JY Business Group

JY Business Group First Geez (Geéz) physical computer keyboard with software. Designed and developed by small firm owned by ሓበሽ in Uppsala, Sweden.

A frim for a better computing support of the Geez writing system.

Hi everyone! Just go to https://www.youtube.com/watch?v=27HZDSCs8jAand comment!A lot more to come soon!
18/05/2019

Hi everyone! Just go to https://www.youtube.com/watch?v=27HZDSCs8jA
and comment!
A lot more to come soon!

ITence Advanced Geez Softkeyboard- the latest, most advanced and dynamic Android input method for Geez.

25/02/2013

ካጻጻፍ ይወረሳል…
(ክፍል ሁለት- Elegance, Simplicity & Harmonic Pattern)

ባለፈው ጽሁፋችን- ክፍል አንድ- የዛሬው ትውልድ ታላቅ የፈጠራ ስራ ወራሽ በመሆኑ ኩራት ሊሰማው ይገባል ከማልት በቀር ስለዛ ታላቅ የፈጠራ ስራ ብዙም የጠቀስነው ነገር አልነበረም። ጠለቅ ብለን ከተመለከትን ግን ፊደሎቻችን የአወዳደቅ መልካቸው ግሩም ከመሆኑ ሌላ፤በመሰረቱ ሲታቀዱ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ረቂቅ የፈጠራ ተግባር ውጤት መሆናቸውን ለመገንዘብ ብዙም የሚያዳግት አይደለም።

እያንዳንዱ ንፁር ፊደል አንድ ድምፅ መወከሉ የማንበብ እና የመፃፍ ሂደትን ከሚገባው በላይ ያቀላጥፋል። ከእንግሊዝኛ ጋር ብናወዳደር ”ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ’ን” አጥንተን ስናበቃ ማንበብ እና መፃፍ እራሱን የቻለ የትምህርት ጉዞ ሲያስፈልገው፤”አቡጊዳ’ን” ተምረን ስናበቃ ግን ማንበብ እና መፃፍ- አነጻጽሮ ለሚችል- ተያይዞ የሚመጣ ገፀ-በረከት ነው። ከደቡባዊ-፣ ከመሃል- እንዲሁም ከሩቅ-ምስራቅ ኤዢያውያን አገሮች የአጻጻፍ ስልቶች ጋር ብናወዳድር፤ ያለማጋነን ስእሎችን ከ-የጭረቶች ስብስብ ጋር ማወዳደር ይሆናል።

ስለሌሎቹ አናውቅም፤ ግእዝን በሚመለከት ግን አንድ እስካሁን ያስቀመጥነው ድብቅ፣ውብ ጠባይ አለ። ይህን ድብቅ ውበት ሁላችንም ገና "ቄስ ትምህርትቤት" ስንሄድ አንስተን የተዋወቅነው ዜማዊ፣ ተደጋጋሚ እና በሰፊው የተበተነ ክስተት ነው። ወደ የድንጋይ ዘመን መመለስ አይሁንብን እንጂ፤ ስንቶቻችን ነን የማናስታውስ፤ አንገት ላንገት ተያይዘን (ተቃቅፈን) ከፊት ወደ ኋላ እየተናጥን ሀ-ግእዝ፣ ሁ-ካኢብ፣ ሂ-ሳልስ ... እያልን ስንቆጥር᎒ ;)

በአጭሩ፤ እኛ ግእዝን የምናቆራኘው ከውበት፣ ቅለት እና ዜማዊ ተዛማችነት ጋር ስለሆነ፤ እነዚህ ጠባዮች ደግሞ እያስተጋቡ እንዲኖሩ ማየት ምኞታችን ነው። ተደጋጋሚ ዜማውነትን ከጥቂት ለማስታወስ ቀላል ከሆኑ መምሪያዎች ጋር በማጣመር ቀለማት ላይ የተመረኮዘ ሰሌዳአቋልፍት ከነ ፕሮግራሙ በመንደፍ ይህንን ምኞች ለማንጸባረቅ ሞክረናል ብለን እናምናለን።

አንድ በስነ-ንድፍ ላይ የተመረኮዘ የስራ ውጤት ጥራቱ በምን ይለካል ብለን ብንጠይቅ መልሱን በርግጠኝነት ልናገኝ የምንችለው ተጠቃሚዎቹ ወይንም ታዛቢዎቹ ከሚያገኙት ርካታ አንጻር ይሆናል። ተጠቃሚዎቹ ከንድፉ ቅለት የተነሳ ስራዉን በሚጠቀሙበት ጊዜ ከራሳቸው ዘንድ ብቁዎች ነን የሚል ስሜት ሊያሳድሩ ከቻሉ፤ የስራ ውጤቱ አስፈላጊውን የጥራት ደረጃ አሟልቷል ማለት ይቻላል። ከዚህ ጋር አያይዘን ለውድ አንባቢያን አንድ ጥያቄ ለማቅረብ እንወዳለን።

ሰሌዳአቋልፍቱን ጠጋ አድርገን (full screen) ብንመለከት፤ አይኖቻችን ሊስትዋቸው የማይችሉ አምስት ቀለማት ከመኖራቸው ሌላ በደንብ ለተገነዘበ ፊደላት ለ፣ሉ፣ሊ፣ላ፣ሌ እና ሎ አንድ ቀለም ከመካፈላቸው ሌላ በአካል ከሌሎቹ አነስ ይላሉ። የትኞቹ አቋልፍት ላይ ተስለው እንደሚገኙም ልብ እንበል- "የላቲን ቫወልስ" ከተሳሉባቸው አቋልፍት ለይ። ሁለቱ ልዩ ቀለም ያላቸውን አቋልፍት ሳንዘነጋ፤ አስቀድመን የጠቀስናቸውን ቀለማዊ እና ይዞታዊ ዝርዝሮችን ብንቀይጥ ምን አይነት ትርጉማዊ ግንዛቤ እናገኛለን᎒

አብዛኞቻችሁ ትክክለኛውን ግንዛቤ ሳታገኙ እንዳልቀራችሁ ባለመጠራጠር፤ እንዳናሰለቻችሁ በመፍራት ክፍል ሁለትን በዚህ ለመዝጋት እንመርጣለን። በሌላ በኩል ግን ያልፈው ጊዜ ቃላችንን ልንጠብቅ ባለመቻላችን ይቅርታ ስንጠይቅ በክፍል ሶስት በሰላም ያገናኘን እያልን ይሆናል።

ሠላም እና ጤና!

Adress

Kirkos Subcity, Woreda 04
Uppsala

Öppettider

Måndag 07:00 - 17:00
Tisdag 07:00 - 17:00
Onsdag 07:00 - 17:00
Lördag 07:00 - 17:00

Telefon

+251937622913

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när JY Business Group postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Dela