08/31/2026
🤖 AI ማለት ChatGPT ወይም Gemini ብቻ ነው?
ብዙ ሰዎች “AI” ሲባል መጀመሪያ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ChatGPT ወይም Gemini ነው።
ግን ChatGPT የAI አንዱ መተግበሪያ ነው። AI ራሱ ግን ከዚህ በጣም ሰፊ ነው።
በቀላሉ እንየው 👇
1️⃣ AI — Artificial Intelligence
AI (Artificial Intelligence) ማለት ኮምፒውተሮች በተለምዶ የሰው አስተዋይነት የሚፈልጉ ሥራዎችን እንዲሰሩ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።
ለምሳሌ፦
• ጽሑፍን መረዳት
• ምስልን መለየት
• ቋንቋ መተርጎም
• ጥያቄዎችን መመለስ
• በመረጃ ውስጥ patterns መለየት
2️⃣ Generative AI
Generative AI ደግሞ አዲስ content ለመፍጠር የሚያገለግል AI ነው።
ለምሳሌ፦
📝 ጽሑፍ
🖼️ ምስል
🎥 ቪዲዮ
🎵 ድምፅ/ሙዚቃ
💻 Code
ሊፈጥር ይችላል።
3️⃣ LLM — Large Language Model
ChatGPT, Claude እና Gemini የሚጠቀሙባቸው ዋና ቴክኖሎጂዎች መካከል LLM (Large Language Model) ይገኛል።
LLM ብዙ የጽሑፍ መረጃ ላይ ተምሮ ቋንቋን ለመረዳትና ምላሽ ለመፍጠር የሚጠቅም የAI model ነው።
4️⃣ ChatGPT, Claude እና Gemini ምንድናቸው?
እነዚህ AIን እንድንጠቀም የሚያስችሉን AI assistants ናቸው።
ከእነሱ ጋር በተለመደ ቋንቋ መነጋገር፣ ጥያቄ መጠየቅ፣ ነገሮችን ማስረዳት፣ ሃሳብ ማመንጨት፣ ጽሑፍ ማዘጋጀት እና ሌሎች ብዙ ሥራዎችን ማገዝ ይችላሉ።
💡 አንድ ቀላል ምሳሌ
Google ላይ፦
“Professional email example”
ብለህ ከመፈለግ ይልቅ AIን (ChatGPT, Claude እና Gemini )፦
“ለManagerዬ ነገ ከሰዓት በኋላ ለቤተሰብ ጉዳይ ፈቃድ የምጠይቅበትን አጭርና professional email ጻፍልኝ።” ብላቹ ብትጠይቁት ለራሳችሁ ሁኔታ የተዘጋጀ ምላሽ ማግኘት ትችላለህ።
⚠️ ግን አንድ ነገር አትርሱ።
AI የሚሰጠው መልስ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም። ጠቃሚ ወይም ወሳኝ መረጃ ከሆነ ማረጋገጥ (verify) ያስፈልጋል።
🎯 የዛሬ Challenge
ChatGPT, Claude ወይም Gemini ክፈቱና ለረጅም ጊዜ ለመረዳት የከበዳችሁን አንድ ነገር ምረጡ።
ከዚያ፦
“ይህን ርዕስ ምንም እንደማላውቅ በመቁጠር በቀላል ቋንቋና በምሳሌ አስረዳኝ።”
ብላችሁ ጠይቁት።
👇 እናንተ AIን በአሁኑ ጊዜ በብዛት ለምን ትጠቀማላችሁ?