ በስሩ ብዙ ቢዝነሶችን አካቷል፡፡ በናይጄሪያ ብቸኛው የቢኤምደብሊው (BMW) መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ፤በ 5000 ሄክታር ላይ ያለ የሩዝ እርሻ፤ ብቸኛው የሮል ሮይስ፤ ፎርድ፤ ጃጉዋር እና ሬንጅ ሮቨር አስመጪ እና አከፋፈይ እና የተለያዩ ፔትሮኬሚካሎች አምራች ድርጅት ነው፡፡የድርጅቱ ሃብትም ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡

ኮስሞስ ለስኬቱ እንደ ዋና ምክንያት የሚያየው ከጃፓናውያን ጋር የነበረውን ቅርርብ፡፡ “ከጃፓናውያን ጋር በነበረኝ ቅርርብ ምክንያት ለስራ ፍቅር እንዲኖረኝ ሆኛለሁ፡፡ ለቃል መገዛትን፤ የደንበኞችን ፍላጎት ማክበርን፤ ገንዘብን በጥንቃቄ መያዝን እና ጠንክሮ መስራትን ከነሱ ነው የተማርኩት” ብሏል፡፡ኮስሞስ በተለያዩ መድረኮች እየተገኘ አነቃቂ ንግሮችን በማድረግ እና ለናይጄሪያ ወጣቶች የራሱን የህይወት ልምዶች በማካፈል ለስራ የሚያነሳሳ ሰው ነው፡፡

ኮስሞስ ከሰጣቸው የቢዝነስ ምክሮች ውስጥም
1. ቢዝነስ ለመስራት የሚያስፈልገው ካፒታል ብቻ አይደለም፡፡ ልትሰሩ ወይም ልትገቡ የምትፈልጉበትን ቢዝነስ ማወቅ ነው መጀመሪያ የሚያስፈልገው፡፡ የገንዘብ አስፈላጊነት 40 በመቶ ያህል ነው፡፡ ዋናው ስለቢዝነስ ብቻ ሳይሆን ልትሰሩ ስላሰባችሁት ቢዝነስ እና ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ያላችሁ እውቀት ነው ይላል፡፡
2. ለራሳችሁ እና ለስራችሁ ጥርት ያለ ራእይ ከሌላችሁ ችግር እና ኪሳራ በቀላሉ ይበግራችሁዋል፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ራእይ ይኑራችሁ፡፡ ልትደርሱበት የምትፈልጉበትን ነገር ጠንቅቃችሁ እወቁ ብሎ ኮስሞስ ይመክራል፡፡

20/05/2021

መሣሪያችንን ጥለን ብዕራችንን እናንሣ።
በቅርብ ቀን!!!

ዲጅታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?ለአነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶች እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን?ማርኬቲንግ ስንል አንድ ቢዝነስ ወይም ግለሰብ የሚያመርተውን ምርት ወይም የሚሰጠውን አገልገሎ...
20/05/2021

ዲጅታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?
ለአነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶች እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን?

ማርኬቲንግ ስንል አንድ ቢዝነስ ወይም ግለሰብ የሚያመርተውን ምርት ወይም የሚሰጠውን አገልገሎት ለማስተዋወቅ እና ደንበኞችን ለማፍራት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው፡፡

በአለማችን ላይ የኢንተርኔት ተደራሽነቱ ከመስፋፋቱም አንፃር ኢንተርኔት የሚጠቀመው ሰው፤ ኦንላይን የሚገባው ሰው በየቀኑ እየጨመረ ነው እየሄደ ያለው፡፡የኢንተርኔት መስፋፋት መረጃዎችን የምናገኝበት መንገድ፤ ከሰዎች ጋር የምንገኛኝበትን/ የምናወራበትን መንገድ እና የምንገበያይበትን መንገድ ቀይሮታል፡፡ ያው እንዳልኩት እንግዲህ እቃዎችን ወይም አገልገሎቶችን የምንሸጥበት፤ የምንገዛበት፤ ከደንበኞቻችንን ጋር የምንገኛኝባቸው መንገዶች ኦንላይን እየሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ከነዚህ ለውጦች ጋር ተያይዞ ማርኬቲንግ የምንሰራበት/ገበያ የምናፈላልግበት መንገድም ተቀይሯል፡፡ ስለዚህ ዛሬ የምንወያየው ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ምን አይነት የዲጂታል ማርኬቲንግ አይነቶች አሉ? አነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶች ዲጅታል ማርኬቲንግን ተጠቅመው እንዴት ቢዝነሳቸውን ማሳደግ ይችላሉ? የሚሉት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ስለ ዲጂታል ማርኬቲንግ ለመወያየት በዘርፉ ሃገራችን ውስጥ በቀዳሚነት እየተንቀሳቀሱ ካሉ አንድ ባለሙያ ጋር በስቱዲዮችን ያደረግነውን ውይይት እንጋብዛችኋለን፡፡

በሃገራችን የስቶክ ማርኬት ሊጀመር ነው!ስቶክ ማርኬት ምንድን ነው?ስንት አይነት ስቶኮች አሉ? ጥቅሙስ ምንድን ነው?እንዴትስ ልንገበያይ እንችላለን?
21/04/2021

በሃገራችን የስቶክ ማርኬት ሊጀመር ነው!
ስቶክ ማርኬት ምንድን ነው?
ስንት አይነት ስቶኮች አሉ? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
እንዴትስ ልንገበያይ እንችላለን?

የአለምን የክትባት ገበያ የተቆጣጠረው ድርጅት ወደ ስራ የህንዱ ሴረም ኢንስትቲዩት Serum Institute of India (SII) በአለም በጣም ታዋቂ ድርጅት አይደለም፡፡ ነገር ግን በአለማ...
18/04/2021

የአለምን የክትባት ገበያ የተቆጣጠረው ድርጅት
ወደ ስራ

የህንዱ ሴረም ኢንስትቲዩት Serum Institute of India (SII) በአለም በጣም ታዋቂ ድርጅት አይደለም፡፡ ነገር ግን በአለማችን ያለ ትልቁ የክትባት አምራች የግል ድርጅት ነው፡፡ ህንድ ፑኔ በሚገኘው ትልቅ ፋብሪካ ውስጥ ይህ ድርጅት በአመት 1.5 ቢሊየን ዶዝ የተለያዩ ክትባቶችን ያመርታል፡፡እንደ ከእነ አስታራ ዜንካ እና ከመሰል ድርጅቶች ኮንትራት እየተቀበለ የኮሮና ክትባቶችን እያመረተ ይገኛል፡፡

የድርጅቱ መሪ አዳር ፑንዋል እንዳለው ከሆነ “ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የወሰድነው ሪስክ አለ፡፡ ብዙዎቹ ክትባቶች የፈቃድ ሂደቱን ሳያጠናቅቁ ነው ስራ የጀመረነው፡፡ ያው አስበንበት ነው ለምሳሌ የአስትራ ዜንካ ክትባት በኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ሳይንቲስቶች የተሰራ ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ሳይንቲስቶች ጋር በተለይ ደግሞ በወባ ክትባት ዙሪያ አብረን ስለሰራን በስራቸው ላይ እምነት ነበረን” ብሏል፡፡

ክትባቶቹን ለማምረት ድርጅቱ ከራሱ ካዝና 260 ሚሊን ዶላር ወጪ አድርጓል፡፡ የተረፈውን ገንዘብ ደግሞ ከነቢል ጌትስ እና መሰል በጎ አድራጊዎች ሲያገኝ ቀሪውን ደግሞ ከሃብታም ሃገራት ለሚሰጣቸው ክትባቶች ቀብድ ተቀብሎ ነው ወደ ስራ የገባው፡፡ እንደ አዳር ከሆነ “እኛ መስከረም ላይ ወደ 600 ሚሊየን ዶዝ የኮሮና ክትባቶችን አምርተን ጨርሰን ነበር፡፡ ይሄንን ያደረግነው ደግሞ ሪስክ ወስድን ማምረቱን ስለጀመርን ነው” ብሏል፡፡ ድርጅቱ የግል ድርጅት ስለሆነ በቀላሉ ውሳኔዎችን ወስነው ወደ ስራ ለመግባት መቻላቸው ለዚህ ስኬት እንዳበቃቸው ይገመታል፡፡

እንደ ድርጅቱ መሪ ከሆነ ፈቃድ ሰጪ አካላት በክትባቱ ጥራት እና ደረጃ ላይ የራሳቸውን ህግ ከማውጣት ይልቅ ቢስማሙ ኖር በተቻለ መጠን ብዙ ክትባት ማምረት ይቻላል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለራሱ፤ እንግሊዝ እና አሜሪካም ለየብቻቸው ስለ ክትባቶቹ ህግ ከሚያወጡ ይልቅ በአንድነት አንድ አይነት የጥራት መመዘኛዎች ቢያዘጋጁ ይሻላል ባይ ነው፡፡

ስራ እና አዎንታዊ አስተሳሰብ (Positive thinking) ወደ ስራ በስራም ሆነ በትምህርት አለም ውስጥ አዎንታዊ አስተሳብ እንዲኖረን ይመከራል፡፡ይሄ ማለት አእምሯችንም ሆነ ስሜታችንን ተ...
24/03/2021

ስራ እና አዎንታዊ አስተሳሰብ (Positive thinking)
ወደ ስራ
በስራም ሆነ በትምህርት አለም ውስጥ አዎንታዊ አስተሳብ እንዲኖረን ይመከራል፡፡ይሄ ማለት አእምሯችንም ሆነ ስሜታችንን ተቆጣጥርን በቻልነው አቅም ጥሩ እና መልካም ነገሮች ላይ ብቻ ማተኮር እና ማሰብ እና በስራችንም ሆነ በትምህርታችን ላይ መልካም ነገር ያጋጥመናል ብሎ ማመን ነው፡፡ ስለዚህ አስተሳሰባችን በአዎንታዊነት ከተቃኘ የምናስበው ስኬትን ማግኘትን ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ በስራ ቦታችን ይሄንን አዎንታዊ አስተሳሰብ ብንይዝ ስራችን ቀለል ብሎን መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
1. ስራችንን ስንጀምር፤ ጠዋት ላይ መልካም ነገሮችን በማሰብ እና በመናገር ብንጀምር ይመከራል፡፡

ብዙ ቢሮዎች ውስጥ የምትለጠፍ አንድ ጥቅስ አለች፡፡ ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል ወይም ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው ይላል ጥቅሱ፡፡ ይሄ እንግዲህ ጠዋት ሲገቡ ያንን ጥቅስ በማየት ቀኑን ደስ በሚል ስሜት ለመጀመር ነው፡፡ ስለዚህ ስራችንን እና ቀኑን መልካም ነገር በማሰብ እና በመናገር መጀመር ይቻላል፡፡

2. በስራ ቦታ ላይ አብረውን የሚሰሩ ሰዎች ፖዘቲቭ (ቀና አስተሳሰብ) ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ አብረውን የሚሰሩ ሰዎችን መምረጥ ባንችልም ከነሱ ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ግን መገደብ እንችላለን፡፡ ስራ ቦታ ላይ አብረናቸው የምንሰራ ሰዎች ለነገሮች ቀና አመለካከት ያላቸው እና ለስራ ፍቅር ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ለስራ ተነሳሽነት እንዲኖረን ያደርጉናል ያ ቀና አስተሳሰብ ይጋባል፡፡

3. የሚሰራ ሰው መሳሳቱ አይቀርም ስለዚህ ስራ ላይ ስህተት ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ ስህተቱን ለመማር እና እራሳችንን ለማሻሻል ብንጠቀምበት ጥሩ ነው፡፡

ስህተት ስንሰራ ሌላ ሰው ላይ ስህተቱን ለማላከክ ከመሮጥ፤ ወይንም ደግሞ እኔ አላረኩትም ብሎ ከመከራከር ከዚህ ስህተት ምን መማር እችላለሁ፤ በሚቀጥለው ጊዜ ይሄን አይነት ሁኔታ ሲያገጥመኝ ምን ማስተካከል እችላለሁ የሚለውን ማሰብ ጥሩ ነው፡፡

4. ሌላው ነገር ደግሞ ከራሳችን ጋር ስናወራ አሉታዊ የሆነ እና ጨለምተኛ የሆነ ወሬዎችን ማውራት ማቆም አለብን፡፡ ለምሳሌ፡- አሁን የተሠጠኝን አዲስ ስራ እያበላሸሁት ነው፡፡ ዝም ብዬ እኮ ነው ከበድ ስራ ማን ተቀበይ አለኝ፡፡ እኔን ብሎ ታታሪ ሰራተኛ አይነት ወሬዎች ከራሳችን ጋር የምንጨዋወት ከሆነ ይሄ ለራሳችን ጨለምተኛ አመለካከት ያዝን ማለት ነው፡፡ ከውጪ ወይም ከሌላ ሰው ማበረታቻ ወይም አድናቆት ከመጠበቃችን በፊት ራሳችንን ማበረታት እና የተሻለ ስራ ለመስራት ማነሳሳት አለብን፡፡

24/03/2021
ኢንቨስትመንት ግን ምንድን ነው?ዩሴን ቦልት በሶስት ኦሎምፒኮች ተሳትፎ 8 የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል፡፡ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 115 ሰከንዶችን ብቻ ሮጧል፡፡ በዚህ ግዜ ግን ከ110 ሚሊየን...
09/03/2021

ኢንቨስትመንት ግን ምንድን ነው?
ዩሴን ቦልት በሶስት ኦሎምፒኮች ተሳትፎ 8 የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል፡፡
በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 115 ሰከንዶችን ብቻ ሮጧል፡፡ በዚህ ግዜ ግን ከ110 ሚሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት በቅቷል፡፡ ለነዚህ 2 ደቂቃዎች ሲል ግን ከ20 አመታት በላይ በልምምድ አሳልፏል፡፡
ኢንቨስትመንት ሩቅ ማሰብ ማለት ነው፡፡ አለመታከት እና ትእግሰት ሁሌም ዋጋቸው ትልቅ ነው፡፡

ሞሪንጋ ተክል ለመድሀኒትነት እንደሚውል በምርምር ተረጋገጠ — ኢንስቲትዩቱ**************************ሞሪንጋ እንዲሁም ሽፈራው እየተባለ የሚጠራው ተክል ለተለያዩ በሽታዎች ለመድሃ...
28/02/2021

ሞሪንጋ ተክል ለመድሀኒትነት እንደሚውል በምርምር ተረጋገጠ — ኢንስቲትዩቱ
**************************

ሞሪንጋ እንዲሁም ሽፈራው እየተባለ የሚጠራው ተክል ለተለያዩ በሽታዎች ለመድሃኒትነት መዋል እንደሚችል በምርምር መረጋገጡን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በሞሪንጋ ዙሪያ በተደረጉ የምርምር ስራዎች ዙሪያ የሚመክር መድረክ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ የኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ እንደገለጹት ኢኒስቲትዩቱ የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የአስር አመት መሪ ዕቅድ በማውጣት ወደ ስራ ገብቷል።

“ሀገር በቀል ዕውቀት በመጠቀም ባህላዊ መድሀኒቶችን በዘመናዊና ሳይንሳዊ ጥናቶች ለመደገፍ የትኩረት አቅጣጫ በማደረግ ከሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጋቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች ጉልህ ስፍራ አላቸው” ብለዋል።

ኢኒስቲቲውቱ ካተኮረባቸው መካከል ሞሪንጋ ለህብረተሰቡ ደህንነት ደረጃውን የጠበቀ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል ።

ሞሪንጋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገሪቱ ትኩረትን እየሳበ የመጣና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሀገር በቀል እጸዋት መሆኑን ተናግረዋል ።

እጽዋቱ ለመድሀኒትነት ያለውን ፋይዳ በምርምርና ጥናት በመለየት በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በኢንስቲትዩቱ መሪ ተመራማሪና የሞሪንጋ ምርምር ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር አስፋው ደበላ በበኩላቸው በምርምሩ የጤና፣ ስነምግብ፣ የግብርና፣ የትምህርትና ሌሎች 13 ተቋማት ተሳታፊ ሆነውበታል።

Address

Riyadh

Telephone

+966553105517

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Highway Star posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share